Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

አንድ ሰው ከዚህ አለም በሞት ሲለይ እገሌ “ሞተ” እንጂ “አረፈ” አይባልምና ይ ታ ረ ሙ



ከሐዲስ 📚 ማኅደር
አንድ ሰው ከዚህ አለም በሞት ሲለይ እገሌ “ሞተ” እንጂ “አረፈ” አይባልምና ይ ታ ረ ሙ❗
ከስድስቱ የእምነታችን መሰረቶች አንዱ በትንሳዔው እለት እውነታ ማመን ነው። ይህ የቂያም እለት ደግሞ በውስጡ እጅግ በርካታ ውጣ ውረዶች ኣሉበት።
እንደምሳሌነትም እንደየስራችን ሂሳባችንን መተሳሰብ፣ የቀብር፣ የማእሸርና የሲራጥ ፈተና፣ ቅጣት፣ እንዲሁም የጀነት ፀጋና የእሳት ስቃይ ኣለበት። ይህ ደግሞ የሚደረስበት ከሞት በኋላ ነው። ማንም ይሁን ማን ፍጡር የተባለ ሁሉ መሞቱ የማይታበል ሀቅ እንደሆነ ሁሉ ከሞተበት እንደገና ተቀስቅሶ ህይወት ተዘርቶለት የማይቋረጠውን የቅጣት ወይም የፀጋ ህይወት እንዲኖር መደረጉም ምንም የማያሻማ እውነታ ነው።
ስለሆነም አንድ ግለሰብ ሲሞት ከዚህ የሂሳብ ውጤት በፊት በተለምዶ እንደሚባለው ለማንም “ኣረፈ” ልንል አይገባም።
በሀዲስ እንደመጣውም « የአላህ መልእክተኛ ሆይ ! “እገሊት ሞተችና አረፈች” ሲባሉ፤ የአላህ መልእክተኛ [ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም] ቆጣ ኣሉና «إِنَّمَا يَسْتَرِيحُ مَنْ غُفِرَ لَهُ» “የሚያርፈውማ ምህረት የተደረገለት ሰው ነው።” ኣሉ… በማለት ዓኢሻ [ረዲየላሁ አንሃ] አስተላልፋልናለች።
📕صحيح _السلسلة الصحيحة(4/286)📕
ይህንን ሀዲስ በመንተራስም አልመናዊ [ረሂመሁላህ]
✍🏼
{ “ የሚያርፈውማ ምህረት የተደረገለት ነው” ማለት ወንጀሉ ተሸፈኖለታልና በሷ አይቀጣም ማለት ሲሆን፤ ምህረት እንደተደረገለት የተረጋገጠለት ሰው በእርግጥም አርፏል። ይኸ ደግሞ ጥሩውና መጥፎው ከተለየና ለጀነት የበቁት ወደ ጀነቱ እንዲገቡ ከታዘዘ በኋላ ነው የሚታወቀው። ስለዚህም ሞት "አሳራፊ" አይደለችም። ከሞት በኋላ ያለው (የየግለሰቡ ውጤት) ከኛ የተሰወረና የማናውቀው ነውና።
ለዚህም ነው አንዱ አዋቂ ሰው “አንድ ባሪያ የእረፍትን ጣዕም የሚያገኘው መቸ ነው?” ተብለው ሲጠየቁ “የመጀመርያ ኮቴው ጀነት ስትረግጥ ነው።” በማለት መልሰዋል።} ብለዋል።
📕فيض القدير(2/365)📕
ስለዚህም ማንም ይሁን ማን ሲሞት ወደ እረፍት ሳይሆን ወደ ሂሳብ ነውና የሚሄደው፤ እገሌ ወይም እገሊት ሞቱ ከማለት ውጭ አረፈ፣ አረፈች ማለት አግባብ አይደለምና ይ ታ ረ ሙ❗
============
25/04/1437🕑04/02/16
©ተንቢሃት
[📑⁰¹⁵/¹⁶]أحمـــــــــــــــabfـــــــد