Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

የትልቁ ሽርክ አይነቶች



የትልቁ ሽርክ አይነቶች

ትልቁ ሽርክ አራት አይነት ነው፦

1. በልመና ማጋራት፡- ልመና ከታላላቅ የአምልኮ ዘርፎች አንዱ ነው፡፡ እንዲያውም የአምልኮ ዋናው ክፍል ነው፡፡ ነብዩ እንዲህ ይላሉ ‹‹ዱዓዕ የዒባዳ ዋናው ነው›› አላህም እንዲህ ብሏል

وَقَالَ رَبُّكُمُ ادْعُونِي أَسْتَجِبْ لَكُمْ إِنَّ الَّذِينَ يَسْتَكْبِرُونَ عَنْ عِبَادَتِي سَيَدْخُلُونَ جَهَنَّمَ دَاخِرِينَ

‹‹ጌታችሁም አለ «ለምኑኝ፤ እቀበላችኋለሁና፡፡ እነዚያ እኔን ከመግገዛት የሚኮሩት ተዋራጆች ኾነው ገሀነምን በእርግጥ ይገባሉ፡፡›› (አል ጋፊር 6ዐ)

ዱዓእ አምልኮ መሆኑ የተረጋገጠ በመሆኑ ከአላህ ሌላ ለሆነ ፍጡር ማድረጉ ሽርክ ይሆናል፡፡ ስለዚህ ነብይን፣ መልአክን፣ ወልይን፣ ቀብርን፣ ድንጋይንና ማንኛውንም ፍጡር የለመነ አጋሪ ከሃዲ ይሆናል፡፡

አላህ እንዲህ ብሏል፦

وَمَن يَدْعُ مَعَ اللَّهِ إِلَهًا آخَرَ لَا بُرْهَانَ لَهُ بِهِ فَإِنَّمَا حِسَابُهُ عِندَ رَبِّهِ إِنَّهُ لَا يُفْلِحُ الْكَافِرُونَ

‹‹ከአላህም ጋር ሌላን አምላክ ለእርሱ በእርሱ ማስረጃ የሌለውን የሚገዛ ሰው ምርመራው እጌታው ዘንድ ብቻ ነው፡፡ እነሆ ከሓዲዎች አይድኑም፡፡›› (ሙእሙኑን 11)

ዱዓእ አምልኮ ስለመሆኑና ከአላህ ውጭ ለሆነ ማድረግ ሽርክ እንደሚሆን ከማስረጃዎች ውስጥ እንዲህ የሚለው የአላህ ቃል አንዱ ነው፡፡

فَإِذَا رَكِبُوا فِي الْفُلْكِ دَعَوُا اللَّهَ مُخْلِصِينَ لَهُ الدِّينَ فَلَمَّا نَجَّاهُمْ إِلَى الْبَرِّ إِذَا هُمْ يُشْرِكُونَ

‹‹በመርከቦች ውስጥ በተሳፈሩ ጊዜም አላህን መገዛትን ለእርሱ ብቻ ያጠሩ ኾነው ይጠሩታል፡፡ ወደ የብስ (በማውጣት) ባዳናቸው ጊዜም ወዲያውኑ እነርሱ (ጣዖትን) ያጋራሉ፡፡›› (አንከቡት 65)

እነዚህ አጋሪዎች ሲመቻቸው እንደሚያጋሩና ሲቸግራቸውና ሲጠባቸው ግን ዒባዳን ለአላህ ብቻ እንደሚያደርጉ ተናገረ፡፡ ታዲያ ሁሌ በድሎትም በችግርም በአላህ ላይ የሚያጋራ እንዴት ሊሆን ነው? አላህ ይጠብቀን፡፡

2. በፍላጐትና የኒያ ማጋራት፡- ማለት በሚሰራው ስራ ዱንያን ወይም ልክ እንደሙናፊቆች ሙሉ በሙሉ ለይዩልኝና ይስሙልኝ ብቻ መስራትና የአላህን ፊትና የአኺራን ሀገር አለመፈለግ፡፡ ይህ ትልቁ ሽርክ ነው፡፡
አላህ እንዲህ ይላል፦

مَن كَانَ يُرِيدُ الْحَيَاةَ الدُّنْيَا وَزِينَتَهَا نُوَفِّ إِلَيْهِمْ أَعْمَالَهُمْ فِيهَا وَهُمْ فِيهَا لَا يُبْخَسُونَ
أُولَئِكَ الَّذِينَ لَيْسَ لَهُمْ فِي الْآخِرَةِ إِلَّا النَّارُ وَحَبِطَ مَا صَنَعُوا فِيهَا وَبَاطِلٌ مَّا كَانُوا يَعْمَلُونَ

