Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

‹‹ያሲን ኑሩ የመንግስት ቅጥረኛ ነውን››?

‹‹ያሲን ኑሩ የመንግስት ቅጥረኛ ነውን››?
ይህን ልጠይቅ የቻልኩት ወደ አርባምንጭ በመሄድ ለዩኒቨርስቲ ተማሪዎች በገዛ መድረሳና መስገጃቸው ላይ የተውሂድ ትምህርት ስንሰጥ BBN እና መሰል ተከታዬቻቸው ‹‹የመንግስት ቅጥረኞች ስለሆናችሁ ነው ዳእዋ ሄዳችሁ ያደረጋችሁት››፣ ‹‹መንግስት ነው ወጪያቸውን የቻለላቸው›› እና የመሳሰለውን ሲሉ ኡኡኡ ብለው ነበር፡፡
ኢኽዋኖች እነሱን የሚያክል ስም አጥፊ የለም፡፡ እነሱ የሚሰሩትን እስላማዊ ቅብ ይቀቡታል፡፡ እነሱ ስሙን ሊያጠፉ የሚፈልጉትን ሰው የሌለ ስም ይሰጡታል፡፡ አርባ ምንጭ ሄዶ ዳዕዋ ማድረግ ‹‹የመንግስ ቅጥረኛ›› ካስባለ የያሲን ኑሩ በየክፍለ ሀገሩ እየዞረ አንዴ መስጂድ ማስገንባት፣ አንዴ መስጂድ ማስመረቅ፣ አንዴ ዳእዋ እያለ ያን ቢድዐውን ማስፋፋቱን ‹‹ለኢስላም መታገል›› ሊባልለት ነው?
ወደ ጥመት የሚጣሩ እስላማዊ እያለ የሚጠራቸውን ከኢስላም የራቁ መፀሃፎቹን አስተያየት የሚያፅፈው የፖለቲካ ፓርቲ ‹‹የህዝብ አደረጃጀትና ግንኙነት ሃላፊ›› ብለው እራሳቸውን የሚጠሩ ካፊሮችን ነው፡፡ ለምሳሌ ብርሃኑ ተ/ያሬድ የሚባልን ግለሰብ፡፡ ለሙስሊሞች የሚቀርቡ ነገሮችን የሚገመግሟቸው የእስልምና ሙሁሮች እንጂ ካፊር ፖለቲከኞች አይደሉም፡፡ ይህ በግልፅ እንደሚያሳየን ፖለቲካ ይፅፍና ኢስላማዊ ቅብ እንሚቀባው ነው፡፡ አሳዛኙ እና ድፍረቱ ይህን ተግባራቸውን ወደ ኢስላም ማስጠጋታቸው ነው፡፡
ሰው በአፍጥር ሰዓት ዱዓ በሚያደርግበት ሰዓት ‹‹ገመድ ጉተታ….›› እያሉ ሰዉን ሊያጃጅሉት ነው፡፡ ሙስሊሞች ሆይ! አፍሪካ ቲቪ ላይ ስንት በዲን ስም የሚወነብዱ ከአህባሽ አቂዳ ምንም ልዩነት የሌላቸው ‹‹አህባሾችን የምንጠላቸው ለፖለቲካል አጀንዳቸው ብቻ ነው›› የሚሉ አደገኛ መርዘኞች አሉ፡፡
ለነፍሱ ያዘነ፣ ለሱና የወገነ እነዚህ ልቦቻቸው ተለያይተው ‹‹አንድ ነን›› እያሉ ከሚሞግቱ አታላዬች እራሱንም፣ ቤተሰቡንም ይጠብቃል፡፡
ያሲን ኑሩ እና ጓደኞቹ ሊያውቁ የሚገባቸው ዛሬ ከኢቅራ ቻናል ላይ ከሚታዩት የስሜት ተከታዬች ኮርጃችሁ የአፍጥር ሰዓት ፕሮግራም እያላችሁ ኡማውን የምታደነዝዙበት እግር ኳስ ጨዋታ በጀለቢያ እና የመሳሰለው ለተዋረዱት ለነነቢል አል-ኢወዲ፣ ለአኢድ አል ቀርኒ፣ ለሙሐመድ አል አሪፊ እንኳን አልሆናቸውም፡፡
ተመለሱ አላህን ፍሩ ከነ ሀሰን ታጁ ጋር የለያያችሁ ሃቅ ላይ ስላልተሰበሰባችሁ ነው፡፡ አሁንም ገና ወደ ሱና ካልቶበታችሁ ውርደትን እንጂ ሌላን አታገኙም፡፡
ያሲን ኑሩ ልታውቅ የሚገባህ በስሜት የሚከተልህና ምንም የማያውቁት ተከታዬችህ ያንተን ፎቶ ፌስቡክ ላይ መለጠፋቸው ሃቅ ላይ ያለህ እንዳይመስልህ፡፡ አትሸወድ፡፡ ሃቁን ስለማትነግራቸው፣ ስሜታቸውን ስለማትነካባቸው ዛሬ ሊወዱህ ይችላሉ ነገ ሃቅን ያወቁ ጊዜ ግን አለቀልህ፡፡ አወልያ ላይ ሚሊዬኖች ነን ስትሉ እንዳልነበር ያ ሁሉ ሚሊየን አልተነነም እኮ ሃቁን ሲያውቅ ትቷችሁ ሄደ እንጂ፡፡
ይህ አብዬታዊ የሰላማዊ ሰልፍና የፖለቲካ አካሄድን ትታችሁ ወደ ነብያት ጎዳና ተመለሱ፡፡ በዚህ ብቻ ነው ሁለት አገር ድልና ስኬት የሚገኘው፡፡ እምቢ ካላችሁ ለናንተ ቀረባችሁ እንጂ ሱና የያዛትን የበላይ እያደረገች ትጓዛለች፡፡ በተለያየ አቂዳና መንሃጅ ላይ ተሰብስባችሁ ህዝቡ ዘንድ ‹‹አንድ ነን›› እያላችሁ የምትዋሹትንም አላህ ስለሚመለከት የትም አትደርሱም፡፡
ተከታዬችህ በየቀኑ ሃቁን እየተረዱት ነው፡፡ እኛ እንደናንተ ሰውን ከመሬት ተነስተን ያለ ማስረጃ አንቀጥፍበትም፡፡ አንተና ጓደኞችህ ከነ ተከታዬቻችሁ ሰውን በምትወርፉበት ጉዳይ ይሀው እንዲህ ስትያዙ መልስ አይኖራችሁም፡፡
ምስጋና ለአላህ የተገባ ይሁን በማስረጃ ብቻ ለማውራትና ለመስራት የመራን የሆነው፡፡