Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ነቢዩ መሐመድ እንደተናገሩት፣ በጽሕፈትም እንደሚገኘው ጥቁር አዝሙድ ከሞት በቀር ለሁሉም በሽታዎች ፈዋሽነት አለው፡፡



ነቢዩ መሐመድ እንደተናገሩት፣ በጽሕፈትም እንደሚገኘው ጥቁር አዝሙድ ከሞት በቀር ለሁሉም በሽታዎች ፈዋሽነት አለው፡፡ ‹‹ይህቺጥቁር ፍሬ አትለያችሁ፡፡ በውስጧ ከሞት በቀር ለሁሉም በሽታዎች ፈውስ ይዛለች፡፡››
ከዚህ በፊት በኢትዮጵያ ምግብ ጥናት ድርጅት አማካይነት በእጸዋት ተመራማሪዎቹ በአቶ ዳዊት አበበ፣ አስፋው ደበላ፣ ቀልቤሳ ዑርጋና ዶ/ር መድኅን ዘውዱ አቀነባባሪነት ተጠንተው ለሕትመት መብቃታቸው ይታወቃል፡፡ እጸዋቱን ለሕክምና ተግባር ለማዋል ሁሉም አስተዋጽዖ ማድረግ ይጠበቅበታል፡፡ የዚህ ጽሑፍ ዓላማ የተባረከውን የጥቁር አዝሙድ ጠቃሚነቱን ከምግብም ሆነ ከሕክምና አንፃር ዕውቀቴን ለማጋራት ነው፡፡
ይህም ሆኖ የጥቁር አዝሙድ አወሳሰድ የዘመናዊውን ሕክምና ይተካል ማለቴ ሳይሆን፣በተጓዳኝ ማንኛችንም ኢትዮጵያውያን የምንጠቀምባቸውን፣ የምንመገባቸውን ፍራፍሬዎችንም ሆነ ቅመማ ቅመሞች ከሕክምና አንፃር ያለውን ሁኔታ በመለዋወጥ እንድንማማር ይጠቅማል ብዬ ጽሑፌን ሳበረክትከአክብሮት ጋር ነው፡፡
1ኛ. ለእርጋታ
አንድ የሾርባ ማንኪያ ትክክለኛውን የጥቁር አዝሙድ ዘይት በባዶ ሆድ መውሰድ ቀኑን ሙሉ መረጋጋትና ንቃት ያጎናጽፋል፡፡ እንዲሁም ከራት በኋላ ወደ መኝታ ከማምራት በፊት አንድ የሾርባ ማንኪያ ትክክለኛውን የጥቁር አዝሙድዘይት መውሰድ ለሊቱን ሙሉ የተረጋጋና ደስ የሚያሰኝ እንቅልፍ ያስገኛል፡፡
አንድ ትልቅ የሾርባ ማንኪያ የጥቁር አዝሙድ ዘይት አንድ ሲኒ ቡና ውስጥ ጨምሮ መጠጣት፡፡ የአእምሮ ጭንቀትን አስወግዶ መረጋጋትን ያስገኛል፡፡
2ኛ. ለሳልና ለአስም
በዘይቱ ደረትንና ጀርባን ማሸት በቀን ሦስት የሾርባ ማንኪያ መጠጣት፣ ሁለት ማንኪያ በሙቅ ውኃ ውስጥ ጨምሮ እንፋሎቱን መሳብ ይረዳል፡፡
3ኛ. የመጫጫንና ስንፍናን ለማስወገድ
አንድ የሾርባ ማንኪያ ዘይት በአንድ ብርጭቆ ብርቱካን ጭማቂ ውስጥ ጨምሮ ጧት ጧት ለአሥር ተከታታይ ቀናት መውሰድ ልዩነቱን ያገኙታል፡፡
4ኛ. የማስታወስ ችሎታንና ፈጣን የግንዛቤ አቅምን ለማጎልበት
አንድ የሾርባ ማንኪያ የጥቁር አዝሙድ ዘይት፣ 100 ሚሊ ሊትር የፈላ ናእናእ (Nena) ተክል ጋር ተቀላቅሎ ለአሥር ተከታታይ ቀናት መውሰድ፡፡
