ሸይኹል አልባኒ (ረሒመሁላህ):-
" ዛሬ ዛሬ ከተሰራጩ ቢድዐዎች መካከል አንድ ሰው (የተሰበሰቡ ሰዎችን) እያንዳንዱን በጨበጠ ቁጥር ሰላም ማለቱ ነው።
'አስሰላሙ ዐለይኩም፣ አስሰላሙ ዐለይኩም፣ አስሰላሙ ዐለይኩም....' ይላል።
ስብስቡ ላይ ሃያ ያህል ሰዎች ቢኖሩ እንኳን ሃያ ያህል ጊዜ ሰላም ይላል። ይህ ቢድዐህ ነው።
ባይሆን ሱናው አንድ ሰው በሰዎች ስብስብ ላይ ቢመጣ ለአንድ ጊዜ ብቻ (ለሁሉም) 'አስሰላሙ ዐለይኩም' ማለቱ ነው።"
[ሲልሲለቱል ሁዳ ወንኑር #181]