#ልብስን―ማስረዘም#
ኢብኑ አልዐረቢ አልማሊኪ (ረሂመሁላህ) እንዲህ ብለዋል፦
"አንድ ወንድ ልጅ ልብሱን ከቁርጭምጭሚቱ ማሳለፍ አይበቃለትም፣
ከቁርጭምጭሚት ያሳለፍኩት ያለ ኩራት ነው ሊል አይገባም፣ የሐዲሱ ክልከላ ይህንንም ያካትታልና።
ሀዲሱ ላይ ያለው ቃልና ፍርድ፣
የተጠቀሰው ምክንያት እኔ ላይ የለምና አልተገብርም ማለት የለበትም፣
ይህ አይነቱ ሙግት ተቀባይነት የለውም፣
እንዲያውም ልብሱን ማስረዘሙ ኩራት እንዳለበት ይጠቁማል…"
【ፈትሑል ባሪ /ኪታቡ ሊባስ ገፅ 771】