Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ከቀብር ጋር የተያያዙ ክልክል ተግባራት!

ከቀብር ጋር የተያያዙ ክልክል ተግባራት!

2ኛ. ቀብር ዘንድ ማረድ

ይህ የሚደረገው ጉዳይን እንዲያሳኩ በማሰብ ለቀብሮች ለመቃረብ ከሆነ ይህ ትልቁ ሽርክ ነው፡፡ ከዚህ ውጭ ለሆነ ዓላማ ከሆነ ደግሞ አደገኛ የሆነና ለሽርክ የሚዳርግ ቢድዓ ነው፡፡

ነብዩ (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) ኢስላም ውስጥ “አቅር” የለም ብለዋል፡፡ አብድረዛቅ እንዳሉት

“በጃሂሊያ ዘመን ቀብር ዘንድ ከብትና በግ ያርዱ ነበር”

3ኛ. ከወጣው አፈር ውጭ በመጨመር ከፍ ማድረግ

4ኛ. ጄሶ መለሰን

5ኛ. ቀብር ላዩ ላይ መፃፍ

6ኛ. ከላዩ መገንባት

7ኛ. ቀብር ላይ መቀመጥ

እነዚህ ሁሉ ለአይሁዶችና ክርስቲያኖች መጥመም ምክንያት የሆኑ ቢድዓዎችና ከፍተኛ የሽርክ መዘዞች ናቸው፡፡

ጃቢር እንዲህ ብለዋል ፦

‹‹የአላህ መልዕክተኛ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም ቀብርን በጄሶ መመረግ፣ ላዩ ላይ መቀመጥ፣ ከላዩ መገንባት፣ ከአፈሩ ውጭ መጨመርና ቀብር ላይ መፃፍ ከልክለዋል፡፡››

8ኛ. ቀብር ዘንድ መስገድ

አቡ ሙርሢድ አልገነዊይ እንዳሉት የአላህ መልዕክተኛ (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) እንዲህ ሲሉ ሰምቻለው

‹‹ወደ ቀብር አትስገዱ ላዩም አትቀመጡ››

አቡ ሰዒድ አልኹድሪይ እንዳስተላለፉት የአላህ መልዕክተኛ (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል

‹‹መሬት ሁሉም መሰገጃ ነው ቀብርና ገላ መታጠቢያ ሲቀር ፡፡”

9ኛ. ቀብር ላይ መስጂድ መገንባት

ይህ አይሁድንና ክርስቲያናትን ያጠመመ ቢድዓ ነው፡፡ ከላይ እንዳሳለፍነው ከዓኢሻ የሚከተለው ሀዲስ ተስተላልፏል

‹‹አይሁዶችና ክርስቲያኖች የነቢያታቸውን ቀብር መስጂድ በማድረጋቸው አላህ ከእዝነቱ አባረሯቸው፡፡››

1ዐኛ. ቀብርን የበዓል ስፍራ ማድረግ

ይህ ቢድዓ አደጋው የከፋ በመሆኑ ግልፅ በሆነ መልኩ ተከልክሏል፡፡

ከአቡ ሑረይራ እንደተላለፈው የአላህ መልዕክተኛ (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል

‹‹ቀብሬን የበዓል ስፍራ እንዳታደርጉ፡፡ ቤታችሁንም መቃብር አታድርጉ፣የትም ቦታ ብትሆኑ ሰላትን አውርዱብኝ ሰላታችሁ የትም ብትሆኑ ይደርሰኛል፡፡››

11ኛ. ጓዝ ጠቅልሎ ቀብርን ለመጐብኘት መጓዝ

ይህም ወደ ሽርክ የሚያደርስ መንገድ በመሆኑ ተከልክሏል፡፡
በአቡ ሑረይራ እንደተላለፈው ነብዩ (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል

‹‹ወደ ሶስት መስጂዶች እንጂ ጓዝን ጠቅልሎ ለመጐብኘት መጓዝ አይፈቀድም መስጂደል ሀራም፣ የመልዕክተኛው (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) መስጂድና የአልአቅሳ መስጂድ፡፡

‪#‎እምነትህን_ጠብቅ‬

የፌስ ቡክ ገፃችንን ለማግኘት
https://m.facebook.com/emnetihintebiq