‹‹ቅርቢቱን ሕይወትና ጌጧን የሚሹ የሆኑትን ሰዎች ሥራዎቻቸውን (ምንዳዋን) በእርሷ ውስጥ ወደነሱ እንሞላላቸዋለን፡፡ እነሱም በርሷ ውስጥ ምንም አይጎድልባቸውም፡፡ እነዚያ እነርሱ በመጨረሻይቱ ዓለም ለእነርሱ ከእሳት በቀር የሌላቸው ናቸው፡፡ የሠሩትም ሥራ በርሷ ውስጥ ተበላሸ፡፡ (በቅርቢቱ ዓለም) ይሠሩት የነበሩትም በጎ ሥራ ብልሹ ነው፡፡›› (ሁድ 15-16)
ይህ የሽርክ አይነት ስውር የሆነና አደገኝነቱ የከፋ ነው፡፡

3. በትዕዛዝ ማጋራት፡- አንድ ሰውን አላህ የፈቀደውን ሲከለክልና አላህ የከለከለውን ሲፈቅድ መታዘዝ እንዲሁም ሰዎች ሀላልና ሀራም ማድረግ እንደሚችሉና በዚህ ላይ እነሱን መታዘዝ እንደሚቻል ማመን ማለት ነው::
ይህ ተግባር እስላምናን ሀይማኖት እንደሚጋጭ እያወቀ ይህን የሚያደርግን የሚታዘዝ አዛዡን ሰው የአላህ ቢጤ አድርጓል ማለት ነው፡፡ በመሆኑም ትልቁን ሽርክ ፈፃሚ ነው፡፡
አላህ እንዲህ ይላል፦

اتَّخَذُوا أَحْبَارَهُمْ وَرُهْبَانَهُمْ أَرْبَابًا مِّن دُونِ اللَّهِ وَالْمَسِيحَ ابْنَ مَرْيَمَ وَمَا أُمِرُوا إِلَّا لِيَعْبُدُوا إِلَهًا وَاحِدًا لَّا إِلَهَ إِلَّا هُوَ سُبْحَانَهُ عَمَّا يُشْرِكُونَ

‹‹ከእርሱ በቀር ሌላ አምላክ የሌለውን አንድን አምላክ ሊገዙ እንጂ ያልታዘዙ ሲኾኑ ሊቃውንቶቻቸውንና መነኮሳታቸውን፣ የመርየምን ልጅ አልመሲሕንም ከአላህ ሌላ አማልክት አድርገው ያዙ፡፡ ከሚያጋሩት ሁሉ የጠራ ነው፡፡›› (አል ተውባህ 31)
የዚህ አንቀፅ ትርጓሜ፡- ዑለማዎችንና ባህታዊያንን በኃጢአት መታዘዝ ማለት እንጂ እነርሱን መለመን ማለት እንዳልሆነ ነብዩ አብራርተዋል፡፡ ዓዲይ ኢብኑ ሃቲም ለነቢዩ “እኛኮ ስናመልካቸው አልነበረም” ሲላቸው እንዲህ በማለት እነርሱን ማምለክ ማለት የአላህን ህግ በመቀየር በወንጀል ሲያዙ ትዕዛዛቸውን መቀበል ማለት እንደሆነ ገለፁለት “አላህ ሀላል ያደረገውን ሲከለክሏችሁ እናንተ ትታዛቿቸው አልነበረምን? አላህ እርም ያደረገውን ደግሞ ሲፈቅዱ እነርሱን በመታዘዝ የተፈቀደ ታደርጉ አልነበርን? “እንዴታ” ሲላቸው እነርሱን ማምለክ ማለት ይኸው ነው አሉት፡፡››

4. በውዴታ ማጋራት፡- ማክበር፣ ማላቅ፣መዋረድና መተናነስን የሚያስከትል ለአላህ እንጂ የማይገባን ውዴታ ለፍጡር ማድረግ ትልቁ ሽርክ ነው፡፡
አላህ እንዲህ ይላል፦

وَمِنَ النَّاسِ مَن يَتَّخِذُ مِن دُونِ اللَّهِ أَندَادًا يُحِبُّونَهُمْ كَحُبِّ اللَّهِ وَالَّذِينَ آمَنُوا أَشَدُّ حُبًّا لِّلَّهِ

‹‹ከሰዎችም ከአላህ ሌላ ባለንጣዎችን (ጣዖታትን) አላህን እንደሚወዱ የሚወዷቸው ኾነው የሚይዙ አልሉ፡፡ እነዚያ ያመኑትም አላህን በመውደድ (ከነርሱ) ይበልጥ የበረቱ ናቸው፡፡›› (አል በቀራህ 165)

#እምነትህን_ጠብቅ
የፌስ ቡክ ገፃችንን ለማግኘት
https://m.facebook.com/emnetihintebiq