5ኛ. ለኩላሊት ጠጠር (የስኳር ሕመም ያለባቸው ማርን መተው ነው)
ሩብ ኪሎ ጥሬ ጥቁር አዝሙድ፣ ሩብ ኪሎ ንጹሕ ማር ማዘጋጀት፡፡ ጥቁር አዝሙድን በሚገባ መፍጨትና ከማር ጋር ቀይጦ በሚገባ ማዋሀድ፡፡ ከዚያም ሁለት ማንኪያ ከቅይጡ ቀንሶ በአንድ ብርጭቆ የሞቀ ውኃ ውስጥ ጨምሮ በጥቁር አዝሙድ ዘይት አንድ ሻይ ማንኪያ በማከል በባዶ ሆድ መጠጣት፡፡
6ኛ. ለብሩሕ ገጽና ለውበት
አንድ ማንኪያ ጥቁር አዝሙድ ዘይት አንድ ማንኪያ የወይራ ዘይት ጋር አዋሕዶ ፊትን መቀባት አንድ ሰዓት ቆይቶ በውኃና በሳሙና መታጠብ ልዩነቱን በጉልህ ያገኙታል፡፡
7ኛ. ከበሽታ ሁሉ ለመጠበቅ
አንድ የሾርባ ማንኪያ የጥቁር አዝሙድ ዘይት ከአንድ ማንኪያ ማር ጋር አዋሕዶ ያለማቋረጥ ጧት ጧት መውሰድ በሕይወት ዘመንዎ ሙሉ ጤነኛና የሐኪም እርዳታ የማያሻው ሰው ይወጣዎታል፡፡
8ኛ. በጭንና ጭን መካከል የቆዳ መቆጣት ሲያጋጥም
በቅድሚያ አካባቢውን በውኃና በሳሙና በሚገባማጠብ፣ ቀጥሎ በሚገባ ማድረቅና በጥቁር አዝሙድ ዘይት ማታ ቀብቶ ማደርና ለሦስት ተከታታይ ቀናት ይህንኑ መፈጸም፡፡ ከመጀመሪያው ቀን ጀምሮ ውጤቱን ያዩታል፡፡
9ኛ. ለልብና ለደም ሥሮች ሕመም
የጥቁር አዝሙድ ዘይት ከትኩስ መጠጥ ጋር በተከታታይ መውሰድ ስብን ለማሟሟትና የደም ሥሮችን ለማስፋት ይረዳል፡፡
10ኛ. ለለምጽና ለመሳሰሉት
ተጠቂውን የሰውነት ክፍል በቱፋሕ (ፖም) ወይም አፕል ኮምጣጤ ማሸት ከዚያም የጥቁር አዝሙድ ዘይት ለ15 ቀናት መቀባት፡፡
11ኛ. ለቁርጥማት ሮማቲዝምና የጀርባ ሕመም
የተወሰነ የጥቁር አዝሙድ ዘይት በጥቂቱ በማሞቅ የታመመውን አካል አጥንትን ዘልቆ እስኪሰማ ድረስ በዘይቱ በደንብ መታሸት በቀን ሦስት ጊዜ አንድ የሾርባ ማንኪያ ዘይት መጠጣት፡፡
12ኛ. ለራስ ምታት
በጥቁር አዝሙድ ዘይት ግንባርንና በጆሮ አካባቢ ያለውን አካል ማሸት ለሦስት ተከታታይ ቀናት አንድ ሻይ ማንኪያ የጥቁር አዝሙድ ዘይት በባዶ ሆድ መጠጣት፡፡
13ኛ. ለጨጓራና ለአሲድ
አንድ ኩባያ ወተት የአንድ የሾርባ ማንኪያ የጥቁር አዝሙድ ዘይት በቀን ሦስት ጊዜ መውሰድ፡፡ ከሦስት ቀናት በኋላ በሽታው ሙሉ በሙሉ ይወገዳል፡፡
14ኛ. ለራስ ማዞርና ለጆሮ ሕመም
አንድ ጠብታ የጥቁር አዝሙድ ዘይት ጆሮ ውስጥ መጨመር በሻይ መልክ አዘጋጅቶ መጠጣት፡፡
15ኛ. ለቆዳ መቀረፍ
