ፆመኛ ሊጠነቀቃቸው የሚገቡ ከፊል ነገሮች
① ሀሜት፣የውሸት ምስክር፣ነገረኝነት እና ማንኛውንም አልባልታ ወሬዎች
ፆመኛ የሆነ ሰው እነዚህን ሊጠነቀቅ ይገባዋል እነዚህን ነገሮች ካልተጠነቀቀ እየተራበ እና እየተጠማ ያለው በከንቱ ነው ማለት ነው ።
የአላህ መልእክተኛ ሶለላሁ አለይሂ ወሰለም እንዲህ በለዋል
"የሀሰት ምስክርን እና በእሱ መስራትን ያልተወ ሰው ምግብ እና ፆም በመተዎ ለአላህ ጉዳይ የለውም" [ቡኻሪ 6057]

② ውዱ በሚያደርግ ግዜ በአፍንጫው ውሃ ሲያስገባ(እስቲንሻቅ ሲያደርግ) በደንብ አለመሳብ
የአላህ መልእክተኛ ሶለላሁ አለይሂ ወሰለም "ፀመኛ የሆንክ ግዜ ሲቀር በአፍንጫህ በደንብ ውሀን ሳብ" ብለዋል [ሱነን አቢ ዳውድ 2366]
ከዚህ ሀዲስ እንደምንረዳው ውሀን የውዱ ግዜ በአፍንጫ በደንብ ወደ ውስጥ በመሳብ ማስገባት ሱና ነው ግን የፆም ግዜ ክልክል ነው ምክያቱም በደንብ ውሃውን ከሳብን ወደ ጉሮሯችን መግባቱ ስለማይቀር ነው በፆም ግዜ የተከለከለው።

③ አብዛሀኛውን ወይን ብዙውን የቀን ክፍል መተኛት ለፆመኛ ጥሩ አይደለም ምክኒያቱም ውድ የሆነውን ግዜ ያለምንም ኢባዳ እንዲያልፍ ያደርግበታል (እንቅልፍም ኢባዳ አይደል ላላችሁኝ አዎ ግን መባል የያዘው ሁሉም በልክ ይሁን ነው)
ጠቢቡ ኢብኑ ኡሰይሚን (ረሂመሁላህ) እንዲህ ይላሉ:-
"ለፆመኛ በሶላት፣አላህን በማውሳት(በዚክር)፣በዱአና ቁራእን በመቅራት (ግዜውን ሊያሳልፍ) ይገባዋል። ሰው በፆመ ግዜ ነፍሱን በተለያየ ኢባዳ ካላመዳት ይህ ለሱ ይገራለትል። (ግን በተቃራኒው ነፍሱን)
በስንፍና እና ረፍት(እንቅልፍ) በማብዛት
ከሆነስ ያላመዳት እሄንኑ ስንፍናውን እንጅ ሌላን አይለምድም (ሁኔታው እንዲህ ከሆነች) የፆመ ግዜ በእርሱ ላይ መልካም ስራ እና ኢባዳዎች ይከብዱበታል" [መጅሙኡል ፈታዋ ወረሳኢል 19/171]

④ በራሱ ላይ ስሜቱን የማይተማመን ሰው ሚስቱን መሳም ይህም በፆም ሰአት ሊጠነቀቁት የሚገባ አደጋ ነው።
ኢብኑ አብዲል በር (ረሂመሁላህ)
"ሚስቱን ከመሳም የተነሳ ፆም የሚያበላሽ ነገር የሚመጣበት ለሆነ ሰው መሳምን(ይፈቀዳል) ያለ (አሊም) አንድንም አላውቅ" ይላሉ [አት-ተምሂድ 5/114]
ስለዚህ በራሱ ላይ ስሜቱን የማይተማመን ሰው ከንደዚህ አይነት ድርጊት እራሱን ሊቆጥብ ይገባዋል

አላህ ፆማቸውን ከተቀበላቸው ያድርገን
0 Comments