Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

አሽሸይኽ ሙሐመድ ዐሊ አደም አልኢትዮጲ ማናቸው?

አሽሸይኽ ሙሐመድ ዐሊ አደም አልኢትዮጲ ማናቸው?

እርሳቸው አሽሸይኽ አልዐላማቱል ሙሐዲሥ ፣ ፈቂህ ፣ ኡሱሊ እና ነሕዊይ ሙሐመድ አሽሸይኽ ዐላመቱል ዐሊይ ቢን አደም ቢን ሙሳ ቢን ሙሐመድ አል ኢትዮጲ አልወለዊይ ናቸው።

ሸይኹ ሐፊዘሁላህ በራሳቸው አንደበት እንደተናገሩት የተወለዱት በ1366 ዓመተ ሒጅራ ነው። ዒልምን «ሀ» ብለው የጀመሩት በአባታቸው አሽሸይኽ ዐሊይ ረሒመሁላህ ቁርአንን በመሐፈዝ ነበር። አባታቸውም ለሸይኽ ሙሐመድ ቀዩ ቁርአንን እንዲያስጨርሷቸው ሰጧቸው። ቁርአንንንም አጠናቀው ከጨረሱ በኋላ በአካባቢያቸው በሚገኘው «ረፊያ» በሚባል መድረሳ ውስጥ ኪታብ መቅራት ጀመሩ።

ሸይኹ ከተማሩባቸው ታላላቅ ዑለማዎች ውስጥ በጥቂቱ . . .

1) ዒልምን ከወሰዱባቸው ውስጥ አባታቸው ታላቅ ዐሊም ፈቂህ ፣ ኡሱሊ፣ ሙሐዲሥ እና ነሕዊይ አሽሸይኽ ዐሊይ ቢን አደም ቢን ሙሳ አሊትዮጲ ወረሂመኒ አልለህጀዲ አልሙሃጂር ረሒመሁላህ ናቸው።

በአባታቸው ከተማሩት ኩቱቦች ውስጥ ከአላህ ኪታብ ቀጥሎ በሃገራቸው ይማሩበት በነበረው ትምህርተ ስርአት የሚካተት የዐቂዳ ኪታቦች እና በሐነፊያ መዝሃብ ውስጥ ተጠቃሽ ከሆኑት ኪታቡል ቁዱሪ ከነማብራሪያው፣ ከንዙል ደቃኢቅ እና የመሳሰሉትን ኩቱቦች ረፊያ በተባለው መድረሳ ውስጥ ተምረውባቸውዋል።

በተጨማሪም በኡሱሉል ፊቕ አልመናር ከነማብራሪያው፣ አልተውዲሕ ሊሰድሪል ሸሪዐህ ከነተንቂህ ከተሰኘው የኪታቡ ማብራሪያ ጋር እና የመሳሰሉትን ኩቱቦች ተምረውባቸዋል።

ከሒሳብ ትምህቶች ዒልመል ጀብር ወልሙቃበላ፣ ዒልመል ሚቃት የቀሩባቸው ሲሆን ከሰሒሕ አልቡኻሪ አብዛኛውን ተማረውባቸዋል። ዛሬ ላይ ሸይኹ ከያዙት እውቀት አብዛኛውን የወሰዱት ከወላጅ አባታቸው ነው። አባታቸውም ይህንን ችሎታቸውን ተመልክተው በቃልና በፅሁፍ የብቃት ማረጋገጫ (ኢጃዛ) ሰጥተዋቸዋል።

2) በመቀጠልም ሸይኹ ሐፊዘሁላህ እውቀት ከወሰዱባቸው ዑለማዎች መካከል አልዐላመቱል ነሕዊይ፣ አልሉጘዊይ፣ ባለመልካም ስነምግባሩ አሽሸይክ ሙሐመድ ሰዒድ ቢን አሽሸይኽ ዐሊ አልደሪይ ረሒመሁላህ ሲሆኑ ሸይኹ ዘንድ ከሶስት አመታት የቀረበ ጊዜ አብረዋቸው አሳልፈዋል። ከሳቸውም ከፊል የሆነ ሰሒሕ ቡኻሪና ሰሒሕ ሙስሊም የተማሩ ሲሆን ከነሕው፣ ከሶርፍ፣ ከበላጛ፣ ከመንጢቅ፣ ከመቁላቱል ዒሽር፣ ከአዳቡል በሕሥ ወልሙናዘራት፣ ከኡሱሉል ፊቕህ ተምረውባቸዋል።

