በሽተኛ
ሰው ውዱእና ትጥበት የሚያከናውንበት የተለየ ሁኔታ አለው። አላህ (ሱብሃነሁ ወተአላ) መልእክተኛው ሙሀመድን
ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም የላካቸው ትክክለኛና ገር በሆነ ሃይማኖት ነው። አላህ (ሱብሃነሁ ወተአላ) እንዲህ ይላል፦
«ْ وَمَا جَعَلَ عَلَيْكُمْ فِى ٱلدِّينِ مِنْ حَرَج»ٍۢ ُۚ
“… በናንተም ላይ በሃይማኖቱ ውስጥ ምንም ችግር አላደረገባችሁም፤…” [አል‐ሐጅ፡ 22 ፥ 78]
«َ ۗ يُرِيدُ ٱللَّهُ بِكُمُ ٱلْيُسْرَ وَلَا يُرِيدُ بِكُمُ ٱلْعُسْرَ »َ
“… አላህ ለናንተ ገሩን (ነገር) ይሻል፤ ለናንተም ችግሩን አይሻም፤… ” [አል‐በቀራ፡ 2 ፥ 185]
«فَٱتَّقُوا۟ ٱللَّهَ مَا ٱسْتَطَعْتُمْ وَٱسْمَعُوا۟ وَأَطِيعُوا۟»َ
“አላህንም የቻላችሁትን የክል ፍሩት፤ ትዕዛዙን ስሙም፤ ታዘዙም፤…”[አል‐ተጋቡን፡ 64 ፥ 16]
ነቢዩም ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም “በእርግጥ ዲን ገር ነው” ብለዋል። [ቡኻሪ] በሌላ ሐዲስ ደግሞ “በአንድ ነገር ካዘዝኳችሁ የምትችሉትን ያክል ፈጽሙ…” ብለዋል። [ቡኻሪና ሙስሊም] ይህንን መሰረታዊ መርህ መሰረት በማድረግ አላህ (ሱብሃነሁ ወተአላ) ዑዝር (ምክንያት) ያላቸውን ሰዎች እንደ ዑዝራቸው ሁኔታ ዒባዳቸውንም አቅልሎላቸዋል። የአላህን ዒባዳ ያለምንም ችግር እንዲፈጽሙት። ምስጋና የዓለማት ጌታ ለሆነው አላህ ይገባው።
እናም የበሽተኛ ሰው ጠሃራ በሚከተሉት ሁኔታ ይፈፀማል፦
⒈ በሽተኛ ሰው በውሃ ጠሃራ ማድረግ ማለትም ውዱእ ማድረግና ከጀናባም መታጠብ ግዴታ ይሆንበታል።
⒉ በውሃ ጠሃራ ማድረግ ካልቻለ (ውዱእና ትጥበትን ካልቻለ) ወይም ውሃ ከነካው በሽታው እንደሚጨምርበት ከፈራ ወይም በሽታው ቶሎ እንዳይድን ያደርጎል ብሎ ከፈራ ተይሙም ያደርጋል።
⒊ የተይሙም አደራረግ በሁለት እጆቹ ንጹሕን መሬት አንድ ጊዜ መንካትና ፊቱን ሙሉ በሙሉ ማበስ ከዚያም እጆቹን አንዱን በሌላው ማበስ።
⒋ በራሱ ማድረግ ካልቻለ ሌላ ሰው ወዱእ ወይም ተይሙም ያስደርጎል። ሌላው ሰው በሁለት እጆቹ ንጹሕ መሬት ነክቶ የበሽተኛውን ፊትና እጅ ያብሳል። በወዱእም እንዲሁ ሌላ ሰው ሊያስደርገው ይችላል።
⒌ በወዱእ አካላቱ ላይ ቁስል ካለበት በውሃ ይጠበው፣ ማጠብ የሚጎዳው ከሆነ እጁን በውሃ አርጥቦ በቁስሉ ላይ በማስኬድ ያብሰው፣ ማበሱም የሚጎዳው ከሆነ ተይሙም ያድርግ።
⒍ በወዱእ አካላቱ ላይ ስብራት ካለና በጨርቅ ወይም በጄሶ ከታሰረ በማጠብ ፋንታ በውሃ ላዩን ያብሳል፣ ተይሙም አያስፈልገውም ማበስ ማጠቡን ይተካልና።
⒎ በግድግዳ ወይም አቧራ ባለው ሌላ ንጹሕ (ጠሃራ በሆነ) ነገር ተይሙም ማድረግ ይችላል። ግድግዳው ከመሬት አካላት ውጭ በሆነ ነገር ለምሳሌ በቀለም ከተቀባ አቧራ ካለው በስተቀር እንጂ ተይሙም ሊደረግበት አይችልም።
⒏ በመሬት ወይም በግድግዳ ወይም አቧራ ባለው ሌላ ነገር ተይሙም ማድረግ ካልተመቸ አፈር በአንድ እቃ ጨምሮ ወይም ጨርቅ ላይ አድርጎ ተይሙም ቢደረግበት ችግር የለውም።
⒐ ለአንድ ሰላት ተይሙም ካደረገና ተይሙም ሳይፈርስበት ቀጣዩ ሰላት ከደረሰ በዚያው በመጀመሪያው ተይሙም ይሰግዳል። ተይሙሙን የሚያበላሽ ነገር ስላልተገኘ ድጋሚ ተይሙም ማድረግ አያስፈልገውም ።
⒑ በሽተኛ ሰው ሰውነቱን ከነጃሳ ማጽዳት አለበት። ካልቻለ ግን ባለበት ሁኔታ ይሰግዳል። ሰላቱ ትክክል ነው። መድገምም አያስፈልገውም።
⒒ በሽተኛ ሰው በንጹሕ ልብስ መስገድ አለበት። ልብሱ በነጃሳ ከተበከለ ማጠቡ ወይም በሌላ ንጹሕ ልብስ መቀየሩ ግዴታ ነው። ካልቻለ ግን ባለበት ሁኔታ ይሰግዳል። ሰላቱ ትክክል ነው። መድገምም አያስፈልገውም።
⒓ በሽተኛ ሰው ንጹሕ በሆነ ነገር ላይ መስገድ ግዴታው ነው። ቦታው በነጃሳ ከተበከለ ማጠብ ወይም በንጹሕ ነገር መቀየር ወይም ንጹሕ ነገር በላዩ ላይ ማንጠፍ ግዴታው ነው። ካልተቻለ ግን በዚያው ላይ ይሰግዳል። ሰላቱ ትክክል ነው። መድገምም አያስፈልገውም።
⒔ በሽተኛው ሰው ጠሃራ (ውዱእ) ማድረግ ባለመቻሉ ምክንያት ሰላትን ማዘግየት አይፈቀድለትም። በተቻለው አቅም ጠሃራ አድርጎ ሰላቱን በወቅቱ መስገድ አለበት። በሰውነቱ ወይም በልብሱ ላይ ማስወገድ ያልቻለው ነጃሳ ቢኖርበት እንኳ።
ጥንቅር፦
[ሸይኽ መሀመድ ኢብኑ ሷሊህ አል‐ዑሰይሚን ረሒመሁላህ]