በቅድሚያ…
መጪው ረመዳን ነው። በረመዳን ወር ውስጥ ደግሞ ሁሉቱንም ፆታዎች ባሳተፈ መልኩ ከሚፈፀሙ የአምልኮ ስርአቶች ውስጥ የተራዊህ፣ የታጁድ (የቂያመ ለይል)ሰላት ተጠቃሽ ነው። እናም በዛሬ መልእክታችን ከመስጂድ ይልቅ በቤት ኢባዳ መፈፀም የሚበልጥላትን «ሙስሊም እህት» ወደ መስጂድ ልምጣ ካለች ካለመከልከሉ ጋር ወደ መስጂድ ስትመጣ ሕግና ስርአቶች አሉ። ይህን ታሳቢነት በማድረግ በቅርቡ በወንድም ሙሐመድ አሊ ዳውድ ወደ አማርኛ ከተተረጎመው የሸይኽ ሷሊህ አልፈውዛን "ተንቢሀት" ኪታብ ይህን ህግና ደንብ ከሚያብራራው ክፍል በዚህ መልኩ አቅርበናል።
ሴት ልጅ ወደ መስጂድ ለሶላት በወጣች ጊዜ የሚከተሉትን ስርአቶች መጠበቅ ግድ ይላታል፦
ሀ/ በልብስ እና ሙሉ በሆነ ሂጃብ የተሸፈነች መሆን አለባት። ዓኢሻ (ረዲየላሁ አንሃ) እንዲህ ትላለች፦
«كان النساء يصلين مع رسول ﷲ صلى الله عليه وسلم ثم ينصرفن متلفعات بمروطهن ما يعرفن من الغلس»
“ሴቶች ከአላህ መልእክተኛ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ጋር ይሰግዱ ነበር። በቀሚሳቸው የተሸፋፈኑ ሆነው ሲመለሱ ጨለማ የቀላቀለበት ንጋት ስለሆነ ማንም አያውቃቸውም ነበር።” [ቡኻሪና ሙስሊም]
ለ/ ሽቶ ያልተቀባች ሆኖ መውጣት ነው።
ለዚህም ነቢዩ ነቢዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) እንዲህ ይላሉ፦
«لا تمنعوا إماءﷲ مساجدﷲ، وليخرجن تفلات»
“የአላህን ሴት ባሮች የአላህን መስጅድ አትከልክሏቸው፤ ሽቶ ያልተቀቡ ሆነው ይውጡ።”[አቡዳውድና አህመድ]
ከአቡ ሁረይራ (ረዲየላሁ አንሁ)በተወራው ሐዲስ የአላህ መልእክተኛ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) እንዲህ አሉ፦
«أيما امرأة أصابت بخورا فلا تشهدن معنا العشاء الآخرة»
“ማንኛውም ሽቶ የነካች ሴት እኛ ጋር የመጨረሻ የሆነችውን የዒሻ ሰላትን እንዳይሳተፍ።”[ሙስሊም አቡዳውድና ነሳኢ]
ሙስሊም ከኢብኑ መስዑድ ባለቤት ከዘይነብ (ረዲየላሁ አንሀ) አንስቶ እንደዘገበው የአላህ መልእክተኛ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) እንዲህ አሉ፦
«إذا شهدت إحداكن المسجد فلا تمس طيبا»
“ከመካከላችሁ መስጅድ የምትሳተፍ ሴት ሽቶን እንዳትነካ።”ብለዋል።[ቡኻሪና ሙስሊም]
ኢማሙ አሽውካኒ “ነይሉል አውጧር” በሚባለው ኪታባቸው 3ኛው ጥራዝ ገፅ 140‐141 ላይ እንዲህ ይላሉ፦ “በሐዲሱ ውስጥ ያለው መረጃ እንደሚያመላክተው የሴት ልጅ ወደ መስጂድ መውጣት የሚፈቀደው መውጣቷ በውስጡ ፈተና ከሌለው እና እንደ ሽቶ የመሰሉ ፊትና ቀስቃሽ የሆኑ ነገሮች ያልተጠቀመች ከሆነ ነው። አክለውም ሸይኹ ከሐዲሱ እንደተገኘው ወንዶች ለሴቶች ወደ መስጂድ መሄድን ሲፈቅዱላቸው መውጣታቸው ወደ ፈተና ጥሪ የሚያደርጉ እንደ ሽቶ፣ ጌጣጌጥ ወይም ማንኛውም ውበትን የሚያመጣ ነገር አብሮ የማይኖር ከሆነ ነው።”
ሐ/ በጌጣጌጥ እና በልብስ የተዋበች ሆና መውጣት የለባትም!
