Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

የላኢላሃ ኢለላህ ትሩፋት!

የላኢላሃ ኢለላህ ትሩፋት!
ከኡትባን በተወራ ሀዲስ የአላህ መልዕክተኛ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል፦
«አላህ የእርሱን ፊት ፈልጎ ላ አላሃ አለላህ¹
ባለ ሰው ላይ (የጀሀነም) እሳትን እርም አድርጓል»

[አል ቡኻሪይ (425) ፣ ሙስሊም (33)፣ ኢብኑ ማጃህ (7054) ፣ ነሳኢይ (1114) ዘግበውታል]
~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~
¹ የላኢላሃ ኢለላህ ትርጉም
«አንድ ሰው ሙስሊም የሚሆንበት ቃል ላኢላሃኢለላህ በመሆኑ ትርጉሙን በሚገባ ማወቅና ተቃራኒውንም መጠንቀቅ የግድ ነው፡፡
ትርጉሙን ለመረዳት
1ኛ إله " “ኢላህ” የሚለውን የአረብኛ ቃል በደንብ ማጤን ያስፈልጋል "معبود" إله " (መዕቡድ) የሚለውን የአረብኛ ቃል የሚተካ ሲሆን (معبود) ደግሞ የሚመለክ፣ (ተመላኪ) ማለት ነው፡፡
በመሆኑም ይህንን ቃል ፈጣሪ፣ መጋቢ፣ ሰጪ ፣ነሺ በሚለውና በመሣሰሉት ትርጉም መረዳት የላኢላሃ ኢለላህን ትርጉም ከማሣጣቱም በላይ ብዙ ሙስሊምች የገዛ ቃላቸውን ትርጉም እንዳይረዱና ሽርክ ላይ እንዲዘፈቁ ምክንያት ይሆናል፡፡
2ኛ ላኢላሃ ኢለላህ ሁለት ክፍሎች እንዳሉት ማወቅ ነው፡፡
1ኛ “ላኢላሃ” لاإله نفي(አፍራሽ)
2-"ኢለላህ "إلاالله اثبات (አረጋጋጭ)
ይህ ማለት አምልኮ የተባለን ባጠቃላይ ከሁሉም አራቁቶ ለአላህ ብቻ ማድረግ ማለት ነው፡፡

[በ አቡ ሀማድ]