የተወሰኑ ኢስላማዊ ስርዓቶች የቤት አገባብና አወጣጥ ስርዓት
1. የቤቱን ሰው ማስፈቀድ
አንድ ሰው ከቤቱ ውጭ የሌላ ሰው ቤት ከመግባቱ በፊት ማስፈቀድ ግዴታው ሲሆን ቤቱ ሲገባም ቢያስፈቅድ መልካም ነው፡፡ አላህ እንዲህ ይላል፡-
يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا لَا تَدْخُلُوا بُيُوتًا غَيْرَ بُيُوتِكُمْ حَتَّى تَسْتَأْنِسُوا وَتُسَلِّمُوا عَلَى أَهْلِهَا ذَلِكُمْ خَيْرٌ لَكُمْ لَعَلَّكُمْ تَذَكَّرُونَ
فَإِنْ لَمْ تَجِدُوا فِيهَا أَحَدًا فَلَا تَدْخُلُوهَا حَتَّى يُؤْذَنَ لَكُمْ وَإِنْ قِيلَ لَكُمُ ارْجِعُوا فَارْجِعُوا هُوَ أَزْكَى لَكُمْ وَاللَّهُ بِمَا تَعْمَلُونَ عَلِيمٌ
‹‹እናንተ ያመናችሁ ሆይ! እስከምታስፈቅዱና በባለቤቶቿ ላይ ሰላምታን እስከምታቀርቡ ድረስ ከቤቶቻችሁ ሌላ የኾኑን ቤቶች አትግቡ፡፡ ይህ ለእናንተ መልካም ነው፡፡ እናንተ ትገነዘቡ ዘንድ (በዚህ ታዘዛችሁ)፡፡ በውስጧም አንድንም ሰው ባታገኙ ለእናንተ እስከሚፈቀድላችሁ ድረስ አትግቧት፡፡ ለእናንተ ተመለሱ ብትባሉም ተመለሱ፡፡ እርሱ ለእናንተ የተሻለ ነው፡፡ አላህም የምትሠሩትን ሁሉ ዐዋቂ ነው፡፡›› (አል ኑር 27-28)
የኢብኑ መስዑድ ባልተቤት ዘይነብ እንዳሉት “ኢብኑ መስዑድ ጉዳያቸውን ጨርሰው ወደቤት ሲመጡ በሚጠሉት ሁኔታ ላይ ድንገት በቅ እንዳይሉ ሲሉ ወደበር ሲቀርቡ ድምፃቸውን ያሰሙ ነበር፡፡”
2. ሰላም ማለት
ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) አንድን ሰውዬ በአግባቡ ባለማስፈቀዱ ምክንያት ለአገልጋያቸው እንዲህ ብለዋታል “በአግባቡ አላስፈቀደምና አሰላሙ አለይኩም ልግባ? እንዲል ንገሪው”
3. ሲገባ የሚከተለውን ዚክር ማለት
« بسم الله ولجنا , وبسم الله خرجنا , وعلى الله ربنا توكلنا »
“ቢስሚላሂ ወለጅና ወቢስሚላሂ ኸረጅና ወዓላ ረቢና ተወከልና”
ትርጉሙም፡ (በአላህ ስም ገባን በአላህ ስም ወጣን በጌታችን አላህ ተመካል)
4. ጥርስን መፋቅ
ዓኢሻ እንዳስተላለፉት “ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ቤት ሲገቡ አስቀድመው ጥርሳቸውን ይፍቁ ነበር፡፡”
5. ቀኝ እግርን ማስቀደም
ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) በሁሉም መልካም ነገራት ቀኝን ማስቀደም ይወዱ ነበር፡፡
6. ሲወጣ ይህን ዚክር ማለት
« بسم الله , توكلت على الله , ولا حول ولا قوة إلا بالله »
“ቢስሚላሂ ተወከልቱ አለላሂ ወላ ሃውላ ወላ ቁወተ ኢላ ቢላህ”
ትርጉሙም፡ (በአላህ ስም፣ በአላህ እመካለሁ፣ ብልሀትም ሆነ ሃይል ያለ አላህ የለም፡፡)