Ibnu Munewor
ጌታዬ!
እኔ በየትኛውም መልኩ ማንኛውንም የበደለኝን ሙስሊም አንተን በማሰብ፣ እዝነትህን በመሻት፣ ይቅርታህን በማስቀደም ይቅር ብያለሁ።
ጌታዬ ክልከላዎችህን ሌት ከቀን የምዳፈረው እኔ በደለኛው፣ ህግጋትህን ዘወትር የምዘነጋው እኔ ውለታቢሱ ደካማ ባሪያህ፣ በፀጋህ እየተጣቀምኩ፣ በችሮታህ እየኖርኩም ምህረትህን፣ ይቅርታህን እከጅላለሁ። በጥፋት ተጨማልቄ ይቅርታህን እየከጀልኩ እንዴት ከባሪያዎችህ ይቅር ለማለት አቅማማለሁ?!
ጌታዬ እኔ እወድሃለሁ ብየ እሞግታለሁ። ግና ጩኸቴ ባዶ ሙግት እንዳይሆን እሰጋለሁ። ጌታዬ በፍርዱ ቀን አታሳፍረኝ።
ጌታዬ እኔ ነብይህን ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እወዳለሁ ብዬ እሞግታለሁ። ነገ ላያቸውም እናፍቃለሁ እላለሁ። ጌታዬ ምኞቴን ከንቱ አታርግብኝ።
ጌታዬ ሆይ "እኔ ከባሪያዬ እሳቤ ዘንድ ነኝ" ማለትህን ሰምቻለሁ። ከነስጋቴ ካንተ መልካምን አስቤያለሁ። መልካም ተስፋንም ሰንቄያለሁ። ነገ እንዳታሳፍረኝ እማፀንሀለሁ።
ጌታዬ አንተን ለመገዛት ብትፈጥረኝም ከፈጠርክብኝ አላማ በፈጠርክልኝ መጣቀሚያ ተዘናግቻለሁ። አይኖቼ፣ እጆቼ፣ እግሬቼ፣ ጆሮዎቼ፣ ምላሴ፣ ··· መላ አካላቴ አንተን ከመገዛት ይልቅ አንተን በማመፅ ዝለዋል። ይህ ሁሉ ሆኖም ከእዝነትህ፣ ከምህረትህ ተስፋ አልቆጥኩም። እንደ ነብይህ እንደ ሹዐይብ "ጌታዬ መሀሪና ወዳጅ ነው" እላለሁ። ወንጀሌ በሀፍረት ጠፍሮ ሳይዘኝ እንድትምረኝም፣ እንድትወደኝም እከጅላለሁ።
ጌታዬ ሆይ! ከደጋጎች ባልደርስም ደጋጎችን እናፍቃለሁ። ነገ በአኺራ እነ አቡበክር፣ እነ ዑመር ጋር ልሆን እከጅላለሁ። ጌታዬ ከምትወዳቸው ባሮችህ ከምወዳቸው ሰለፎቼ አታርቀኝ።
ጌታዬ ሆይ! ልቤ በወንጀል ደርቋልና አርጥብልኝ። ከተቅዋ ልብስ ተራቁቻለሁና አልብሰኝ። ስንቄ እንደቀለለ ወደ አኺራ አትውሰደኝ።
ጌታዬ ሆይ መጨረሻየን አሳምርልኝ። ሸሂድነትን አጎናፅፈኝ። አሚን።