ሁሉም ነገር ስርኣት አለው
ሃዘን ሲደርስብን ወዳጅ ዘመድ ሲሞትብን ምን ይውጣ ካንደበታችን
∙ ⇝❓⇜
ሞት እያንዳንዳችን ላይ የተደነገገች፣ የማትቀርልን ናት። ይኸም ጥርጥር የሌለውና በየተራ ቤታችንን እያንኳኳ ያለ ነገር ነው።
ሞትንም ይሁን እኛን የፈጠረን ፈጣሪ አምላካችን አላህ እንዲህ ይለናል።
” …كُلُّ نَفْسٍ ذَائِقَةُ الْمَوْتِ ۗ “
آل عمران:185
«ነፍስ ሁሉ ሞትን ቀማሽ ናት፡፡»
ኣሊኢምራን:185
ምናልባ ማዘግየትና ማፍጠን ይቻል እንደሆን ብለን እንዳናስብም ከሰኣቷ ወደፊትም ወደኋላም ፈቀቅ የማትልልን አይቀሬ እድላችንም መሆኗን ነገረን በተግባርም እየታየች ናት።
” ۗ لِكُلِّ أُمَّةٍ أَجَلٌ ۚ إِذَا جَاءَ أَجَلُهُمْ فَلَا يَسْتَأْخِرُونَ سَاعَةً ۖ وَلَا يَسْتَقْدِمُونَ “
يونس﴿٤٩﴾
« … ለሕዝቦች ሁሉ የተወሰነ ጊዜ አልላቸው፡፡ ጊዜያቸው በመጣ ወቅት አንዲትን ሰዓት አይቆዩም፤ አይቀደሙምም» በላቸው፡፡
ዩኑስ:(49)
ይህንን አይቀሬ የዚህች ዓለም መሰናበቻ ድልድይ የምናስተናግድበት ሁኔታ ግን የብዙዎቻችን ከኢስላም ስርኣት ያፈነገጠና መሰረተ ቢስ በሆነ ተለምዶ ነው።
ለመሆኑ መልእክተኛው صلى الله عليه وسلم ምን ነበር ያስተማሩት ❓
وعن أم سلمة رضي الله عنها قالت
سمعت رسول الله صلى الله عليه وسلم يقول
ما من عبد تصيبه مصيبة، فيقول إنا لله وإنا إليه راجعون: اللهم أجرني في مصيبتي، واخلف لي خيرا منها، إلا آجره الله تعالى في مصيبته واخلف له خيرا منها.
رواه مسلم
ከኡሙሰለማህ ረዲየላሁ ዐንሃ ከአላህ መልእክተኛ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም ሰምታ በነገረችን ሀዲስ እንዲህ ብላለች:
« ማንኛውም የአላህ ባርያ የሆነ አደጋ ደርሶበት " ኢና ሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂዑን " እኛም የአላህ ነን ወደሱም ተመላሾች ነን። አምላኬ ሆይ በደረሰብኝ አደጋ መልካም ምንዳ ስጠኝ። ካጣሁት የተሻለም ተካልኝ። ያለ እንደሆን :~ በደረሰበት አደጋ ሰበብ አጅር ሳይሰጠውና ካጣው ነገር የተሻለም ሳይተካለት አላህ አይተወውም።» ብለዋል ብላለች።
{ ኢንና ሊላሂ ወኢንና ኢለይሂ ራጂዑን}
{ አላሁመ አጂርኒ ፊ ሙሲበቲ
ወኽሉፍሊ ኸይረን ሚንሃ }
ኡሙ ሰለማ ታሪኩን ስታስረዳን ውዱ ባለቤቷ አቡሰለማ (ረዲየላሁ ዐንሁም አጅመዒን) ሲሞባትና በጣም ተሰምቷት በሃዘን ተውጣ አግኝተዋት
“ ይህንን ቃል እንድል የአላህ መልእክተኛ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም አዘዙኝና አልኩት። አላህም ከአቡ ሰለማ የተሻለውን የአላህን መልእክተኛ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም ተካልኝ። ” ብላለች።
ሀዘንተኛን ለማፅናናት ሲሆን ደግሞ በየሀዘን ቦታው የሚደረገው የተሳሳተ ተለምዶን በተመለከተ የሸይኽ ሷሊህ አልፈውዛንን ምክር እነሆ👉
ሃዘንተኛን ለማፅናናት ቁርኣንን
ስለ መቅራት
••••••••••••••••
ታላቁ ሊቅና ፈቂህ ሸይኽ
ሷሊህ ፈውዛን አልፈውዛን
አላህ ይጠብቃቸውና
ስለዚህ ጉዳይ የቀረበላቸውን ጥያቄና የሰጡትን ምላሽ እናካፍላችሁ።
ጥያቄ:
በአገራችን ተሰራጭቶ እንደሚገኘው ሀዘንተኛን ለማፅናናት በሚል ሰዎች ተሰባስበው እጃቸውን ከፍ በማድረግ ፋቲሐን ይቀራሉና ይህ ነገር በሸሪዓ ይፈቀዳልን❓
↪ ምላሽ:–
🔹ይህ ነገር ታዕዚያ (ሰውን ማፅናናት) ሳይሆን በዲን ላይ የተጨመረ አዲስ ፈጠራ ቢደዐ ነው።
🔹ታዕዚያ ወይም ማፅናናት ማለት ሀዘን ለደረሰበት ሰው:–
👉አላህ ፅናትህን የተሻለ ያድርግልህ፣
👉ያጋጠመህንም ጉዳት አላህ ይጠግንልህ፣
👉ሟችህንም አላህ ይማርልህ።
ሲባል ነው ማፅናናት የሚባለው።
➡ቁርአንን መቅራት ወይም ፋቲሃን ወይም ከቁርአን የሆነን ክፍል ለማፅናናት (ለታእዚያ) ብሎ መቅራትን በተመለከተ ምንም አይነት ማስረጃ አልመጣም።
➡ በቀብር ስነ ስርኣት ወቅት እንዲሁም ቀብር ላይም ሆነ ቀብር ዘንድ ሆኖ ቁርአን መቅራትን በሚመለከት ምንም ማስረጃ ባለመምጣቱ ይህ ነገር በሙሉ ቢድዓ ነው።
📓 قـراءة القـرآن في العـزاء .
• لـ فضيلة الشيخ العلامة الفقيه /
صالح بن فوزان بن عبد الله الفوزان
- حفظه الله ورعاه -
`````````````````````````
🔊 لسمــاع المقطــع الصوتــي :
http://
◇◇◇
📝 23 ጁማደል አወል 1436
Abufewzan 14March15