Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ሙእሚን አንድን መጥፎ ተግባር ሲፈፅም ቅጣቱ በአስር መንገዶች ይመከትለታል።


ከሊቃውንት 📑 ማኅደር

ሙስሊሞች እምነታቸው ምንም ያህል ጠንካራ ቢሆንም የሰው ልጆች ናቸውና ይሳሳታሉ፣ ይዘነጋሉ፣ ይረሳሉም። በነዚህና በመሳሰሉት ምክንያቶች ወንጀል ቢፈፅሙ፣ ስህተት ቢገኝባቸው እንኳን ሃያሉ ጌታችን አላህ የተለያዩ ሰበቦችን በመፍጠር ከኃጢኣታቸው ያፀዳቸዋል።

እንደምሳሌነትም ሸይኹል ኢስላም ኢብኑ ተይሚያ رحمـه اللـه ቀጣዩን ያስገነዝቡናል።☞

🍂🍃
{[ ሙእሚን አንድን መጥፎ ተግባር ሲፈፅም ቅጣቱ በአስር መንገዶች ይመከትለታል።

~ ተውበት ያደርግና አላህ ይቅር ይለዋል። ከኃጢኣቱ የሚመለስ ሰው ምንም ኃጢኣት እንዳልነበረው ነውና።

~ ወይም ጌታውን ማረኝ ይለውና [ኢስቲግፋር አድርጎ] ይምረዋል።

~ ወይም መልካም ተግባርን ይፈፅምና ያብስለታል። በጎ ተግባራት መጥፎዎቹን ያስወግዳሉና።

~ ወይም ሙእሚን የሆኑ ወንድሞቹ ዱዓእ ያደርጉለታል፤ በህይወት ቢኖርም ባይኖርም ምህረትን ይለምኑለታል። በዚህም ይታበስለታል።

~ ወይም [ሙእሚን ወንድሞቹ] የበጎ ተግባራቸውን ምንዳ ይሰጡትና አላህ በዚህ እንዲጠቀም ያደርገዋል።

~ ወይም ነቢዩ ሙሀመድ صلى الله عليه وسلم አማላጅ ሆነውለት ከጌታው ምህረትን ይጠይቁለታል።

~ ወይም ሃያሉ አላህ በዚህች ዓለም ላይ [በተለያዩ መከራዎች] ይፈትነውና ኃጢኣቱን ያብስለታል።

~ ወይም በበርዘኽ [በቀብሩ ውስጥ ጥበት] እንዲሁም በሰዕቃህ صعقة [የሞት ጥሩንባ ሲነፋ ደንግጦ በሚወድቀው] ይፈትነውና በዚህም ኃጢኣቱን ያብስለታል።

~ ወይም በቂያማ ሜዳ ኃጢኣቱን የሚሸፍንለት በሆነ ሁኔታዋ ይፈትነዋል።

~ ወይም የአዛኞች አዛኝ የሆነው [አርሀሙ ራሂሚን] ያዝንለታል። [በዚህም ይምረዋል።]

በመሆኑም ከነዚህ አስሩ ያልተገጠመ ሰው ራሱን እንጂ ማንንም አይውቀስ።🍃🍂

🌱 مجموع الفتاوى(١٠/٤٥_٤٦ ) .
=========

27/04/1437🕑06/02/16
©ተንቢሃት