Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

የመግቢያ ዋጋ 50.00 ብር ይላል የአምባሳደሩ ቲያትር ቤት የሚመረቀው በዲን ስም የሚዘፈነው ነሺዳ።

Sadat Kemal Abu Nuh

የመግቢያ ዋጋ 50.00 ብር ይላል የአምባሳደሩ ቲያትር ቤት የሚመረቀው በዲን ስም የሚዘፈነው ነሺዳ። እንዲህ ነው እንጂ በዲን ስም መነገድ።
በ50.00 ብር ወንጀል ከመግዛት ከ 50.00 ብር ባነሰ 30 ጁዝ ቁርአን ገዝታችሁ ለመስጂድ ዘውታሪ ሰደቃ ነዩ።
እነዚህ ሰዎች ነበሩ በረመዳኑ "ኑ በአፍሪካ ሲኒማ ጥበብን ጉዷን ስናፈላው ተመልከቱ" ሲሉ የነበሩት።
የአላህ ባርያዎች ሆይ! "ቁርአን ተቃጠለ" እየተባለ በፌስ ቡክ የመፈክር መአት ይፃፍ የለ ወይ?
ታድያ ነሺዳስ ግብአቱ ሰዎች ወደ ቁርአን ፊታቸውን እንዳያዞሩ ማድረግ አይደለ ወይ?
ስንት ህፃናትን ትመለከታለህ የተፈጠሩለትን አላማ ፋቲሃን ማንበብ አይችሉም። ነገር ግን "ፊዳከ፣ የታሉ፣ ሀቢቢ" እያሉ በሽርክ የተጨማለቁትንም የሚያዜሙ።
ይህ አይደለም ወይ ታድያ በዲን ስም መነገድ? በዲን ስም ዲንን ማውደም?
የነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ሱና ተቃርኖ
1) ፂሙን "ኦ (O)" እየተቆረጠ፣
2) ፂሙን እየላጨ፣
3) ሱሪውን መሬት እየጎተተ፣
4) ፀጉሩን አንዱን አንዱ አበላልጦ እየተቆረጠ
5) ሲኪኒ (ቃርያ ሱሪ) እየለበሰ

አያፍርም "ፊዳከ አቢ ወኡሚ" ይላል። አባትና እናቱን ፊዳ ከማለቱ በፊት ለነብዩ ሱና ነፍሱን ቀድሞ ፊዳ አያደርግምን?
አላህ የማይሰሩትን ከመናገር ይጠብቀን።