ኢኽዋኖች ሆይ!!
እኛንም እናንተንም አላህ ይምራንና
① እውነት ለሸይኽ ፈውዛን ክብሩ ካላችሁ ሸይኹ ደጋግመው ኢኽዋንን ይተቻሉና እዚህስ ለምን አትቀበሏቸውም? ለምንስ ኢኽዋን ላይ የሚሰነዝሩትንም ትችት አታሰራጩላቸውም?
② ፈውዛን ሌላው ቀርቶ ዐብደላህ አልሙጥለቅንም "ኢኽዋኒ ነው " ነው ይላሉ። እንዳውም "ሌላ የምትጠይቁት አጣችሁ?" በማለት ለፈትዋ እምነት የሚጣልበት እንዳልሆነም ይጠቁማሉ። ይሄንንስ ለምን አታሰራጩላቸውም?
③ በዚያ ላይ ሸይኽ ፈውዛን ቀርቶ ኢኽዋኒው ዐብደላህ አልሙጥለቅ እራሱ እናንተ የምታብጠለጥሉትን የሳዑዲ መንግስት በእጅጉ ያወድሳል? ትቀበሉታላችሁን? መረጃን መሰረት አድርጋችሁስ ነው ንግግሮቹን የምትጥሉትና የምታነሱት?
እባካችሁን ነገሮችን ከስሜት ነፃ ሆናችሁ ተመልከቱ።
የሸይኽ ፈውዛንን በሙጥለቅ ላይ የተናገሩትን ከስር ታገኙታላችሁ።
የሸይኽ ፈውዛንን በሙጥለቅ ላይ የተናገሩትን ከስር ታገኙታላችሁ።