ይፆማል ግን አይሰግድም!
ጥያቄ: – « ሁለተኛው ጥያቄ ደግሞ ሸኽ ሆይ! ሰውየው ይፆማል ግን ሰላት አይሰግድም ። ፆሙ ተቀባይነት አለውን? ይህ (ተግባሩ) ከኢስላም ያስወጣዋልን? »
መልስ ከታላቁ ዐሊም ሸኽ ሙሐመድ አኩር: –
« ፆሙ ተቀባይነት የለውም። ምክንያቱም ፆም ከኢስላም ማዕዘናት ውስጥ አራተኛው አርካን (ማዕዘን) ነው። ከሱ በፊት የእምነቱ መሠረቶች የሆኑት ሁለት ሸሐደተይን (ምስክቶች) አሉ። አንድ ሰው ከአላህ ውጪ በሐቅ የሚገዙት አምላክ የለም ብሎ ከመሰከረና ሙሐመድም የአላህ መልዕክተኛ ናቸው ብሎ ከመሰከረ ቀጥሎ የአምስት ወቅት ሰላቶችን መስገድ በርሱ ላይ ግዴታ ነው ። የሰገደ እንደሆን ምስክሮቹ (ላኢላሃ ኢለላህ ሙሐመደን ረሱሉላህ ማለቱ) ተቀባይነት ይኖረዋል ። ያልሰገደ እንደሆን ምስክሮቹ አይፈይዱትም። ምክንያቱም ከምስክሮቹ አላህ ብቸኛ በሐቅ ተመላኪ ጌታ መሆኑን እና ሙሐመድም የአላህ መልዕክተኛ መሆናቸው ከመመስከር አንዱ ሁኔታ ሰላትን ማቆም (መስገድ) ነው። ይህም የሆነው ከሳቸው (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ሙዐዝን ወደ የመን ሲልኩት ከተናገሩት ቃል (ተነስተን) ነው (እንዲህ አሉት) : –
« መጀመሪያህ የምትጠራቸው አላህን በብቸኝነት እንዲያመልኩ ሙሐመድም የአላህ መልዕክተኛ መሆኑን እንዲመሰክሩ ይሁን። ይህን ከታዘዙህ አላህ በቀንና በሌሊት አምስት ወቅት ሰላቶችን እንደደነገገባቸው አስተምራቸው ። ይህንን ከታዘዙህ ከሃብታቸው ተወስዶ ለድሆቻቸው የሚከፋፈል ዘካን አላህ ግዴታ እንዳደረገባቸው ንገራቸው ። »
በመሆኑም የኢስላም ማዕዘናት አንዱ በአንዱ ላይ የተደጋገፈ ነው ። ስለዚህም ሁለቱ ምስክሮች ያለአምስት ጊዜያት ሰላት ተቀባይነት የላቸውም ። ፆም ያለአምስት ጊዜያት ሰላት ተቀባይነት የለውም ። ዘካህ ያለ በወቅቱ የተሰገደ ሰላት ተቀባይነት የለውም ። እናም ሰላት የስራዎች ሚዛን ነው። የሚሰግድ ስራው ተቀባይነት ይኖረዋል። ከሁለቱ ምስክሮች በህዋላ። የማይሰግድ ሰው ቀሪው ስራው ሁሉ ተመላሽ ነው ። ከዘካውም ፣ ከሐጁም ፣ እንዲሁም ከሌላው (ስራ)። በመሆኑም የሚፆም ነገር ግን የማይሰግድ ከርሱ ተቀባይነት የለውም።
(( በኛና በነርሱ መካከል ያለው ግርዶሽ ሰላት ነው ። (ሰላትን ከመስገድ) የተወ ሰው በርግጥ ክዷል ወይንም አጋርቷል)) [ነቢዩ ሙሐመድ ሰለላሁ ዐለይሒ ወሰለም] »
(ጥያቄው የተለጠፈው በ1335ኛው ሂጅራ በ15 ወርሃ ረመዷን ነው)
ፈትዋውን በድምፅ ለማግኘት ከታች ያለውን አስፈንጣሪ ተጭናቹ ዳውንሎድ በማድረግ ማድመጥ ትችላላቹ ባረከላሁ ፊኩም
https:// phaven-prod.s3.amazonaws.co m/files/audio_part/asset/ 1195246/ 4Zwdm7PdqFR71MidjtXcQreDGtY /Fasts_but_not_Pray.mp3
ማስታወሻ: – ይሄ ፈትዋ የሚመለከታቹ ሰዎች ሆይ! ይሄ ትልቅ ማንቂያ ደወል ነው! በዚህ ረመዳን ለመለወጥ ቆርጣቹ መነሳት ይገባቿል። ከዚች ቅፅበት ወዲ በተውበት ወደ አላህ መመለስ በናንተ ላይ ግዴታ ነው። በቀሪው የረመዷን ቀናት አላህን ምህረት መለመንና በትእዛዙም ላይ እንዲያፀናቹ ጌታቹን መወትወት ይገባቿል። አላህ መሃሪና አዛኝ ነውና። ሌሎቻችን ደግሞ በአቅራቢያችን ተመሳሳይ ሁኔታ ላይ ለወደቁ ሰዎች ወደ አላህ ለመጣራት ከዚህ ወር የበለጠ ምቹ ጊዜ አናገኝምና በርትተን በጥበብ ልንጠራቸው ብሎም ዱዐ ልናደርግላቸው በኛ ላይ የተገባ ነው ። የሚያቀናው የሚያጠመውም እርሱው አንድዬው ጌታችን ነውና።
አላህ ይርዳን

https://