‹‹መደድ ወይንም መደዴ›› ማለት ምን ማለት ነው???
ብዙ መንዙማ ባዩች ነብዩን (ﷺ) ‹‹መደድ እና መደዴ›› ብለው ይጠራሉ፡፡ መደድ ማለት ትርጉሙ ‹‹እርዳታ እርዳታ›› ማለት ነው፡፡
ከአላህ ውጭ ያለን እርዳታ መጠየቅ ደግሞ ሽርክ ነው፡፡ ነብዩንም (ﷺ) ይሁን ጂብሪልን፤ ኢሳን፤ ሚካኤልን፤
መርየምን፤ አለይን፤ አብድልቃድር ጀይላኔን፤ ሰይፉ ጨንገሪንም…… የመሳሰሉትን እርዳታ በሰላምም በጭንቀትም፤
የሚጠየቀው የፍጡራን ጉዳይ ሁሉ ብቻውን የሚያስተናብረው አላህ ነው፡፡ አላህ ሆይ! እውቀትን በተለይ የተውሂድ እና
ሱናን እውቀት ጨምርልን፡፡ አላሁመ አሚን፡፡