3) በተጨማሪም የፋኪህ አልጀኒያን ከፊል፣ አልፊያ ቢን ማሊክ ከነማብራሪያው ኢብን ዐቂል፣ አልኹደሪ፣ ሙጂቡል ነዳ ዐላ ቀጥሪንነዳ ያሲን ሒምሲ ከፃፉት ማብራሪያው ጋር፣ ሙጝኒን ለቢብ አን አልዱሱቂ እና አልአሚር ከፃፉት ማብራሪያው ጋር፣ ሻፊያ ኢብን አልሓጂብ ከነማብራሪያው፣ ከበላጛ ኩቱቦች ደግሞ አልቀዝዊኒ ከነማብርሪያው፤ ከመንጢቅ ኩቱቦች ደግሞ ሰልም አልመንሩቅ ከነማብራሪያው፣ አሊሳጙጂ ከነማብራሪያው የተማሩባቸው ሲሆን በአጠቃላይ አብዛኛውን የዐረብኛ እውቀት የያዙት ከኚሁ ዐሊም ነው። ረሒመሁላህ

ከሸይኾቻቸው መካከል . . .

1) ሸይኽ ዐብዱል ባሲጥ ቢን ሙሐመድ ቢን ሐሰን አል ኢትዮጲ አል ቦረኒ አል ምናሢ ሲሆኑ ለበርካታ አመታት በጓደኝነት አሳልፈዋል። የዘመናቸው ሲበወይህ (የነሕው አስተማሪያቸው) ነበሩ። ከርሳቸው የዐረብኛ እና ሌሎች እውቀቶችን የወሰዱባቸው ሲሆን ከተማሩባቸው ኩቱቦች ውስጥ የአጅሩሚያ ሙቀዲማ ኢዕራብ፣ ሙልሐቱል ኢዕራብ ከነማብራሪያው ከሽፉል ኒቃብ፣ አልፈዋኪሁል ጀኒያህ፣ ነዝሙል አንዋር ፊ ሙስጦለሒ አልሐዲሥ የተማሩባቸው ሲሆን እኚህ ሸይኽ ወደ አዲስ አበባ ለኑሮ በመጡበት ጊዜ ሸይኽ ሙሐመድ ዐሊ አደምን በርሳቸው ቦታ ይተኳቸው የነበረ ሲሆን ሸይኹ የማስተማር ፍቃድ ሰጥተዋቸዋል።

2) ሌላኛው ሸይኹ ከተማሩባቸው ሹዩኾች መካከል አልዐላመቱል ነሕሪር አሽሸይኽ ሙሐመድ ዘይን ቢን ሙሐመድ አሊትዮጲ አልዳኒይ ረሒመሁላህ ናቸው። በሳቸውም ከሶሒሕ ሙስሊም በኢማሙ ነወዊ ማብራሪያ አብዛኛውን የቀሩባቸው ሲሆን በተጨማሪም የሱነኑል በይሃቂይ መጀመሪያዎቹን ክፍል፣ የሶሒሐል ቡኻሪን ትምህርት ሲያስተምሩ ብዙውን አድምጠዋል። የቁርአን ተፍሲርን እና ከበላጛ ትምህርትም ጀውሃረል መክኑን፣ በሙስጦለሐል ሐዲሥ ደግሞ ጠላዐቲል አንዋር ከነማብራሪያው እና የመሳሰሉትን በርሳቸው ላይ ተምረዋል። ረሒመሁላህ

3) በተጨማሪም ሸይኹ ሐፊዘሁላህ የዘመናችን የሐበሻ ምድር ሙሐዲሥ የነበሩት አልዐላመቱል ሙሐዲሥ #አሽሸይኽ_ሙሐመድ_ራፊዕ ረሒመሁላህ የተማሩባቸው ሲሆን ከተማሩባቸውም ኩቱቦች ውስጥ ጃሚዑል ቲርሚዚይ፣ አቢዳውድን ፣ ነሳኢይ፣ ኢብን ማጃህ፣ እና የተወሰነውን ሶሒሕ ሙስሊም ሌሎች ተማሪዎቻቸውን ሲያስተማሩ አድምጠዋል። እሳቸውም የማስተማር ፍቃድ ሰጥተዋቸዋል።

ከዚያም ወዲህ ሸይኹ ሐፊዘሁላህ ወደ መስጂደል ሐረም መከተል ሙከረማ የተጓዙ ሲሆን በመስጂደል ሐረም ውስጥ በርካታ እውቀቶችን ቀስመዋል። በአሁን ሰአትም በመካ መስጂድ ውስጥ የማታ ክፍለ ጊዜ ላይ እና በመኖሪያ ቤታቸው ውስጥም ጭምር በማስተማር ላይ ይገኛሉ።

