Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ማሳሰቢያ ፦ ይህ ድርጊት ሰላትህ ሊያበላሽ ይችላል እና ተጠንቀቅ


ማሳሰቢያ ፦
ይህ ድርጊት ሰላትህ ሊያበላሽ ይችላል እና ተጠንቀቅ��
��አንዳንድ ከኢማም ተከትለው የሚሰግዱ ሰዎች ኢማሙ ሁለተኛውን ተስሊማ ሳያሰላምት ያመለጣቸው ረከዓን ለመሙላት ሲሉ ብድግ ይላሉ።
��ይህ ስህተት ነው
የአላህ መልክተኛ (ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ ይላሉ፦
"እኔ ኢማማቹህ ነኝ፣በሩኩዕም ሆነ በስጁድ እንዲሁም ብድግ በማለት ፣ በማሰላመትም አትቅደሙኝ።"
��【ሙስሊም ዘግበውታል】
ታላቁ የዘኘናችን ሸይኽ ኢብኑ ባዝ(ረሂመሁላህ) እንዲህ ይላሉ፦
"ኢማሙ ሁለተኛውን ተስሊማ ሳያሰላምት ያመለጠውን ቀዳ ለማውጣት የተነሳ በእረግጠኝነት ስህተት ሰርታል።
ምክንያቱም ትክክለኛው ተግባር ኢማሙ ሁለተኛውን ተስሊማ ካሰላመተ በኋላ ነው መነሳት ያለበት።"��
ኢማሙ ሁለተኛውን ተስሊማ ሳያሰላምት የተነሳ የሰላትን ግዴታ ትቷል፣ይኸውም፦ ኢማሙ ሁለተኛውን ተስሊማ እስኪያሰላምት ቁጭ ማለት ነበረበት፣ ከኺላፍ ለመውጣት ሲል እና ለዲኑ ጥርጣሬ የሌለውን ተግባር ከመስራት አኳያ ይህኛውን ሰላት መድገም ይኖርበታል፣ምክንያቱም ኢማሙ ሰላቱ ሳያጠናቀቅ ቆሟልና፣ከኢማሙ ጋር ከጅማሪው ሰላት ያለጀመረ በረከዓ ወይንም ረከዓዎች የተቀደመ ከኢማሙ በፊት ማሰላመት የለበትም።"
【ኑሩን ዓላ ደርብ ፤12/368