Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ኢኽዋኖች የተወገዘው ሙግትና ክርክርን በውይይት ሽፋን ለምን ይሁን ስራችን ብለው የተያያዙት?


ኢኽዋኖች የተወገዘው ሙግትና ክርክርን በውይይት ሽፋን ለምን ይሁን ስራችን ብለው የተያያዙት?
ሐቅ ላይ ያለ ሰው ሐቁን ለማስተላለፍ የሀቅ ምንጭ የሆነውን ቁራንና ሐዲስ በማስተማር ፤ በሀቅ ሰዎች የተፃፉትን ኪታብ በማስቀራት ብቻ ነው ፤ ሃቁን አውቆ የተቀበለ ሰው አልሃምዱሊላህ እምቢ ያለው ደሞ አላህ ያግራለት ይላሉ ። በመሰረቱ ሀቅን ተቀብሎ ኸይረኞች ሰዎችን ከበዛም የሚወደድና የሚፈለግ ነው ለዛም ነው ዳዕዋ የሚደረገው
ትምህርትም የሚሰጠው ፤ቢሆንም የሰው ቁጥር ማብዛቱ ዋነኛ የዳዕዋ አላማ ሳይሆነ ሐቅን ለሚፈለገው ሰው ማድረስ ነው ፤ ይህ ማለትም ያንን ሐቅ የተከተለ ሰው በጣም ቢያንሱም ሐቅን ከሐቅነቱ አያወጣውም አይጎዳውም ።
ከሀቅ ርቀው የባጢልን መንገድ የሚከተሉት የሚያሳስባቸው እነሱን የሚደግፉት የሰው ብዛት ማፈራት ብቻ ነው ። ያንን ለማሳካት የፈለጉትን መንገድ ይከተላሉ ለሽርክ ከለላ ይሰጣሉ ፤ ቢድዓን ሱና ያደርጋሉ ፤ ሱናን ቢድዓ ያደርጋሉ ፤ማዕሲያን(ጥፋትን ) ማዕሩፍ (መልካም ) ያደርጋሉ ፤ ማዕሩፍን (መልካምን) ማዕሲያ (ጥፋት ) ያደርጋሉ ። ባጢላቸውን ለሰው ለማድረስም ሆነ ለማስገንዘብ ፤ ውሸትን ፤ ትችትን ፤ ስድብን ፤ ሙግትን ይጠቀማሉ ። ቁጭ ብለው በተከታታይ ኪታብ የሚያስቀሩበት በቂ ግዜ የላቸውም ። ሙስሊሙን በትክክለኛ ኢስላማዊ እውቀት ማዳበር አይደለም ፍላጎታቸው ፤ ፍላጎታቸው ሙስሊሙ የማስረጃ ትውልድ ሳይሆን እነሱ የሚሰሩትን የሚያስተላልፉትን አሜን ብለው እንዲቀበሉ፤ የቁርዓንና ሐዲስ ተከታይ ሳይሆኑ የነሱን ተከታይ እንዲሆኑላቸው ነው ፤ ለዚህም ነው እነሱን የሚከተሉት የፈለከውን የቁርዓን አንቀፅና ሐዲስ ብታመጣላቸው የማይቀበሉት ።
በዚህ በፌስ ቡክና በወትስ አፕ ያሉት የነሱ ኡስታዝ ተብዬዎችም ፤ ተከታያቸውን ልባቸውን ለማረጋጋት ፤እነሱ ሀቅ ላይ መኖራቸው ለማረጋገጥ ፤ ሌላው ትክክል አለመሆኑን ለማስረዳት ፤ በውይይት ስም ወደ ተወገዘው ሙግትና ደረቅ ክርክር ሌላውን ሰው በመጋበዝ ፤( አያቹ መልስ ስለሌላቸው ይሸሻሉ ፤ ተመልከቱ መልስ መስጠት ሲያቅታቸው ) በማለት ሀቅነታቸው ሊመሰክሩ ይፈልጋሉ ። ለምን ይሁን?? እውን እነሱ ሀቅ ስለያዙ ሌላው እነሱን በክርክር የማይሸንፉ መሆናቸው ተከታዮቻቸውን ለማሳየት ነው? ።
በሙጉትና በደረቅ ክርክር እውነትን ውሸት ማድረግ ፤ ውሸትንም እውነት አድርጎ ማቅረብ ይቻላል ፤ ሆነ በሎ ሙግትን ይዞ የሚንቀሳቀስ ከላይ ከላይ ሁሌ አሸናፊ ሆነ ነው የሚታየው ለምን ሐቅ ግልፅ ቢሆንለትም ኒያው ሙጉት ስለሆነ ያንን ሀቅ የሚመልስበት ስልት ይፈልጋል እንጂ ለሀቅ ልቡን ስለማይከፍት ነው ። ለዚህም ነው ነቢያችን ሰለላሁ አልይሁ ወሰለም የተወገዘውን ሙግትን እንድንጠነቀቅ የመከሩን ። ለዚህም ነው የተወገዘው ሙግት የሰለፎቻችን መንገድ ያልሆነው ። ለዚህም ነው በአህሉሱና ወልጀማዓ ሙጉት የደዓዋ አደራረግ ስልት ተደርጎ ያልተወሰደው ።
