Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

አዛንና ኢቃም‬

‪#‎አዛንና_ኢቃም‬
የአዛንና ኢቃም ትርጉሞችና ሸሪዓዊ ድንጋጌዎቻቸው
ሀ. የአዛንና የኢቃም ትርጉም፦
አዛን ማለት የዓረብኛ ቋንቋ ትርጉሙ ማሳወቅ ማለት ነው፡፡
አላህ እንዲህ ብሏል፡-
“ይህ) ከአላህና ከመልክተኛው በታላቁ ሐጅ ቀን የወጣ ወደ ሰዎች የሚደርስ ማስታወቂያ ነው”(9:3)
ሸሪዓዊ ትርጉሙ፦ በተወሰኑ ዚክሮች የሰላት ወቅት መድረሱን ማሳወቅ ማለት ነው፡፡
ኢቃማ ማለት ደግሞ የዓረብኛ ቋንቋ ትርጉሙ የተቀመጠን ማስነሳት ማለት ሲሆን ሸሪዓዊ ትርጉሙ በሚታወቁ ዚክሮች ለሰላት እንዲቆም የሚደረግ ጥሪ ማለት ነው፡፡
ለ. ሸሪዓዊ ድንጋጌያቸው፦
አዛንና ኢቃም ለአምስት ሰላቶች ወንዶች ላይ “فرض كفاية” (በተወሰኑ ሰዎች ላይ ብቻ ግዴታ) የሆነ ሲሆን በቂ ሰው ከፈፀመው ግዴታነቱ ከሁሉም ይነሳል፡፡
ሁለተኛ
ትክክለኛ እንዲሆኑ መሟላት ያለባቸው መስፈርቶች
1. ሙስሊም መሆን፡- ካፊር ቢፈፅማቸው ትክክለኛ አይሆኑም
2. አእምሮ ጤናማ መሆን፡- ልክ እንደሌሎች አምልኮቶች እብድ በስካር ላይ ያለና ህፃን ቢፈፅማቸው ትክክል አይሆኑም፡፡
3. ወንድ መሆን፡- ሴት ድምጿ ፈታኝ በመሆኑ አዛን ማድረግ የለባትም፡፡ እንዲሁም ፍናፍንት ከሆነ ወንድነቱ ስለማይታወቅ አዛንና ኢቃም ማድረግ የለበትም፡፡
4. አዛኑን በሰላት ወቅት ማድረግ፡- ለሱብሂና ለጁምዓ የመጀመሪያዎች አዛን ካልሆነ በቀር የሰላት ወቅት ሳይደርስ አዛን ማድረግ አይፈቀድም፡፡ ኢቃም የሚደረገው ደግሞ ሰላት ውስጥ ለመግባት ሲፈለግ መሆን አለበት፡፡
5. አዛንና ኢቃም ሲደረግ ቅደም ተከተላቸውን የጠበቀ ተከታታይ የሆኑ ቃላቶች መሆን አለባቸው፡፡ የአደራረጉ ሁኔታ አራተኛው ነጥብ ላይ ይገለፃል፡፡
6. አዛንና ኢቃም ሸሪዓው በደነገጋቸው ቃላቶችና በዓረብኛ ቋንቋ መደረግ አለባቸው፡፡
የዛሬ ጥያቄ ይሳተፉ!
አዛን ትክክለኛ እንዲሆኑ መሟላት ካለባቸው መስፈርቶች አንዱን ጥቀሱ?
‪#‎ፊቅህን_ለመረዳት‬
የፌስ ቡክ ገፃችንን ለማግኘት…
www.facebook.com/easyfiqh
ሼር ማድረግ እንዳይረሱ!