በዚህ አይነቱ ሕመም የተጠቃው የአካል ክፍል በጥቁር አዝሙድ ዘይት መቀባት ሕመሙ እስኪወገድ ድረስ ይህንኑ መቀጠል፡፡
16ኛ. ለቡግር
ጥቁር አዝሙድ አድቅቆ መፍጨት የሰሊጥ ዘይትና አንድ ማንኪያ የስንዴ ዱቄት ጨምሮ በአንድነት መለወስ ማታ ማታ ተቀብቶ ማደርና ጠዋት ለብ ባለ ውኃና በሳሙና መታጠብ፡፡
17ኛ. ለስብራት አፋጣኝ ጥገና
የምስርና የሽንኩርት ሾርባ፣ ቅቅል እንቁላል፣ አንድ ትልቅ ማንኪያ የደቀቀ ጥቁር አዝሙድ በአንድነት ቀላቅሎ ቢያንስ አንድ ቀን ወስዶ በቀጣዩ ቀን አርፎ እንደገና በሁለተኛው ቀን መውሰድ፤ ስብራቱ የዘመናዊ ሕክምና በጀሶ ከታሰረ በኋላ በአቅራቢያ ያለውን አካል በጥቁር አዝሙድ ዘይት ማሸት፤ እስሩ ከተፈታ በኋላ ደግሞ ለብ ባለ የጥቁር አዝሙድ ዘይት በየቀኑ ማሸት ነው፡፡
18ኛ. ለጠባሳና ለመሳሰሉት
አንድ እፍኝ ጥቁር አዝሙድ በሚገባ ማፍላት የተጎዳውን አካል ማጠብና ለሩብ ሰዓት በተዘጋጀው ፍል ጥቁር አዝሙድ ውስጥ መንከር፡፡ አካሉን ማንቀሳቀስ፡፡ ሳይሸፈን አድካሚ እንቅስቃሴ ሳያደርጉ መቆየት፡፡ ከመኝታ በፊት በየቀኑ ይህን መደጋገም፡፡
19ኛ. ለደም ብዛት
ትኩስ መጠጥ ባሰኘው መጠን ጥቂት የጥቁር አዝሙድ ዘይት ጠብታዎችን ጨምሮ መጠጣት፡፡ በተጨማሪም ገላውን ጥቁር አዝሙድ በመቀባት ቢያንስ በየሳምንቱ አንድ ጊዜ የፀሐይ ሙቀት ቢወስዱ ምንኛ ጥሩ ነበር፡፡
20ኛ. ለኩላሊት ኢንፌክሽን
የጥቁር አዝሙድ ዱቄት በወይራ ዘይት ለውሶ ሕመም በሚሰማበት ቦታ መለጠፍ፤ በተጨማሪም አንድ ማንኪያ የጥቁር አዝሙድ በየቀኑ በባዶ ሆድ ለአንድ ሳምንት ጥሬውን መቃም፣ ከዚያ በኋላ ኢንፌክሽኑ ይወገዳል፡፡
21ኛ. ለሐሞት ከረጢት
አንድ ማንኪያ የጥቁር አዝሙድ፣ ሩብ ማንኪያ የተፈጨ ሬት፣ አንድ ኩባያ ማር ጋር መለወስና ጧትና ማታ መብላት፡፡ ፊትዎ ቅላት እስኪያሳይና ችግሩ እስኪወገድ ድረስ ይህንኑመፈጸም፡፡ በየዕለቱ በባዶ ሆድ አንድ ሲኒ የወይራ ዘይት መጠጣት አይርሱ፡፡
22ኛ. ለልብና ለደም ዝውውር ችግር
የልብ ሕመምተኛ ሰው በማናቸውም ወቅት እንደ ምግብም፣ እንደመጠጥም እንደአስፈላጊነቱ መውሰድ ይኖርበታል፡፡
23ኛ. ለትውከት
ጥቁር አዝሙድ ከቅርንፉድ ጋር በደንብ ማፍላት ማጣፈጫዎች ሳይጨምሩ በቀን ሦስት ጊዜ መጠጣት፡፡ ሁለተኛ ዙር መጠጣት አያስፈልግም፡፡
24ኛ. ለቃርና ለመሳሰሉት
