Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ሙታንንና ቀብሮችን ማምለክ



ሙታንንና ቀብሮችን ማምለክ

ሙታን ለራሱም ምንም ማድረግ የማይችል በመሆኑ ቀብሩ ዘንድ ሄዶም ይሁን በሩቁ አንዳችን ነገር እንዲያሳካ መለመን መከጀል ወይም ጉዳት ያደርስብኛል ብሎ መስጋት በአላህ ላይ ማጋራት (ሽርክ) ነው፡፡
ነብዩ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም ቀብርን ለማምለክ ከሚዳርጉ ነገሮች ሁሉ ከሩቁ አስጠንቅቀዋል፡፡ ቀብር ላይ ከመስገድ ወይም መስጂድ ከመገንባት እንዲህ በማለት ከልክለዋል፦
“ከናንተ በፊት የነበሩ ህዝቦች የነብያቸውን ቀብር መስገጃ አድርገዋል እናንተም ቀብሮችን መስገጃ እንዳታደርጉ አጥብቄ እከለክላለሁ”

አይሁዶች እና ክርስቲያኖችን የነቢያትን ቀብር መስገጃ ስፍራ በማድረጋቸው እንዲህ በማለት ረግመዋል፦
“አይሁዶች እና ክርስቲያኖች አላህ ከእዝነቱ ያርቃቸው፤ እነሱ የነቢያቸውን ቀብር መስጂድ አድርገዋል”

የእሳቸው ቀብር እንዳይመለክ አላህን እንዲህ በማለት ለምነዋል፡-
“ጌታዬ ሆይ! ቀብሬን የሚመለክ ጣዖት እንዳታደርግብኝ”

እነዚህና ሌሎችም ነቢያዊ ትምህርቶች ቀብር ላይ ድንበር እንዳይታለፍና እንዳይመለክ ከሩቁ የሚያስጠነቀቁ ናቸው፡፡ ነብዩ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም እንኳን ቀብር ሊመለክ ይቅርና ቀብር ዘንድም ለአላህ እንዲሰገድ አልፈቀዱም፦
“ወደ ቀብር አትስገዱ ላዩም አትቀመጡ"

#እምነትህን_ጠብቅ

የፌስ ቡክ ገፃችንን ለማግኘት
https://m.facebook.com/emnetihintebiq