Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ዉዱእ ትርጉሙና ሸሪዓዊ ድንጋጌው

ዉዱእ

ትርጉሙና ሸሪዓዊ ድንጋጌው

ውዱእ የተሰኘው የዓረብኛ ቃል ቋንቋዊ ትርጉሙ ማማርና መፅዳት ማለት ነው፡፡

ሸሪዓዊ ትርጉሙ፡-

ውሃን አራት አካሎች (አራት አካሎች ፊት፣ እጆች፣ ራስና እግሮች) ላይ ሸሪዓው በወሰነው መልኩና አላሀን ለማምለክ ታስቦ መጠቀም ነው፡፡

ሸሪዓዊ ድንጋጌው፡-

ሰላትንና መሰል ውድእ የሚያስፈልጋቸውን እንደጠዋፍ፣ ቁርአንን መንካትና የመሳሰሉትን ለመፈፀም በፈለገና ውዱእ በሌለው ሰው ላይ ግዴታ ነው፡፡

ዉዱእ ዋጂብ (ግዴታ) የሚሆነው መቼ ነው?

ግዴታ ለመሆኑ ማስረጃው የሚከተለው የአላህ ቃል ነው፡-

‹‹እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ወደ ሶላት በቆማችሁ (ለመቆም ባሰባችሁ) ጊዜ ፊቶቻችሁን፣ እጆቻችሁንም እስከ ክርኖች እጠቡ፡፡ ራሶቻችሁንም (በውሃ) አብሱ፡፡ እግሮቻችሁንም እስከ ቁርጭምጭሚቶች (እጠቡ)፡፡ (ሴት ጋር በመገናኘት ወይም በሌላ ምክንያት «ጀናባ») ብትኾኑ (ገላችሁን) ታጠቡ፡፡ በሽተኞች ወይም በጉዞ ላይ ብትኾኑም ወይም ከእናንተ አንዳችሁ ከዓይነ ምድር ቢመጣ ወይም ሴቶችን ብትነካኩና ውሃን ባታገኙ ንጹሕን የምድር ገጽ አስቡ ፡፡ ከሱም ፊቶቻችሁንና እጆቻችሁን አብሱ፡፡ አላህ በእናንተ ላይ ምንም ችግር ሊያደርግ አይሻም፡፡ ግን ታመሰግኑ ዘንድ ሊያጠራችሁና ጸጋውን በእናንተ ላይ ሊሞላ ይሻል፡፡››
(አል ማኢዳህ 6)

ነብዩ (ﷺ) እንዲህ ብለዋል

“አላህ ያለ ውዱእ ሰላትን አይቀበልም፣ ከተሰረቀ ዕቃም ምፅዋትን አይቀበልም”

(ሙስሊም ዘግበውታል)

በሌላም ሀዲስ እንዲህ ብለዋል

“አላህ ውዱእ የሌለውን ውዱእ እስካላደረገ ሰላቱን አይቀበለውም”

(ሙስሊም ዘግበውታል)

ከሙስሊሞች ውስጥ ይህንን የተቃወመ አንድም ሰው አይታወቅም፡፡ ስለዚህ የውዱእ ግዴታነት በቁርአን በሀዲስና በኡለማዎች ስምምነት (ኢጅማዕ) የፀደቀ ነው፡፡

ግዴታ የሚሆነው መች ነው?
ለሚለው ደግሞ፡-

የሰላት ወቅት ሲደረስ ወይም ደግሞ ውዱእ መስፈርት የሆነበትን ነገር ለምሳሌ ጠዋፍ ለማድረግና ቁርአንን ለመንካት የመሳሰሉትን ስራ መስራት ሲፈልግ ነው፡፡

ግዴታ የሚሆንበት ሰው ደግሞ ሙስሊም የሆነ፣ አካለ መጠን የደረሰና አእምሮው ጤነኛ የሆነ ሰው ላይ ነው፡፡

‪#‎ፊቅህን_ለመረዳት‬
የፌስ ቡክ ገፃችንን ለማግኘት…
www.facebook.com/easyfiqh
ሼር ማድረግ እንዳይረሱ!