የተወሰኑ የጥቁር አዝሙድ ቅባት ጠብታዎች በአንድ ኩባያ ትኩስ ወተት ውስጥ ጨምሮ በማር አጣፍጦ መጠጣት፡፡ የቃር ስሜትዎ እንዳልነበር ሆኖ ይጠፋል፡፡ በእንግሊዘኛ (Lettuce) የተሰኘውን ተክል በብዛት መብላትንም አይዘንጉ፡፡
25ኛ. ለዓይን በሽታ
በጥቁር አዝሙድ ዘይት በዓይንና በጆሮ መካከል ያለውን የሰውነት አካል ከመኝታ በፊት ማሸት በማናቸውም ትኩስ መጠጥ ውስጥ አልያም የሥራ ሥር ጭማቂ እንደ ካሮት የመሳሰሉት ውስጥ ጥቂት ጠብታዎች ጨምሮ መጠጣት ነው፡፡
26ኛ. የምግብ ፍላጎትን ለማሳደግ
ከምግብ በፊት ጥቂት ደቂቃዎች ቀደም ብሎ አንድ ማንኪያ ጥቁር አዝሙድ ቅመሙን በጥርሶችዎ ማድቀቅ፣ ከዚያም ጥቂት ኮምጣጤ ጠብታዎች የተቀላቀለበት አንድ ስኒ ቀዝቃዛ ውኃ ያወራርዱት፡፡
27ኛ. ለቅማልና ለቅጫም
ጥቁር አዝሙድ አድቅቆ መፍጨት በኮምጣጤ ለውሶ ለመታሻ በሚያገለግል መልኩ ማዘጋጀት ፀጉርን ተላጭቶ መቀባት አሊያም ቆዳው ድረስ ዘልቆ እንዲገባ ማድረግና ለሩብ ሰዓት ለፀሐይ ማጋለጥ፡፡ ከአምስት ሰዓታት በኋላ መታጠብ፡፡ ለአንድ ሳምንት ያህል ይህንኑ ደጋግሞ መፈጸም፡፡
28ኛ. ለጥርስ፣ ለቶንስልና ለጉሮሮ ሕመም
የጥቁር አዝሙድ አፍልቶ መጉመጥመጥና ለጉሮሮችግር እጅግ ጠቃሚ ነው፡፡ አንድ ማንኪያ አዘጋጅቶ ለብ ባለ ውኃ ውስጥ ጨምሮ መጠጣትና በዘይቱም የጉሮሮን ውጫዊ አካል መቀባት በውስጥ ደግሞ መንጋጋን መቀባት፡፡
29ኛ. ከደም ላይ ኮሊስትሮን (ስብን) ለማስወገድ
አንድ ማንኪያ የጥቁር አዝሙድ ዱቄት አንድ ማንኪያ የእኸሊ ቅጠል ከአንድ ስኒ ንጹሕ ማርጋር ለውሶ በባዶ ሆድ መብላት፡፡
30ኛ. ለሽንት መታቀብ ችግር
ከእምብርት በታች ያለውን የሰውነት አካል በጥቁር አዝሙድ ቅባት ከመኝታ በፊት ማሸት፡፡ አንድ ማንኪያ የጥቁር አዝሙድ ዘይት በአንድ ኩባያ ውኃ አፍልቶ በማር አጣፍጦ ከመኝታ በፊት በእለቱ መጠጣት፡፡
31ኛ. ፊት ላይ እንደ ቡጉር ክብ ሆኖ ለሚወጣ አተርን ያክል ጠጣር ነገር (WATER)
በሽታ በሽታው የሰፈረበትን አካባቢ በረጅላ (Purslane) ተክል በሚገባ ማሸት ከዚያም የጥቁር አዝሙድ ዘይት 15 ቀናት መቀባት በቀን ሦስት ጊዜ አንድ አንድ ማንኪያ የጥቁር አዝሙድ ዘይት መጠጣት፡፡
32ኛ. ለሚያስነጥስ
ከባሕር ዛፍ የተጨመቀ ዘይት 40% ከጥቁር አዝሙድ ዘይት ጋር ደባልቆ በሁለቱም አፍንጫ በቀን ሦስት አራት ጊዜ ጠብታ ማድረግ ነው፡፡
ስለ ጥቁር አዝሙድ በዝርዝር መረዳት ለሚፈልግ በ http:www.Nigella-sativa-research.com/ማግኘት ይችላል፡፡