Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ለምትጎነጨው ውሃ እንኳን ቢሆን ከሰዎች ፈላጊ ሆነህ በቀረብካቸው ቁጥር፤ እነርሱ ዘንድ የሚኖርህም ክብር በዚያው ልክ ይወርዳል። »

~√ ከሊቃውንቶቻችን ፊቅህ √~

🌷📖🌷

« ለምትጎነጨው ውሃ እንኳን ቢሆን ከሰዎች ፈላጊ ሆነህ በቀረብካቸው ቁጥር፤ እነርሱ ዘንድ የሚኖርህም ክብር በዚያው ልክ ይወርዳል። »

ሸይኩል ኢስላም ኢብን ተይሚያ ረሂመሁላህ

” وَمَتَى احْتَجْتَ إلَيْهِمْ - وَلَوْ فِي شَرْبَةِ مَاءٍ - نَقَصَ قَدْرُكَ عِنْدَهُمْ بِقَدْرِ حَاجَتِكَ إلَيْهِمْ “
شيخ الإسلام إبن تيمية: رحمه الله
` ይገርማል

የተውሂድን ፍሬና ተፅዕኖ
በሁሉም መስክ እናያለን

ወደ ጌታህ በቀረብክ ቁጥር፣ ፀጋውን በከጀልክ ልክ፣ ሲሳዩን በለመንከውና ተስፋ ባሳደርክበት መጠን…

• ክብር ይጨምርልሃል
• ደረጃህን ከፍ ያደርገዋል

• ተወዳጅነትህን ያሳድጋል
• በሰው ዘንድም ያስከብረሃል

• የምትፈልገውንም ይሰጠሃል
• ከምትሰጋውም ይጠብቀሃል

• የተሟላ ዋስትና ያደርግልሃል
• ከምንም መውጫ ቀዳዳ ያበጅልሃል

• እውቀትህን ይጨምርልሃል
• ኃጢኣትህን ይሰርይልሃል

• መልካም ተግባሮችህን ያነባብርልሃል
• ይበልጥ ያቀርበሃል

ሰዎችን በተለማመጥክ፣ በከጀልክና በለመንክ ቁጥር ግን

• ይሰለቹሃል፣ ይንቁሃል
• ይኮፈሱብሃል
• ያዋርዱሃል
• ይመፃደቁብሃል
• ይተቹሃል፣ ያሙሃል

ስለዚህም ሰዎችን መለመኑም መከጀሉም ባልተወገዘበት ሁኔታ ከነርሱ መጠበቁ መጠየቁ ይህን ያህል ክብርን የሚያወርድ ከሆነ የተከለከለውና ለአላህ ብቻ የሚገባውስ ወዴት ይወስድ ይሆን

እነሆ የተከለከለውን ክጃሎትና ልመና እንዲሁም ገለፃን ለምሳሌነት እንመልከት:

~ እገሌ ወሊይ ድረስልኝ
~ የዚያ አድባር አንተ ጠብቀኝ
~ ቆሌዬ እንዳይደፋኝ

~ እነሸህ በርስዎ መጀን
~ ውቃቢዬ ተቆጣብኝ
~ ከራማቸውን ፈራሁኝ

~ አንቱ እንትና ጀነትን አደራ
~ እርስዎ እያሉ ምንም አይነካኝ
~ አማና ብያለሁ እጄን ያዙኝ

~ ከቀዳእ ከቀደር በርስዎ አመለጥኩኝ

~ ሁሉን አዋቂ ኖትና የትም ጠብቁኝ… ………

የመሳሰሉ ለፈጣሪ አምላካችን ብቻ የሚገባውን ከፍጡራን መጠበቅ ወይም እነሱን በዚህ መልክ መግለፅ እጅግ አስከፊ አዘቅት ውስጥ የሚከት የባእድ አምልኮ የሽርክ መገለጫ ቃላቶች ናቸው።

ይኸ ኢስላምን የሚፃረርና እምነትህን የሚያፈርስ በመሆኑ ሙሉ በመሉ መራቅ ይገባሃል።

🌴 🌴

የሚቻለውንም የመተጋገዝ በር ከማንኳኳትህ በፊት

~ ተጣጣር ራስህን ቻል
~ ከሰው አትከጅል

~ ለመቀበል ሳይሆን
ለመስጠት ፍጠን
~ ተፅዕኖ ፈጣሪ ሁን

~ ዱብ ዱብ በል አሳድግ ራስህን
~ ከማያልቅበቱ ጠይቅ
ፈጣሪህን

~ ባለህ ተብቃቃ በልክህ ኑር
~ የሪዝቅ በር ሰፊ ነውና
ቀያይረህም ሞክር።

ወደ ሰዎች የግድ ያደረሰህም ጉዳይ ሲገጥምህና መልካም አቀባበልና ጥሩ ምላሽ ሲሰጡህም ለድጋፋቸው ቦታ ስጥ ። አመስግናቸው። ወደ ጌታህም መልካም ዱዓእን ኣድርግላቸው።
•••••••• 🌴🌴🌴 ••••••••
« ለምትጎነጨው ውሃ እንኳን ቢሆን ከሰዎች ፈላጊ ሆነህ በቀረብካቸው ቁጥር፤ እነርሱ ዘንድ የሚኖርህም ክብር በዚያው ልክ ይወርዳል። »

ኢብን ተይሚያ ረሂመሁላህ
_________
📝احمد سيرة abufewzan
31Jan15
10 Rabi'e al-sani 1436