~~~ ሙጉት ሲባል በሁለት ይካፈላል ~~~ ፤- ( የፈተቀደና የተወገዘ ።)
1. የተፈቀደ ሙጉት የሚባለው ፤( አንድን ሀቅ ላይ ያለ ሙስሊም ያንን ሀቅ ለማደረስ ያንን ሀቅ የሚቃረኑትና የማያምኑበት ሰዎችን ፤ ለነሱ ማስረጃ በማቅረብ በደዓዋ መልክ እነሱን ለማሳመን የሚደገግ ፍልሚያ ነው )
- ይህ ዓይነት ሙጉት በመተመለከተ አላህም በቁርዓኑ እንዲህ ይላል
(ادْعُ إِلَى سَبِيلِ رَبِّكَ بِالْحِكْمَةِ وَالْمَوْعِظَةِ الْحَسَنَةِ وَجَادِلْهُمْ بِالَّتِي هِيَ أَحْسَنُ) [النحل:125].
ወደ ጌታህ ተጣራ በጥሩ ምክርና ጥበብ በተሞላበት ፤ እነሱንም መልካም በሆነ መንገድ ተከራከራቸው "
- እንዲሁም በሱርቱ አል አንከቡት (وَلا تُجَادِلُوا أَهْلَ الْكِتَابِ إِلَّا بِالَّتِي هِيَ أَحْسَنُ إِلَّا الَّذِينَ ظَلَمُوا مِنْهُمْ) [العنكبوت:46].
- ነቢያችንም ሰለላሁ አሌይይሂ ወሰለም በሀዲሳቸው
وقال فيه النبي صلى الله عليه وسلم: "جاهدوا المشركين بأموالكم وأنفسكم وألسنتكم”.
" ሙሽሪኮችን በንብረታቸውና በነፍሶቻችሁና በምላሳቹ ተዋጋቸው "
በዚህ ዕይነት የሙጉት አይነት ነው ሰው ላይ ሁጃ ለማቆም ሐቅን ለማድረስ ሲባል ፍልሚያ የሚደረገው ። ለዚህም ነው ኢብኑ አባስም ከዋሪጆችጋ ሄዶ በማስረጃ አሳምኖዋቸው ወደ ሀቅ ከፊሉን የመለሱት ።
2. ሁለተኛው የተወገዘው ሙጉት ማለት ፤( በሚደረገው ውይይትና በሚቀርበው ማስረጃ ሀቅን ለመቀበል ሳይሆን ሆነ ብሎ የራሱን ፍላጎና አላምን ብቻ ለማሳካት ብሎ ሰውን የሚሞግት ነው ። )
ይህም የተወገዘው ሙጉት ብዙ ክፍሎች አሉት ከነዚህም ።
2.1 አንደኛው الجدال لطمس نور الحق (ትክክለኛውን ሐቅ ለማጥፋትና ለማጥለሸትና የሀቅሰዎችን ከሐቁ ለማዘናጋት ሲባል የሚደረጉ ሙግቶች ናቸው ።)
የዚህ ዓይነት ሙግት አላህ በቁርዓኑ እንዲህ በማለት ይኮንንነዋል ፡
- (وَإِنَّ الشَّيَاطِينَ لَيُوحُونَ إِلَى أَوْلِيَائِهِمْ لِيُجَادِلُوكُمْ) [الأنعام:121] ( ሼይጣኖች እንዲሞግታቹህ ዘንድ ወደ ጭፍሮቻቸው መልዕክት ያማስተላለፍ )
እንዲ አይነቶች ሰዎችንም እንዲህ በማለት በሱረኡል ጋፊር አላህ ይገልፃቸዋል ፡ (وَجَادَلُوا بِالْبَاطِلِ لِيُدْحِضُوا بِهِ الْحَقَّ فَأَخَذْتُهُمْ فَكَيْفَ كَانَ عِقَابِ) [غافر:5].
