ብዥታን ማስተካከያ
ማን ነው የእውነት የሙስሊሞች ጉዳይ የሚያስጨንቀው???
በአላህ ስም እጅግ በጣም አዛኝ በጣም ሩህሩህ፡፡ የአላህ ሰላት እና ሰላም በነብያችን፤ በቤተሰቦቻቸው፤ በሰሃባዎቸ እና ፈለጋቸውን በተከተለ ላይ ሁሉ ይሁን፡፡
የአላህ መልክተኛ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል ‹‹ዘመን ይመጣል ሰዎች የሚጭበረበሩበት፤ እውነተኛው ውሸተኛ፤ ውሸታሙ እውነተኛ የሚባልበት….›› ብለዋል፡፡
አላሁ (ሱብሃነሁ ወተዓላ) የነብያት መደምደሚያ የሆኑትን ሙሀመድ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለምን) ለአለማት እዝነት አድርጎ ልኳል፤ ከዚህም አልፎ አላህ ስለሳቸው እንዲህ ይላል ‹‹ነብዩ ለአማኞች ከነፍሳቸው በላይ ነው››፡፡ ለፍጡራኑ ከአላህ በላይ አዛኝ የለም፤ ከሱ በመቀጠል ነብያችን (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ለአማኞች ከነፍሳቸው በላይ፤ ለኡመቱ መመራት ደግሞ በጣም ይጨነቁ እና ያስቡ ነበር፡፡
ይህ ጭንቀታቸው ደግሞ በተግባር የተገለፀ ነበር፡፡ የሰው ልጅ በዚህም አለም ይሁን በሚቀጥለው አሳማሚ ቅጣት እንዳያጋጥመው አላህን በብቸኝነት እንዲያመልክ፤ የሳቸውን ሱና እንዲከተል አጥብቀው ያዙ ነበር፡፡ ከነብያት ቀጥሎ የነብያት ወራሾች የሆኑት ኡለማዎች እና የነሱ ተማሪዎች ይህንን የነብያት ፈለግ በመከተል፤ ለሙስሊሙም ይሁን ለኡማው በማሰብ የአላህን አጀንዳ ወደ ፊት በማስቀደም፤ ጥሪያቸውን ከተውሂድ እና ሱና ይጀምራሉ፡፡
ነገር ግን አዛኝ ቂቤ አንጓች እንደሚሉት የዘመናችን የቢድዓ አራማጆች ነብያት ሁሉ የተላኩበትን፤ የተፈጠርንበትን አላማ ተውሂድ ትተው ሌላ አጀንዳ ውስጥ ገብተዋል፡፡ በጣም የሚገርመው እራሳቸውን የሙስሊሞች ጉዳይ ከእኛ በላይ የሚያሳስበው የለም እያሉ፤ ሁለት አገር ለእሳት ኑሮ የሚዳርገውን ‹‹ሽርክ፤ እና ቢድዓ›› ሲሰራ እያዩ ዝም ይላሉ፡፡
አህለል ኪታቦችም ‹‹እኛ የአላህ ልጆች እና ተወዳጆቹ ነን›› ብለው ነበር፡፡ ነገር ግን ይህ ሙገታቸው ውድቅ ነው፡፡ አላህ ልጅ የለውም፤ የአላህን ውዴታ ለማግኘት ነብዩን (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) መከተል ግድ ነው፡፡ ለምሳሌ በዘመናችን እነዚህ ቢድዓ ተከታዬች የነብያትን ተልኮ ስለሚተገብሩ ሰዎች የሚከተለውን ይላሉ
የቢድዓ አራማጆች ዘንድ
1) አንድ ሰው ተውሂድ ካስተማረ እና ሽርክን ካወገዘ ‹‹የኡማው ጉዳይ አያሳስበውም››
2) ስለ ሱና ያወራ እና ቢድኣን እና ባለቤቶቿን ያወገዘ ሰው ‹‹በታታኝ ነው››
3) ስለ ሰሃባ ታላቅነት ካወራ እና ሰሃባን ከሚሳደቡ ሰዎች ኡማውን ካስጠነቀቀ ‹‹ሀሜተኛ፤ የሙስሊሞች ስጋ የሚበላ››
4) ጌዜያችንን እንጠቀም ፊልም፤ መንዙማ ሽርኪያት፤ ኳስ እንራቅ ካለ ‹‹ሂክማ እና አኽላቅ የሌለው››
5) ሴት ልጅ አለባበሷን ትጠብቅ፤ ፎቶዋን ከፊስቡክ ላይ ሴትም ይሁን ወንድ ያውርድ ካለ ‹‹ጠባብ እና አክራሪ››
እና የመሳሰለውን ይሉታል
እንዚህ ሰዎች ዘንድ ቀብር አይመለክ፤ ቢድዓ አይሰራ፤ ለሰሃባ ክብር ይሰጥ ካልክ አለቀልህ ‹‹አንተ የኢስላም ጣላት፤ የሙስሊሞች ጉዳይ የማያሳስብህ ነህ›› ይሉሃል፤ ሊያሸማቅቁህ፤ አትስማቸው፡፡ ለምሳሌ ታላላቅ ሰሃባዎች የሚሰደቡበት ኪታብ አገራችን ላይ ይበተናል ያለው፤ የሰው ስም አታንሱ ሲሉ፤ የሰሃባዎች ስም ይጣፍጣልን??? የሙስሊሞች ስጋ አትብላ ይሉሃል፤ ሰሃባዎችስ ስጋቸው ጣፍጧችሁ ነው?????????
የሙስሊሞች ጉዳይ የእውነት የሚያሳስበው ሰው ዱንያ አኸይራቸው የሚስተካከልበትን ተውሂድ፤ ሱና፤ ሰሃባ፤ ጌዜን በአግባቡ መጠቀም እና ሸሪዓ ያዘዘባቸው ጉዳዩች ሁሉ ያሳስባቸዋል፤ እንደ ቅደም ተከተሉ፡፡
አላህ ከአህለል ቢድዓ ተንኮል እና ያሸበረቀ ማታለያ ቃል ይጠብቀን፡፡
አላህ ሆይ! ሀቅን አሳየን የምንከተለውም አድርገን፤ ባጢልንም አሳየን የምንርቀውም አድርገን፡፡