Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

የግዴታ_ሰላቶች_ብዛት‬



#‎የግዴታ_ሰላቶች_ብዛት‬
ግዴታ የሆኑ ሰላቶች አምስት ሲሆኑ እነሱም ሱብሂ፣ ዙህር፣ ዐስር፣ መግሪብና ዒሻ ናቸው፡፡ በዚህ ላይ ዑለማዋች ሁሉ የተስማሙ ሲሆን ማሰረጃው ጠልሃ ኢብን ኡበይዲላህ ያስተላለፉት ሀዲስ ነው፡፡
“አንድ ገጠሬ ዓረብ ወደ ነብዩ (ﷺ) በመምጣት “አላህ ግዴታ ያደረገብኝ ሰላቶች ስንት ናቸው? በማለት ሲጠይቃቸው እሳቸውም “በቀንና ሌሊት ውሰጥ አምስት ሰላቶችን መስገድ ነው” በማለት መለሱለት::
(ሙስሊም ዘግበውታል)

አነስ ባስተላለፉትም ሀዲስ :-
“ከገጠር አንዱ ወደ ነብዩ (ﷺ) መጣና “የእርሶ መልዕክተኛ በቀንና ሌሊት አምስት” ሰላቶችን መስገድ እንዳለብን ነግሮናል” ሲላቸው እሳቸው “እውነቱን ነው” በማለት መለሱለት፡፡(ሙስሊም ዘግበውታል)
‪#‎የግዴታ_ሰላት_የሚመለከተው_ሰው‬
ሰላት ግዴታ የሚሆነው በማንኛውም ሙስሊም አቅመ አዳም በደረሰና አእምሮው ጤናማ በሆነ ሰው ሲሆን ህፃን ልጅ ግን ሰባት አመት ሲሞላው እንዲሰግድ መታዘዝ ሲኖርበት አስር አመት ሲሞላው ማይሰግድ ከሆነ በመግረፍ እንዲሰግድ ማድረግ ግዴታ ነው፡፡
ነብዩ (ﷺ) እንዲህ ብለዋል
“ልጆቻችሁ ሰባት አመት ሲሞላቸው እንዲሰግዱ እዘዟቸው አስር አመት ሞልቷቸው አልሰግድም ካሉ ግረፏቸው እንዲሁም በመኝታ ለዩዋቸው::” (አህመድ አቡዳውድና ቲርሚዚይ)
የፌስ ቡክ ገፃችንን ለማግኘት…
www.facebook.com/easyfiqh
ሼር ማድረግ እንዳይረሱ!