Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

አይ ቢድዓ‬!


Haider Khedir 
April 10, 2014  

‪#‎አይ_ቢድዓ‬!!!
አንዲት ቢድአ ስትወለድ "ምን ችግር አላት" የሚል ርእስ ይጻፍባታል፣ ቀጥሎም እድሜዋ ለአቅመ "ሙስተሀብ" ይደርስና በስተመጨረሻም "ግዴታ" ወይንም
እሷን ከተቃወምክ "ልታከፍርህ" የምትችል ትሆናለች::
እንዴት ማለት ጥሩ ... በደንብ እንዲገለጽልህ ምሳሌን ላስከትል...
የኢስቲዋእን ጉዳይ ብቻ ብትመለከት እነኳ መልእክተኛው (ሠለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) አላህ ከአርሽ በላይ ነው ብላ የመለሰችውን "‪#‎ሙእሚን‬ ናት" አሉ፥ ከጊዜ ሂደት በኋላ ጉዳዩ "‪#‎ኺላፍ_አለበት‬"
በሚል አረፍተነገር ተለወሰ፥ በስተመጨረሻም ሙሉ ቀለሙን ቀይሮ "#ሙእሚን ናት" የሚለው የመልእክተኛው (ሠለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ብይን "‪#‎ካፊር_ናት‬" በሚል ተፈጸመ::

ወዳጄ ሆይ! ታዲያ እንዲገባን ጭንቅላታችን ላይ ትምህርት ቤት መገንባት የለበትም በጣም ግልጽ ነው:: ጉዳዩ እዚህ ድረስ አደጋ ነው::
ቢድዓን ሳይቃጠል በቅጠል እንደተባለው ብሂል በእንጭጩ መቅጨት ጭጭ ማድረግ እንጂ አድጋ እንድታጠፋ
"ምን ችግር አለበት" በሚል የስራ ፍቃድ መስጠት ኋላ ለዲን መበላሸት ለሱናህ መጥፋት ምክንያት ነውና ከወዲሁ ነቃ ብለን ልትታገለው ይገባል
ወገብን ጠበቅ ማድረግ ነው::