Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ምነው አንተ ቅጠል! ግጥም

 
ምነው አንተ ቅጠል!
መልክህ አረንጓዴ መዘዝህ ግን እሬት
ምነው አንተ ቅጠል ሰዎች ቢኖሩበት?
አሞራን ሲበሏት ጅግራ ናት እንዳሉት
ያንተም ባልደረቦች ስምክን ሊያወድሱት
ምነው አንተ ቅጠል ስምክን ጫት አሉት።
ምነው እኔ ባልኩህ መዘዘኛው ጠላት
ኢኮኖሚን በዝባዥ የሱሶች ባላባት
የጊዜ ደመኛ የእስልምና ጠላት
ምነው አንተ ቅጠል ስምክን አወደሱት
የሙእሚኖች ቀለብ የዱዓ ፀጋ አሉት!!!
አይደለም ለሙእሚን ልትሆን ለሙስሊሞች
ለፍየልም አትሆን ያውም ለእንሰሳቶች።