Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ጠያቂ ፦ አንድ ሰው ሱሑር እየበላ ሳለ አዛን ቢልበት አፉ ውስጥ የጎረሰውን የመትፋት ግዴታ አለበትን?

ጠያቂ ፦ አንድ ሰው ሱሑር እየበላ ሳለ አዛን ቢልበት አፉ ውስጥ የጎረሰውን የመትፋት ግዴታ አለበትን?

መልስ (ከታላቁ የየመን ዐሊም ሸይኽ ሙቅቢል ረሒመሁላህ)፦
“አፉ ውስጥ የጎረሰውን መትፋት የለበትም። ነገር ግን ከአዛኑ በሗላ ከአፉ ውጪ ያለውን ሊጨምር (ሌላ ሊጎርስ) አይገባውም።
ውሃን ሲቀር። በአቡ ሁረይራህ ተወርቶ በሱነን አቡ ዳውድ እንደተዘገበው የአላህ መልእክተኛ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል፦
“አንዳችሁ ጥሪን (አዛን) ብትሰሙና እጃችሁ ላይ ኩባያው (መጠጫው እቃ) ካለ ከርሱ የሚያሻውን ያህል እስኪጠቃቀም ድረስ አያስቀምጠው።”
በመሆኑም ሙአዚኑ ለአዛን ጥሪ ቢያደርግም እጅ ላይ ያለን ውሃ መጠጣት ችግር የለውም።”

[ፈታዋ ሊሸይኽ ሙቅቢል ቢን ሃዲ አልዋዲዒ ረሒመሁላህ ]

Www.fb.com/exposingahbashandikhwan