ሸይኹ ሐፊዘሁላህ እጅግ የሚያስደምም የሒፍዝ ችሎታ ያላቸው ሲሆን ብዙ የሆኑ የዐረብኛ ስነፅሁፍና ግጥሞችና ሌሎችም ዲናዊ ዘርፎች ላይ የተፃፉ ኩቱቦችን በቃላቸው ሸምድደዋል ። ከነርሱም አልፊያ ኢማም ማሊክ (ባለ አንድ ሺህ ስንኝ) እና አልፊያ አስሱዩጢ (አንድ ሺህ ስንኝ በሙስጦለሓል ሃዲስ) እናም የመሳሰሉት ዘርፎች ላይ የተከተቡ ኩቱቦችን በቃላቸው ሸምድደዋል። በነሕው ፣ በሶርፍ ፣ በበላጛ ፣ በኡሱል ፣ በመንጢቅ ፣ በሐዲሥ ፣ በፊቕ ፣ በሌሎች ኢስላማዊ ጥናቶች ላይ ላቅ ያለ ዕውቀት አላቸው።

ከሳቸው የተማሩ ተማሪዎችም በአሁኑ ሰአት ሸይኹ እውቅና (ተዝኪያ) ሰጥተዋቸው በተለያዩ የዓለም ክፍሎች ላይ ከርሳቸው የተማሩትን እውቀት እያስተማሩና ፈታዋ እየሰጡ ይገኛሉ

ሸይኹ ሐፊዘሁላህ ከማስተማር ባሻገር ጊዜያቸውን ለአላህ ዲን ሰውተው በርካታ ኩቱቦችን በተለይም በሐዲሥ ዘርፍ ላይ ፅፈዋል።

ሸይኹ ከፃፏቸው ኩቱቦች ውስጥ . . .

(1) ሸርሁ ሱነን አንነሳዒ «ዘሒረተል ዑቅባ ፊ ሸርሒል ሙጅተባ» በአርባ ሁለት ጥራዝ የፃፉ ሲሆን እስካሁን ለበርካታ ጊዜ ለህትመት በቅቷል።

ታላቁ የየመን የሱና አንበሳ አሽሸይኽ ሙቅቢል አልዋዲዒይ ረሒመሁላህ ስለዚህ ኪታብ እና ስለሸይኹ ሲናገሩ ፦

« ይሄ ማብራሪያ ልክ በሐፊዝ ኢብኑ ሐጀር (የቡኻሪ ማብራሪያ) ፈትሑል ባሪ አዘገጃጀት መልኩ የተዘጋጀ ሲሆን ሚዛን የሚደፋውን እና ማስረጃ የሚገጥመውን አመራረጣቸው ነፍስን በሚያረካ መልኩ ነው። እኔ ለእውቀት ፈላጊዎች (ለተማሪዎች) የምመክረው ይህን ታላቅ ኪታብ (ይዘው) በማከማቸት ላይ እንዲሽቀዳደሙ ነው ። የዚህ አይነት ማብራሪያ የዘመናችን ሙሐዲሦች ይዘው ሊመጡ አይቻላቸውም።»

ሸይኽ አልባኒ ረሒመሁላህ በበኩላቸው ይሄን ኪታብ ሲገልፁት፦
« ይህን በመሰለ መልኩ በነሳኢይ ላይ አንድም የሰለፊ ማብራሪያ አላውቅም» ብለዋል።

