Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

የውዱእ መስፈርቶች! ውዱእ ትክክለኛ እንዲሆን የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይኖርበታል፡-

የውዱእ መስፈርቶች!
ውዱእ ትክክለኛ እንዲሆን የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይኖርበታል፡-
1. ሙስሊም፦
አእምሮ ጤናማ የሆነና ጥሩና መጥፎ የሚለይ ካፊርና እብድ ሰላታቸው ትክክለኛ ያልሆነ ሲሆን ህፃን ከመለያ እድሜው በፊት ቢሰግድም ሰላቱ አይቆጠርም፡፡
2. ኒያ (በልብ ማሰብ)፦
ለዚህ ማሰረጃ የሚከተለው ሀዲስ ነው
“ስራዎች ትክክል የሚሆኑት በኒያ ነው”
(ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል)
ኒያን በምላስ መናገር ግን ከነብዩ መመሪያ የሌለ ነው፡፡
3. ንፁህና የሚያፀዳ ውሃን መጠቀም፦
በነጃሳ ውሃ ውዱእ ማድረግ አይቻልም፡፡
4. ውሃ ወደ አካል እንዳይደርስ የሚያግዱ ነገሮችን ማስወገድ፡፡
ለምሳሌ ሻማ፣ ሊጥ፣ የጥፍር ቀለምና የመሳሰሉት::
5. አስፈላጊ ከሆነ ኢስቲንጃእ ወይም ኢስቲጅማር ማድረግ::
6. ማከታተል::
7. ቅደም ተከተሉን መጠበቅ።
8. ማጠብ ግዴታ የሚሆኑ አካሎችን ሁሉ ማጠብ፡፡
በውዱዕ ጊዜ የግድ መታጠብ ያለባቸው አካሎች ስድስት ናቸው፦
1. ፊትን ሙሉ በሙሉ ማጠብ፡፡ አላህ እንዲህ ብሏል፡-
‹‹ወደ ሶላት በቆማችሁ (ለመቆም ባሰባችሁ) ጊዜ ፊቶቻችሁን…(እጠቡ)፡፡››
(አል ማኢዳህ 6)
መጉመጥመጥና በአፍንጫ መሳብ ከፊት ማጠብ ጋር የሚካተቱ ናቸው፡፡
2. እጆችን ከነክርኖች ማጠብ፡፡ አላህ እንዲህ ብሏል፡-
‹‹እጆቻችሁንም እስከ ክርኖች እጠቡ፡፡››
(አል ማኢዳህ 6)
3. ሙሉ ራስን ከጆሮ ጋር አብሮ ማበስ፡፡
አላህ እንዲህ ብሏል፡-
‹‹ራሶቻችሁንም (በውሃ) አብሱ፡፡››
(አል ማኢዳህ 6)
ነብዩም (ﷺ) “ጆሮ ከራስ የሚካተት ነው” ብለዋል ከፊል ራስን አብሶ ከፊሉን መተው በቂ አይደለም፡፡
4. እግሮችን እስከ ቁርጭምጭሚቶች ድረስ ማጠብ፡፡ አላህ እንዲህ ብሏል፡-
‹‹እግሮቻችሁንም እስከ ቁርጭምጭሚቶች (እጠቡ)››
(አል ማኢዳህ 6)
5. ቅደም ተከተሉን መጠበቅ፦
ምክንያቱም አላህ በቅደም ተከተል ስለገለፃቸውና ነብዩም (ﷺ) አላህ በገለፀው መልኩ በቋሚነት ስለተገበሩ፡፡ ቅደም ተከተሉ አብደላህ ኢብኑ ዘይድ ከነብዩ (ﷺ) ባስተላለፉት ሀዲስ መሰረት
“ፊት ከዚያ እጆች ቀጥሎ ራስ እና በመጨረሻም እግሮች ናቸው፡፡
6. ማከታተል፦ ማለትም አንዱን አካል አጥቦ ሳይዘገይ ወደ ሌላው አካል ማለፍ፡፡
ለዚህ ማሰረጃው ነብዩ (ﷺ) ውዱእ ሲያደርጉ በማከታተል ነበር፡፡
ኻሊድ ኢብኑ ሚዕዳን ባስተላለፉትም ሀዲስ፦
«ነብዩ (ﷺ) አንድ ሰው እየሰገደ ሳለ እግሩ ላይ ውሃ ያልደረሰው ዲርሐም የሚያህል ቦታ ደርቆ አዩትና ውዱኡን በድጋሚ እንዲያደርግ አዘዙት፡፡»
(አህመድና አቡዳውድ ዘግበውታል)
ይህ ሀዲስ ውዱእን በማከታተል ማድረግ ግዴታ እንደሆነ ይጠቁማል፡፡ ምክንያቱም ግዴታ ባይሆን ኖሮ ውሃ ያልደረሰውን እንዲያጥብ እንጂ በድጋሚ እንዲያደርግ አያዙትም ነበር፡፡
‪#‎ፊቅህን_ለመረዳት‬
የፌስ ቡክ ገፃችንን ለማግኘት…
www.facebook.com/easyfiqh
ሼር ማድረግ እንዳይረሱ!