Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

የእናታችን ዓኢሻ ረዲየላሁ ዐንሃ ክብር !!

የእናታችን ዓኢሻ ረዲየላሁ ዐንሃ ክብር !!

ረሱል ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ዘንድ ተወዳጇ ሚስት ነበረች።

ረሱል ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ያገቧት ብቸኛዋ ልጃገረድ ነች።

ረሱል ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ጋር አብረው ሂጅራ ከተሰደዱ አባትና እናት የተገኘች ብቸኛዋ ባለቤታቸው ናት።

ጌታችን አላህ የእናታችን ዓኢሻን ንፁህነት ለማረጋገጥ በርካታ የቁርአን አያዎችን አውርዶላታል።

ሶሃባዎች ያደናገራቸውን የዲን እውቀት ሁሌም ለማረጋገጥ የሚመጡት ወደ እናታችን ዓኢሻ ነበር።

ጅብሪል ዐለይሂ ሰላም በሐር የተሰራ የእናታችንን ዓኢሻ ምስል ይዞ ወደ ነቢያችን ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም በመምጣት "አግባት፣ የወደፊት ሚስትህ ናት" ብሏቸዋል።

ውዱ ነቢያችን ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ገላቸውን በአንድ ባልዲ አብረዋት የሚታጠቡት ከእናታችን ዓኢሻ ጋር ብቻ ነበር።

ረሱል ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ከአላህ የሆነ ወህይ (ቁርኣን) የሚወርድላቸው ከሚስቶቻቸው ውስጥ ከእናታችን ዓኢሻ ጋር ብቻ ሲሆኑ ነበር።

ሐቢቢና ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ጣረ ሞት ላይ ሆነው ዓኢሻ ዘንድ መሞቱን ፈልገው ነበር። እንደ ፍላጎታቸውም ደረቷን ተደግፈው ሳለ ሩሃቸው ወደ ጌታችን ሄዳለች።

የተቀበሩትም እርሷ ቤት፣ እርሷው ክፍል ነው።
ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም

[ ጀላአልአፍሃም ሊ'ኢብኑል ቀዪም 237-241]

አንድ ጊዜ አንድ ሰው ወደ እናታችን ዓኢሻ ይመጣና "የሆነ ሰው አለ። አንቺን እናታችን አይደለሽም እያለ ነው። ሲላት
ዓኢሻም " እውነቱን ነው። እኔ የምእመናን እናት እንጂ የመናፍቃን እናት አይደለሁም።" ብላ መለሰችለት

ረዲየላሁ ዐንሃ ሊኡሙና ዓኢሻ ኡሙ ዐብደላህ ወኡሙል ሙእሚኒን