Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

“የእናንተ ዳዕዋ ሰዎችን ይከፋፍላል!”

“የእናንተ ዳዕዋ ሰዎችን ይከፋፍላል!”
ሸይኽ ሙሐመድ ናስሩዲን አል አልባኒ (ረሒመሁላህ):-
‹‹ እንስማማለን! የእኛ ዳዕዋ የሐቅ ጥሪ ነው። (በመሆኑም) በሐቅና በሐሰት መካከል ይለያያል። ትክክል የሆነውን እና ትክክል ያልሆነውን (ይለያያል።) ለዚያም ነው ከነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ስሞች መካከል አንዱ “አልሙፈሪቅ” (ከፋፋይ፣ የሚለያይ) መሆኑ የማያስገርመው። እነዚህ ኢስላማዊ ዱዐቶች (ተጣሪዎች) አላዋቂ የሆኑበት አንድ ነገር አለ። እሱም እነዚህ ተጣሪዎች ይህን (አልሙፈሪቅ (ከፋፋይ፣ የሚለያይ)) የሚለውን (የነቢያችን ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ስም ቢሰሙ ግራ ይጋባሉ። ይህም የሆነው ኢስላምን ስላልተረዱ ነው። የነቢያቶች፣ የመልእክተኞች እና የመለኮታዊ መፃህፍት ዋና ዓላማ ሐቁን ከሐሰቱ መለየት ነው። ለዚያም ሙስሊሞች ከሐቅ ጋር (እና) የሐሰት (ደግሞ) ተቃራኒ ናቸው። ››
[ሲልሲለቱል ሁዳ ወንኑር (280)]