Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ግራጁዌሽን Graduation day

ግራጁዌሽን
አላህ ለዋለልን ውለታ ልናመሰግነው እንጂ ልናምፀው አይገባም፡፡ የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች በየአመቱ ግራጁዌሽን (ምርቃት) ሲደርስ ኢስላማዊ መፅሄት ማዘጋጀት አለብን፣ ፎቶ መነሳት አለብን …… እና የመሳሰለውን የሚሉ አልጠፉም፡፡ እንደው የማይሰልመውን ሁሉ ካላሰለምን ማለት ምናለ ቢቀርብን፡፡ የወንድም ይሁን የሴት ሙስሊሞች ፎቶ ተለጥፎ ስም ከነአባባሎች ተፅፈው በጎኑ ጥቄት ሀዲሶች ተደባልቀውበት ኢስላማዊ ሊባል አይችልም፡፡
ኢስላም የሚከለክለውን ሳይከለከሉ ኢስላማዊ ማለት ምንኛ ሞኝነት ነው፡፡ አስገራሚው አንዳንዶች ‹‹ዶሩራ (ለችግር ጊዜ የሚደረግ ነው)›› ይላሉ፡፡ እስቲ የሙስሊሞች መፅሄት ተብሎ የወጣት ሴቶችንና ወንዶችን ፎቶ አለመለጠፉ ምኑ ነው ችግር?
እንዲያውም ይሄ ፅድቅ፣ አላህን መታዘዝ እንጂ (ፎቶ አለመለጠፉ)፡፡
ያው ሳታማሃኝ ብላኝ እንዳለው ነው፡፡ ሴትና ወንድ ወጣቶችን እሳትና ጭድን አንድ የመደባለቅ ያህል ይደበልቋቸዋል፡፡ አስገራሚው ኢስላማዊ የሚል ስም ይሰጡታል፡፡ ተመራቂ ተማሪዎች ሆይ! እንዲህ አይነት አፀያፊ ተግባሮችን ራቋቸው፡፡ ‹‹የአሚር ትዕዛዝ ነው›› የሚባለውንም ቅጥፈት ወደ ጎን ተዉት፡፡ አላህ በሚታመፅበት ጉዳይ ፍጡራንን መታዘዝ የለም ይሉና የአላህ መልክተኛ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም)፡፡
ድሮ የዩኒቨርስቲ ተማሪ በነበርን ጊዜ ሸውደውን ነበር ‹‹ቁጥራችንን ማሳየት አለብን›› ፎቶ እንነሳ እየተባለ፡፡ አላህ ከሱና ኡስታዞች ጋር አስተዋውቆን ኢስላም ማለት በስሜት መነዳት እንዳልሆነ፣ ሱናን መከተልና ቢድዐን መራቅ እንደሆነ አስተማሩን፡፡
አልሃምዱሊላህ፡፡