አንድም ተምር ቢሆን?
ጠያቂ:– በሐዲስ እንደመጣው ...
(( من فاطر صائما كان له مثل اجره غير عنه لا ينقص من اجر صائما شيئا ))
ትርጉሙ « አንድን ፆመኛ ሰው ያስፈጠረ ከፅዋሚው ሰው ምንም አጅር (ምንዳ) ሳይቀነስ እኩል ተመሳሳይ ምንዳን (አስፈጣሪው) ያገኛል።»
ፆመኛውን ሰው ለማስፈጠር በተምርና በውሃ ብቻም ቢሆን (ሃዲሱን ለመተግበርና) ምንዳውን ለማግኘት በቂ ነውን?
መልስ ከታላቁ ዐሊም ሸኽ ዑሰይሚን (ረሒመሁላህ) :–
« ዑለማዎች (አላህ ይዘንላቸውና) በዚህ ጉዳይ (በሃሳብ) ተለያይተዋል። ከፊሎቹ አንድን ፆመኛ ሰው ለማስፈጠር ማለት ፆሙን የሚፈታበትን (ብቻ) ያህል በቂ ነው #አንድም ተምር እንኳን ቢሆን ሲሉ ..
ከፊሎቹ ደግሞ ፆመኛን ሰው ማስፈጠር ማለት ሰውየው ሙሉ እስከሚሆን (እስከሚጠግብ) ድረስ ማለት ነው ። ምክንያቱም ሰውየው ለሌሊቱ ክፍለ–ጊዜ የሚጠቅመው ይሄ ነው ። ብሎም ከፍጡር ፍለጋም ነፃ ያደርገዋል (ብለዋል)።
ነገር ግን ከዚህ ሐዲስ በግልፅ እንደምንረዳው አንድ ሰው #በአንዲት ተምር እንኳን ፆመኛን ሰው ቢያስፈጥር የፆመኛውን ምንዳ ያገኛል።
በመሆኑም ሰዎች ፆመኛን ሰው አቅማቸው በሚችለው መልኩ በማስፈጠራቸው ደስተኛ መሆን በነርሱ ላይ የተገባ ነው። ይበልጡኑ ደግሞ በችግር እና በድህነት ላይ ላሉ ሰዎች።
[ مجموع فتاوى ورسائل الشيخ محمد بن صالح العثيمين المجلد العشرون – كتاب الصيام]
ማስታወሻ: – ከላይ በተዘከረው የመልዕክተኛው ሐዲስ ብሎም በሸኹ ፈታዋ ለመተግበር ያልጓጓ ልብ እራሱን ሊጠይቅ ይገባዋል ። ከኪሳችን ከ3 ብር እስከ 5 ብር እንካን መፅውተን ተምር በመግዛት ለመገጝሪብ ወደመስጂድ የሚመጣውን የስንቱን ፆመኛ መአት አጅር መሸመት እንችላለን? በጣም ብዙ!
ከአገር ውጪ ያለንስ ወንድም እና እህቶች አገር ቤት ላለን ሰው ከሃላል ገንዘባችን ቆንጥረን ልከንለት ‘ተምር ገዝተህ ለመሳጂዶች ስጥልኝ’ ብንል የስንቱን ፆመኛ ምንዳ በገፍ እንሰበስብ ይሁን?
ለማንኛውም አላህ ኢኽላስ ይሰጠን ዘንድ ዱዐ አድርገን ወደ ምንዳ ስብሰባ ....!
አላህ ይቀበለን