Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ጉዞ ወደ አብሬት?

ጉዞ ወደ አብሬት?
ህያው የሆነው የማይሞተውን አላህ በማምለክ ከሽርክና ቢድዐ በመራቅ ሁለት አገር ደስታ ማግኘት እየተቻለ፣ ለምን ይሆን ሰዎች የማይሰሟቸው፣ የት እንዳሉ የማያውቋቸውን፣ ይመጣሉ እያሉ (አበራሙዝ ሺሊላህ ሰንብቶኒ ‹የአበራ ሙዝ አባት ሰንብቱልን›) የሚጠብቋቸውን ፍጡር ለማምለክ የሚጥሩት?
ሁለት አገር መክሰር ፈለጉን?
ዱንያ ላይ አቅጣጫው ጠፍቶባቸው ቢጠሩ የሚሰማቸው አጥተዋል፡፡ በአላህ ላይ እያጋሩ ንሰሃ ሳይገቡ ከሞቱ አለቀላቸው፡፡ ከሞት ጀምሮ ከባድ አደጋ ያጋጥማቸዋል፡፡ የሚቀጥለው አለም ደግሞ ከዚህ የከፋ ነው
- የአላህን ፊት አለማየት፣
- ጀነት በፍፁም አለመግባት፣
- ገሃነም ውስጥ ገብቶ መቼም አለመውጣት፣
እና የመሳሰሉትን፡፡
ውድ የአላህ ባርያዎች እነዚህን ሰዎች ቤተሰቦቻችንም ይሁን አይሁኑ ልናስጠነቅቃቸው ይገባል፡፡ ሁሉን በማድረግ ላይ ቻይ የሆነውን ብቸኛው ፈጣሪያችን አላህ ሊፈሩና አለ የሚባለውን አምልኮ ሁሉ በብቸኝነት ሊፈፅሙለት ይገባል፡፡ ሙታን፣ ደካማ፣ መልስ መስጠት ለማይችሉ፣ ፍጡራን መላእክትም ይሁኑ ነብይ ምንም አይነት አምልኮ ሊፈፀምላቸው አይገባል፡፡ ይህን የፈፀመ ሁለት አገር ከሰረ፡፡
አላህ እንዲህ ይላል
إِن تَدْعُوهُمْ لَا يَسْمَعُوا۟ دُعَآءَكُمْ وَلَوْ سَمِعُوا۟ مَا ٱسْتَجَابُوا۟ لَكُمْ ۖ وَيَوْمَ ٱلْقِيَٰمَةِ يَكْفُرُونَ بِشِرْكِكُمْ ۚ وَلَا يُنَبِّئُكَ مِثْلُ خَبِيرٍ
ብትጠሩዋቸው ጥሪያችሁን አይሰሙም፡፡ ቢሰሙም ኖሮ ለእናንተ አይመልሱላችሁም፡፡ በትንሣኤም ቀን (እነርሱን በአላህ) ማጋራታችሁን ይክዳሉ፡፡ እንደ ውስጠ ዐዋቂው ማንም አይነግርህም፡፡

አብሬትም፣ ቃጥባሬም በጠቅላላ ፍጡራን፣ ሙታን ሲሆኑ ብቸኛው የፍጡራን ሁሉ ፈጣሪ ደግሞ የማይሞት ህያው ነው፡፡ ታድያ ምን ለማግኘት ነው ከምንም እራሳቸውን ማስጣል የማይችሉ ሙታንን ከአላህ ጋር አጋር ተደርገው የሚደረቡት?
ድንገት ይሉ ይሆናል፡፡ ወልዬች የአላህ ቅርቦች ናቸው፡፡
መልሱ የአላህ ወልይ የሆነውን የሚያውቀው አላህ ብቻ ነው፡፡ የአላህ ወልዬች ጥቅል ባህሪያቸው በአላህ አምነው እሱንም የሚፈሩ (ይጠነቀቁታል፣ ትዕዛዙን በመታዘዝ ክልከላውን በመከልከል) ናቸው፡፡
አደለም ገና አላህ ዘንድ ያላቸው ቦታ ያልተረጋገጠላቸው ግለሰቦች ሁለቱ ታላቅ የአላህ ባርያዎች ጂብሪል (አለይሂ ሰላም) የመላእክቶች አለቃና፣ ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) የአደም ልጆች ሁሉ ምርጥ ምንም አይነት አምልኮ አይገባቸውም፡፡
ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለምም) አንድ አላህ በብቸኝነት እንዲመለክና ከእርሱ ውጭ ያሉት አምልኮዎች ሁሉ እርግፍግፍ ተደርገው እንዲተው ጥሪ ለማድረግ አብሳሪና አስፈራሪ አድርጎ ነው አላህ የላካቸው፡፡
ጓዝ ተይዞ ጎዞ ወደ አብሬት ውድቅ ነው፡፡ ምክንያቱም ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) እንዲህ ይላሉ ‹‹ከ3 መስጂዶች ውጭ ጓዝ ተቅልሎ ጎዞ የለም ወደ መስጂድ አል ሀረም፣ የኔ መስጂድ (መዲና የነብዩ መስጂድ)፣ መስጂደል አቅሳ››፡፡
ታድያ የነብዩን ትዕዛዝ እየጣሱ ነብዩንም ይሁን አላህን መውደድ ውሸት አይደለምን
ነው እንጂ፡፡ የቅጥፈትም ቅጥፈት፡፡
አላህ ሀቁን መንገድ ይምራን፡፡