Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ሩቃ

ሩቃ

ትርጉሙ፦

“ሩቃ” ሩቅያ ለተሰኘው የዓረብኛ ነጠላ ቃል ብዜት ሲሆን ሩቅያ ማለት በሽተኛን ለመፈወስ የሚነበነቡ ከቁርአንም ይሁን ከሀዲስ ጥቅሶች ማለት ነው፡፡

ሸሪዓዊ ብይኑ፦

የተፈቀደ ነው፡፡ ከማስረጃዎች ውስጥ ዓውፍ ኢብኑ ማሊክ እንዳሉት ፦

«በድንቁርና ዘመን በሽተኛ ላይ እናነብ ነበርና የአላህ መልዕክተኛ ሆይ ﷺ ! እንዴት ያዩታል? ብለን ጠየቅናቸው፡፡ እሳቸውም ምታነቡትን ግለፁልኝ፤ ማጋራት የሌለበት እስከሆነ ድረስ በሽተኛ ላይ ማንበብ ችግር የለውም አሉ»

[ሙስሊም ዘግበውታል]

አነስ ኢብኑ ማሊክ እንዲህ ብለዋል

«የአላህ መልዕክተኛ ﷺ ለቡዳ በሽታ፣ ለመነደፍና ቁስለት ሩቃ ማድረግ ፈቅደዋል»

[ሙስሊም ዘግበውታል]

ጃቢር ኢብኑ ዐበደላህ እንዳስተላለፉት የአላህ መልዕክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል ፦

«ወንድሙን (ከህመሙ ለመፈወስ በመቅራት) መጥቀም የቻለ ያድርግ››

[ሙስሊም ዘግበውታል]

ከአዒሻ እንደተዘገበው የአላህ መልዕክተኛ ﷺ ከኛ ውሰጥ አንዱ ሲታመም በቀኝ እጃቸው እየዳበሱት እንዲህ ይሉ ነበር፦

«የሰዎች ጌታ ሆይ! ጉዳትን አስወግድ፤ፈውሰው አንተ ፈዋሸ ነህ ከአንተ ሌላ ፈዋሽ የለም ህመምን በማያስቀር ፈውስ ፈውሰው»

[ ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል ]

‪#‎ሺፋእ‬
ቁርዓናዊ ፈውስ ለጂን እና ሲህር !
ፔጁን ላይክ ለማድረግ፡-
https://www.facebook.com/nosihr
ሼር በማድረግ ሙስሊሙን ዑማ በብዛት እየጎዳ ያለውን የሲህር በሽታ
ለመከላከል የበኩሎን አስተዋፅዖ ያበርክቱ!