Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ጥያቄ፦ አንዲት ሴት ጂልባባዋን መሬት ላይ እስኪጎተት ማስረዘም ከሒጃብ መስፈርቶች ይቆጠራልን?


ጥያቄ፦
አንዲት ሴት ጂልባባዋን መሬት ላይ እስኪጎተት ማስረዘም ከሒጃብ መስፈርቶች ይቆጠራልን?
መልስ፦
ይህ ከላይ የተጠቀሰው ነገር መስፈርት የሚሆነው፦
ይህ ረጅም ልብስ ወይም ጂልባብ ካለ ሱሪ ፣ ካልሲ እና ሌሎችም የሴቷን ባት እና ተረከዝ የማይሸፍኑ ነገሮች ባሉበት ጊዜ ነው መስፈርት ሆኖ የሚቀርበው።
ሴቶች ዛሬ ዛሬ እንደሚለብሱት ፦
ካልሲ ምናልባትም ረጅም ሱሪ እና የመሳሰሉትን የምትለብስ ከሆነ ጂልባቡ መርዘም ሸርጥ አይደለም።
የአላህ መልክተኛ (ሰለሏሁ አለይሂ ወሰለም) ጅልባብ እንዲረዝም ያዘዙበት ሁኔታ አለ፣
ያ ግን ከሴቶች አውረት እንደ ባት እና ተረከዝ ያሉ ክፍሎች እንዳይገለጥ ከመስጋት የተነሳ ነው።
እነዚህ አካሏ በረጅም ጅልባብ ወይም በካልሲ፣ በልብስ የተሸፈነ ከሆነ ከመሬት ላይ እንደ ጭራ መጎተት አስፈላጊ አይሆንም።
【ሸይኽ አልባኒ :ሲልሲለቱ አልሁዳ ወ ኑር ካሴት ቁጥር (565)】
አሳሳቢ ፈትዋዎች ለሙስሊሟ
http://telegram.me/muslimua