የሙእሚኖች እናት የሆኑት ዓኢሻ (ረዲየላሁ አንሃ) እንዲህ ትላለች፦
«لو أن رسولﷲ صلىﷲ عليه وسلم رأى من النساء ما رأينا لمنعهن من المسجد كما منعت بنو إسراءيل نساءها»
“የአላህ መልእክተኛ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለ) አሁን እኛ የምናየውን ከሴቶች ቢያዩ ኖሮ የእስራኤል ልጆች ሴቶቻቸውን እንደከለከሉት ከመስጅድ ይከለክሏቸው ነበር።”[ቡኻሪና ሙስሊም]
ኢማሙ አሽውካኒ ነይሉል አውጣር በሚባለው ኪታባቸው ላይ “እኛ ያየነውን ቢያዩ ኖሮ” የሚለውን የዓኢሻን ንግግር ያለፈውን አይነት ተመሳሳይ ትንታኔ ሠጥተዋል። ማለትም የልብሳቸውን ውበት፣ የሚቀቡትን ሽቶ፣ የሚያደርጉትን መዋዋብ እና መገላለጣቸውን ቢያዩ ኑሮ ከመስጂድ ይከለክሏቸው ነበር። ሴቶች ይወጡ የነበረው በቀሚሳቸው፣ በጋቢያቸው እና ወፍራም በሆነ መጠቃለያቸው ነበር።
ኢማሙ ኢብኑል ጀውዚይ ረሂመሁላህ “አህካሙ አብ‐ኒሳእ” በሚባለው ኪታባቸው ገፅ 39 ላይ እንዲህ ይላሉ፦ “በተቻላት መጠን ሴት ልጅ ከመውጣት መቆጠብ አለባት። ምክንያቱም እርሷ ሰላም ብትሆን ሰዎች ከርሷ ሰላም አይሆኑም። ለመውጣት ከተገደደች መውጣት ያለባት፦ በባሏ ፍቃድ፣ ያልተዋበች ሆና፣ የመንገዱን አውራ ጎዳና እና የገበያ ቦታ ሳይሆን ገለልተኛውን ቦታ መንገድ በማድረግ፣ ድምጿ እንዳይሰማ ጥንቃቄ በማድረግ፣ የመንገዱን መካከል ሳይሆን ዳሩን ይዛ በመጎዝ መሆን አለበት።”
ኡሙ ሰለማ (ረዲየላሁ አንሃ) በአስተላለፈችው ሐዲስ እንዲህ ትላለች፦ ነቢዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) “አሰላምተው ሲጨርሱ እቦታቸው ላይ ትንሽ ይቆያሉ”
ዙህሪይ እንዲህ ይላሉ፦ ትክክለኛውን አዋቂው አላህ ነው “ይህን እኛ የምናየው (የሚመስለን) ከሴቶች የሚመለሱት እንዲወጡ ነው።”
«ሸርህ አልከቢር አለል መቅኒዕ ይመልከቱ»
ኢማሙ አሽውካኒ “ነይሉል አውጣር” በተሰኘው ኪታባቸው ላይ 2ኛው ጥራዝ ገፅ 326 ላይ፦ መሪ የሆነ ሰው የሚመራቸውን ሰዎች ባህሪ መጠበቅ ይወደድለታል፣ ክልክል ወደ ሆኑ ነገሮች ላይ የሚያደርሱ ነገሮች መጠንቀቅ፣ ጥርጣሬ ያለበትን ቦታ መጠበቅ እና የመሳሰሉት ናቸው።
ሌላው አይደለም እቤት በመንገድ ላይ እንኳን ወንዶች ከሴቶች ጋር መቀላቀል እንደማይፈቀድላቸው ከሐዲሱ የምንማረው ነው
ኢማሙ አንነዋዊይ ረሂመሁላህ አል‐መጅሙዐ በሚባል ኪታባቸው 3ኛው ጥራዝ ገፅ 455 ላይ እንዲህ ይላሉ፦
ሴቶች ወንዶችን በጀመአ ሰላት ላይ በተወሰኑ ነገሮች ይለያሉ፦
አንደኛ፦ በእነሱ ላይ እንደ ወንዶች የጠነከረች (ግዴታ) አይደለችም።
ሁለተኛ፦ የምታሰግደው ሴት በሰጋጆቹ ሴቶች መካከላቸው ትቆማለች ።
ሶስተኛ፦ ከወንድ በአንፃሩ አንድ ሴት ከሆነች ከወንድ ጎን ሳይሆን ከኋላው ትቆማለች።
አራተኛ፦ ከወንድ ጋር የሚሰግዱ ከሆነ በላጩ ሶፍ መጀመሪያው ሳይሆን መጨረሻው ነው።
ካለፉት ነጥቦች ላይ በተጨማሪ የምናገኘው እውቀት የወንድና የሴት መቀላቀል ሐራም መሆኑን እናውቃለን።
[ተንቢሀት ከተሰኘው የሙሀመድ አሊ ዳውድ ትርጉም መፅሀፍ ከገፅ 69‐73 የተወሰደ]