(2) «ቁረቱል ዐይን» የሁለቱ ሰሒሖች (ቡኻሪና ሙስሊም) ሐዲሥ ዘጋቢ ግለሰቦች ላይ የሚያጠነትን ኪታብ በሁለት ጥራዝ

(3) «ቁረቱል ዐይኑል ሙሕታጅ ፊ ሸርሒል ሙቀዲመቱል ሙስሊም ቢን ሓጃጅ» በሁለት ጥራዝ

(3) البحر المحيط الثجاج في شرح صحيح مسلم بن الحجاج، تم منه سبعة وعشرين جزءاً، طبع منه أربعة عشر جزءاً.
(4) مشارق الأنوار الوهاجة، ومطالع الأسرار البهاجة في شرح سنن ابن ماجه، تم منه أربع مجلدات.
(5) قرة العين في تلخيص تراجم الصحيحين، مجلد، طبع مرتين.
(6) إسعاف ذوي الوطر في شرح نظم الدرر، شرح «ألفية السيوطي» في المصطلح، مجلدان، طبع ثلاث طبعات. وهذا هو الشرح الصغير
(7) «البحر المحيط الأزخر في شرح نظم الدرر في علم الأَثَر» شرح موسع لم يكمل، هو أصل «إسعاف ذوي الوطر» المذكور
(8) نظم شافية الغلل في ألفية العلل.
(9) مزيل الخلل شرح شافية الغلل المذكور. مطبوع معها
(10) نظم الجوهر النفيس في نظم أسماء ومراتب الموصوفين بالتدليس وعدَّتها مائة وثمانية عشر بيتاً.
(11) الجليس الأنيس في شرح الجوهر النفيس المذكور.
(12) تذكرة الطالبين في ذكر الموضوع وأصناف الوضاعين.
(13) الجليس الأمين في شرح تذكرة الطالبين المذكور.
(14) رفع الغين في ثبوت زيادة «وبركاته» في التسليم من الجانبين.
(15) عمدة المحتاط في نظم أسماء من رُمي من الثقات بالاختلاط.
(16) عُدّة أولي الاغتباط في شرح عمدة المحتاط المذكور.
(17) نظم إتحاف أهل السعادة بمعرفة أسباب الشهادة.
(18) بغية طالب السيادة في شرح إتحاف أهل السعادة بمعرفة أسباب الشهادة. شرح إتحاف أهل السعادة المذكور
(19) إتحاف النبيل بمهمات علم الجرح والتعديل.
(20) إيضاح السبيل في شرح إتحاف النبيل.
(21) قصيدة في مدخل شرح النسائي.
(22) قصيدة في الرد على بكر بن حماد الشاعر المغربي في ذمه علم الحديث وأهله.
(23) مختصر مجمع الفوائد، ومنبع العوائد بذكر الأثبات والأسانيد المسمّى «مواهب الصمد لعبده محمد».
(24) فتح القريب المجيب شرح مُدني الحبيب نظم مغني اللبيب في النحو، نظم الشيخ عبد الباسط بن محمد رحمه الله تعالى، مجلدان.
(25) الجليس الصالح النافع شرح الكوكب الساطع في أصول الفقه، مجلد.
(26) التحفة المرضية نظم في أصول الفقه على طريقة أهل السنة السنيّة في (3072) ثلاثة آلاف واثنين وسبعين بيتاً.
(27) المنحة الرضية في شرح التحفة المرضية، ثلاث مجلدات.
(28) نظم مختصر في علم الفرائض.
(29) فتح الكريم اللطيف، شرح أرجوزة التصريف، شرحٌ لنظم الشيخ عبد الباسط رحمه الله تعالى لكتاب المراح في الصرف.
(30) الفوائد السمية في قواعد وضوابط علميّة.
(31) قصيدة الرد المُبكي للمجرم الدينماركي.
(32) جامع الفوائد، وضابط العوائد، جُمعت فيه الفوائد العلميّة النحويّة أو اللغويّة، أو الحديثيّة، أو الفقهيّة، نظماً أو نثراً. (يصدر قريبا إن شاء الله تعالى)
(33) نظم مقدمة التفسير لابن تيمية رحمه الله تعالى. (يصدر قريبا إن شاء الله تعالى)
(34) نظم في علم التوحيد. (يصدر قريبا إن شاء الله تعالى)
(35) نظم خاتمة المصباح المنير. (يصدر قريبا إن شاء الله تعالى)
(36) رجزٌ في علمي العروض والقوافي. (يصدر قريبا إن شاء الله تعالى)
(37) إتحاف ذوي الهمة بفوائد مهمة جُمعت في بيان حكم القيام للقادم وتقبيل اليد ونحوه. (يصدر قريبا إن شاء الله تعالى)
(38) «مجمع الفوائد، ومنبع العوائد بذكر الأثبات والأسانيد» وهو ثَبَتٌ مُطوّل جامع لأشتات الأسانيد والأثبات. لم يكمل
(39) نظم الأحاديث المتواترة، لم يكمل
(40) نظم شافية ابن الحاجب، لم يكمل
(41) نظم العقيدة الواسطية، لم يكمل

እና ሌሎች በዐረብኛ ነሕው፣ ሶርፍ፣ እና በሐዲሥ ዘርፍ ዙሪያ በርካታ ኩቱቦችን ፅፈዋል ።

አላህ ሱብሓነሁ ወተዓላ ሸይኹን ረዥም እድሜ እንዲሰጣቸውና እኛም ከእውቀታቸው የምንጠቀም ያድርገን።