ዝሙትን ከማስፋፋቱ በላይ ጥንቆላው ባሰ፡፡
ሙስሊሞች ሆይ! እያንዳንዱን ነገር በሸሪዐ ሚዛን ማየት ግድ ይለናል፡፡ ሰሞኑን 8305 በሚል ቁጥር ስልኬ ላይ የሚከተለው ሜሴጅ ደረሰኝ፡፡
‹‹የሚወዱትን ሰው ፍቅር ፕረዘንት ለማወቅ ከፈለጉ የ ፍቅረኛዎ! ወይም ወላጅዎ! ስሙን እና የእርሶን ስም ከዚህ በታች ባለው ምሳሌ መሰረት ወደ 8305 ይላኩ …. በ 3 ኢትዬጵያ ብር፡፡››
አኡዙ ቢላህ፡፡
1) ‹‹የሚወዱትን ሰው ፍቅር ፕረዘንት ለማወቅ ከፈለጉ›› የሚለው አስገራሚ እርኩስ አባባል ነው፡፡ ዘመናዊ አለም ነኝ ብሎ እራሱን የሚጠራው ‹‹ምድርን አበላሽ፣ የሰይጣን ሰራዊቶች›› ፍቅረኛ ብሎ የሚጠራው ከትዳር በፊት ያለውን የፍጡራን ሁሉ ፈጣሪ፣ ብቸኛው አምላክ አላህ እንዳትቀርቡት ያለውን ዝሙት ነው፡፡ ሱብሃነላህ እነሱ ይሀው ወጣቶችን ሊያባልጉ ‹‹የሚወዱትን ሰው ፍቅር ፕረዘንት ለማወቅ ከፈለጉ›› ብለው የማያውቁትን ይናገራሉ፡፡ አላህ ዝሙትን እንዳትቀርቡት ነው ያለን፡፡ ሙስሊሞች ሆይ! እንዲህ አይነት የማያውቁትን የሚናገሩ፣ ያውም የሩቅ ሚስጥርን የሚሞግቱ በመጋረጃ ቢጋረዱም ባይጋረዱም ተጠንቀቋቸው እራቋቸው፡፡
2) ‹‹የ ፍቅረኛዎ! ወይም ወላጅዎ! ስሙን እና የእርሶን ስም ከዚህ በታች ባለው ምሳሌ መሰረት ወደ 8305 ይላኩ አልማዝ#አበበ››፡፡
አሁንም አኡዙቢላህ፡፡
በመጋረጃ ተጋርደው የሚንቀሳቀሱ ጠንቋዬች ነበሩ የእናት የምናምን ስም እያሉ የሚጠይቁት፡፡ ዛሬ ይሀው በስልክ ኤስ ኤም ኤስ በ3 ብር ጥንቆላ ቀረበ ለህዝቡ፡፡ ሙስሊሞች ሆይ! ይህን እርኩስ ተግባር ራቁት፡፡
ሌላው ስንት አልማዝና አበበ አሉ የተለያየ ፍላጎት፣ የተለያየ አስተያየት ያላቸው፡፡ የሰው ልጅ በተለይ ወጣቶች በብዛት አንድን ነገር እንሞክረው ይላሉ ግን ምን ያህል ከኢስላም አኳያ ያለውን አደጋ ያውቁ ዘንድ የነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ሀዲስ እንካችሁ፡፡
‹‹የነገን አውቃለሁ ባይ (የጠመጠመም ይሁን ያልጠመጠመ ጠንቋይ፣ ከመጋረጃ በስተጀርባም ይሁን አይሁን፣ ኮከብ ቆጣሪም ይሁን፣ የሲኒ አተላ አንባቢ ወይንም እንዲህ እንደ 8305 የማያውቀውን የሚናገር) ጋር የሄደ ሰው የ40 ለሌት ሰላቱ ውድቅ ነው››፣
‹‹ካመነበት በሙሐመድ ላይ በተወረደው ክዷል›› ይላሉ ውዱ ነብይ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም)
3) ‹‹በ 3 ኢትዬጵያ ብር፡፡›› ሙስሊሞች ሆይ! 3 ብር ፍፁም የአላህን ፊት ብቻ በመፈለግ ለምስኪን ከተሰጠ ነፍስን ከዘሳማሚዋ እሳት ለማስጠበቅ ሰበብ ሊሆን ይችላል፡፡ ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ከእሳትን ግማሽ ተምርም በመመፅወትም ቢሆን ነፍሳችንን እንድናድን ነግረውናል፡፡
4) ሰሞኑን ደግሞ እንዲህ ሲል ሴቶችን በጅምላ ጭፍጨፋ ይፈፅምባቸዋል፡፡
‹‹10ቱ የዘመኑ ሴቶች ዉሸቶች ለማወቅ ከፈለጉ C ፊደልን ወደ 8305 ይላኩ››
Generalization ሁሉን በአንድ መፈረጅ የመሃይማን መገለጫ ነው፡፡ ስንትና ስንት መልካም ሴቶች በዘመናችን አሁንም አሉ፡፡ ምንም እንኳን መጥፎዎቹ ከመልካሞቹ በቁጥር ቢበልጡም ‹‹10ቱ የዘመኑ ሴቶች ዉሸቶች ለማወቅ ከፈለጉ C ፊደልን ወደ 8305 ይላኩ›› ተብሎ በፍፁም አይፃፍም፡፡ እንዲህ በጅማላ እየፈረጁ ኪስን ማደለብ ነውር ነው፡፡
ለማንያውም ሙስሊሞች ሆይ! ማንኛውንም ነገር ጌምም ይሁን ሌላ ኢስላም ምን ይላል የሚለውን መጀመርያ መጠየቅ ይበጃል፡፡ አለበለዚያ እንዲህ አኸይራ የሚያጠፉ ነገሮች ውስጥ መሳተፉ በሁለት አገር አደጋው ከባድ ነው፡፡
አላህ ሆይ! ውዱ ባርያህ ኢብራሂም አለይሂ ወሰለም ‹‹እኔንም ልጆቼንም ጣኦትን ከማምለክ ጠብቀን›› ብሎ እንደለመነህ እኔም እለምንሀላሁ፡፡ የአላህ ሰላትና ሰላም በነብያት ሁሉ መደምደሚያ፣ በቤተሰቦቻቸው፣ በባልደረባዎቻቸውና ሃቅን በተከተለ ላይ ሁሉ ይሁን፡፡