Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

የሩቃ መስፈርቶች!

የሩቃ መስፈርቶች!

ሩቃ የሚፈቀደው ሶስት መስፈርቶች ሲሟሉ ነው:: እነሱም፡-

አንደኛ፡-

ከአላህ ፈቃድ ውጭ ያድናል በሚል ሊታመን አይገባም፡፡ ከአላህ ፈቃድ ውጭ እንደሚጠቅም ማመን ሽርክ በመሆኑ የተከለከለ ነው፡፡

ሁለተኛ፡-

ሸሪዓን የሚጋጭ መሆን የለበትም፡፡ ለምሳሌ፦ ከአላህ ሌላ መለመን ወይም ከጭንቅ እንዲገላግል ጋኔንን መጥራት የመሳሰሉት ከታከሉበት ሽርክ በመሆኑ ክልክል ይሆናል፡፡

ሶስተኛ፡-

ግልፅ የሆነ ትርጉም ያለው መሆን አለበት፡፡ ትርጉም የሌለው አተታ ከሆነ አይፈቀድም፡፡

ኢማም ማሊክ እንዲህ በሚል ተጠየቁ የታመመ ሰው ላይ መቅራት ይቻላልን? እሳቸውም እንዲህ በማለት መለሱ፦
«በመልካም ቃላቶች ከሆነ ችግር የለውም፡፡»

ክልክል የሆነ ሩቅያ፡-

ከላይ የተጠቀሱ መሰፈርቶች ያልተሟሉበት ሩቅያ በመሉ ክልክል ነው::

ለምሳሌ፦ አንባቢው ወይም የሚነበብለት ሰው ሩቅያ ራሱን ችሎ ፈውስ ነው በሚል የሚያምን ከሆነ ወይም ሩቅያው የሽርክ የቢድዓ የመሳሰሉ ቃላቶችን ያቀፈ ከሆነ ወይም ደግሞ ትርጉም በሌለው አተታ ከሆነ አይፈቀድም፡፡
________
‪#‎ሺፋእ‬

ቁርዓናዊ ፈውስ ለጂን እና ሲህር !
ፔጁን ላይክ ለማድረግ፡-

https://www.facebook.com/nosihr
ሼር በማድረግ ሙስሊሙን ዑማ በብዛት እየጎዳ ያለውን የሲህር በሽታ ለመከላከል የበኩሎን አስተዋፅዖ ያበርክቱ!