Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ሀቅ ሀቋን እናውራ ውሸትን እንተው ግጥም

በወንድማችን አቡ ቢላል አላህ ጀነቱን ይወፍቀው
Abu Bilal
ሀቅ ሀቋን እናውራ ውሸትን እንተው
መቅጠፍም ይቅርብን ሚያዋጣው እውነት ነው
ማነው ተሳዳቢ ሰውን ሚያንቋሽሸው
ሀቅን ማውራት ትቶ የሚደባብሰው
ማነው በታታኙ የአንድነት ፀር
ስላልጣመው ብቻ ሰውን የሚያከፍር
ማነው አይሁድ ብሎ ስም የሚለጥፈው
ሙናፊቅ እያለ ለሰው የሚያወራው
ኧረ እኔስ ገረመ�ኝ ግራም ተጋባሁ
ሁሉ ነገር ዛሬ የተገላቢጦሽ ሲሆን እያየሁ
ሰሀባ ሚሳደብ በመጥፎ ሚያነሳ
እየተሞገሰ ሲታይ እንደ አንበሳ
ኡማውን ጠቅላላ ፈርጆ ሚያከፍር
ሸሂድ ነው እያሉ ሲቸር ሳየው ክብር
በእውነትም ገረመኝ የጊዜው ሁኔታ
ሀቅን ለመደበቅ ሰው እንዲህ ሲያምታታ
ሸሪአን የሚጥስ ዘፈን የሚሰማ
ቅንጣትን አያፍሩ እሱን ሲሉ ኡለማ
አላህን ከፍጡር እያመሳሰለ
በዚህ ንፁህ ዲን ላይ የሱን ፖለቲካ እየቀላቀለ
ከቶ እንዴት ተብሎ ይህ ሊሆን ኡለማ
መውጣትን የሚያልም ወደ ስልጣን ማማ
ሙብተዲን ማያወግዝ ከነሱ ሚወዳጅ
እንዴት ሆኖ ይሆናል ይህ የአንድነት ወዳጅ
ሰዉ ምን ነክቶት ነው ግራ የሚጋባው
እውነትን በውሸት የሚቀላቅለው ።
(አቡ ቢላል)