Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

እንግዳው ሆይ አይዞህ ቀና በል የዘመናችን ሙጀዲድ ሸይኹል አልባኒ (ረሒመሁላህ) እንዲህ ይሉሃል :–

Abu Aisha
 
‪#‎እንግዳው_ሆይ_አይዞህ_ቀና_በል‬ !!!
የዘመናችን ሙጀዲድ ሸይኹል አልባኒ (ረሒመሁላህ) እንዲህ ይሉሃል:–
« ... ስለ ተውሒድ ስትናገር የሽርክ ሰዎች ይቃወሙሃል።
ስለ ሱና ስታወራ የቢድዓ ሰዎች ይቃወሙሃል።
ስለ ማስረጃና ማረጋገጫ ስትናገር የመዝሃብ (የቡድንተኛ አካሄድ) ጭፍን ተከታዮች እና መሃይማን ይቃወሙሃል።
ስለ በመልካም ነገር (ሙስሊም) መሪዎችን ስለመታዘዝ፣ ለነርሱ ዱዓ ስለማድረግ፣ እነርሱን (መሪዎችን) (በግልና እና በድብቅ) ስለመምከር፣ እና ስለ አህለል ሱንናህ ዓቂዳ ስትናገር ኸዋሪጆች (ከሙስሊም ጀመዓ ለመጀመሪያ ጊዜ አፈንግጠው የወጡ፣ በጅምላ ሙስሊሙን የሚያከፍሩ፣ ሙስሊሙን የሚገድሉ የቢድዓ ቡድንተኞች) እና ሌሎች አፈንጋጭ ቡድንተኞች ይቃወሙሃል።
ስለኢስላም እና በእለት ተእለት ኑራችን (ኢስላምን) ስለመተግበር ስትናገር ሴኩላሪስቶች፣ ሊበራሊስቶች (ፀረ–እምነት ቡድኖች) እና እነሱን የመሳሰሉ ዲናችንን ከእለት ተእለት ኑራችን መለየት የሚፈልጉት ይቃወሙሃል።

አህለል ሱንናህ እጅጉን ባይተዋሮች (እንግዶች) ናቸው። እነዚያ (የጥመት) ቡድኖች በእኛ (በአህለል ሱናዎች) ላይ በሚቻላቸው ሁሉ ጦርነት አውጀዋል። በድምፅ መሳሪያ (በራዲዮ፣ በቴሌቪዥን)፣ በፅህፈት (በጋዜጣ፣ በኢንተርኔት) ጦርነት አውጀውብናል። ቤተሰብና ጓደኛ ሁሉ ሳይቀር በዚህ እንግዳ (በቁርአንና በሱና የሚተዳደረውን) ላይ ጦርነትን አውጀዋል።
ሆኖም ይህ በእንዲህ እንዳለ እኛ ግን በዚህ ባይተዋርነታችን ደስተኞች ነን። እንኮራበታለንም። ምክንያቱም የአላህ መልእክተኛ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም ባይተዋሮችን አወድሰዋቸዋልና።
የአላህ መልእክተኛ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል: –
“ ኢስላም እንግዳ ሆኖ ጀምሯል። እንደ ጅማሮውም እንግዳ ሆኖ ይመለሳል። ለእንግዶቹ ‘ጡባ’ (ጀነት ውስጥ የምትገኝ ዛፍ ወይንም መልካም ነገር) አለቻቸው።”
“እነርሱ (እንግዶቹ) እነማን ናቸው?” ተብለው በተጠየቁም ጊዜ የአላህ መልእክተኛ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለምም: –
“ሰዎች በተበላሹ ጊዜ (እራሳቸውን እና ሌሎችንም) ‪#‎አስተካካዮች‬ ናቸው።” ብለው መለሱ።»
[ሲልሲላህ አስሰሒሐህ 1273]