ጥመትን ይዞ ይሞገታሉ ፤ ሐቅን በሱ ለማሸነፍ ብለው ••."
= ወደዚኛው የሙግት አይነት ሰውን ከሚወስደው ምክንያት አንዱ በልባቸው ያኖሩት ኩራት መሆኑን አላህ እንዲህ በማለት ይገልፀዋል (إِنَّ الَّذِينَ يُجَادِلُونَ فِي آيَاتِ اللَّهِ بِغَيْرِ سُلْطَانٍ أَتَاهُمْ إِنْ فِي صُدُورِهِمْ إِلاَّ كِبْرٌ مَا هُمْ بِبَالِغِيهِ فَاسْتَعِذْ بِاللَّهِ إِنَّهُ هُوَ السَّمِيعُ الْبَصِيرُ) [غافر:56].
2.2 ሁለተኛው ፡ الجدال لإظهار المزية والتقليل من شأن الآخرين: ( ሐቅን ለመቀበልና ለመስጠት ሳይሆን ፤ ራሱን ለማላቅና የበላይ መሆኑን ለማሳየትና ሌሎችን ደሞ ዝቅ ተደርገው እንዲታዩ ለማደረግ የሚደረጉ ሙግቶች ናቸው )
- ይህን ዓይነት ሙግት ደሞ በጣም የከፋና ቡዙ ሰዎች የሚላበሱት አይነት ሙጉት ሲሆን ፤ ሰውን ወደ ጥመት የሚወስዳቸውና ፤ የጥመት ሰዎች ምልክት መሆኑን ነቢያችን ሰለላሁ አሌይሂ ወሰለም ኢብኑ ማጃህ ባወሩት ሃዲስና አልባኑ ሰሂህ ባሉበት እንዲህ ይላሉ፦
"ما ضل قوم بعد هدىً كانوا عليه إلا أوتوا الجدل".ثم تلا قوله تعالى: (مَا ضَرَبُوهُ لَكَ إِلَّا جَدَلاً بَلْ هُمْ قَوْمٌ خَصِمُونَ) [الزخرف:58] ። ሰዎች ትክክለኛ መንገድ ከያዙ ቦሃላ አይጣመሙም ፤ ሙጉት ወስጥ እስካልገቡ ድረስ "
_እንዲህ አይነቶች ሰዎችንም አላህ የማይወዳቸው ሰዎች መሆናቸው ነቢያችን ቡኻሪ በዘገቡት ሐዲሳቸው እንዲ ይላሉ ፡ "إن أبغض الرجال إلى الله الألدُّ الْخَصِم". (البخاري" በአላህ ዘንድ እጅጉ የተጠላ ሰው በሙግት ድንበር የሚያልፍ ነው "
- በእንደዚህ ዓይነት ባህሪ የተላበሱት ደሞ የአላህ ቁጣ በነሱ ላይ እንደሚወርድ ነቢያችን ሰለላሁ አሌይሂ ወሰለም ኣቡ ዳውድ በዘገቡት አልባኒ ሰሂህ ባሉት ሐዲሳቸ ችንዲህ ይላልይ "ومن خاصم في باطل وهو يعلمه لم يزل في سخط الله حتى ينزع". (أبو داود وصححه الأباني). "አንድ ሰው በባጢል በሆነ ነገል ላይ ሆነ ብሎ የሚሞግት ሰው ፤ በአላህ ቁጣ ስር ነው ያለው ከዛ ድርጊቱ እስካልተመለሰ ድረስ "
- ነቢያችን ሰለላሁ አሌይሂ ወሰለም እንዲህ አይነት ሙግትን መተው በታም በሰው ላይ ስለሚከብድ ፤ ይህንን ደሞ ነፍሲያውን ተቆጣጥሮ የተወ ሰው እንዲህ በማለት ምንዳውን ይናገራሉ ፡
"أنا زعيم بيت في ربض الجنة لمن ترك المراء وإن كان محقًا". (أبو داود وحسنه الألباني في السلسلة الصحيحة).
2.3 ሶስተኛው الجدال لاغتصاب حقوق الناس ( (የሰውን ሐቅ ለመውሰድ በውሸት የሚሞግት )
ሌላው አፀያፊው የሙጉት አይነት የሰውን ንብረት ሆነ የሰውን ሐቅ ለመውሰድ ሲል በተለያዩ መልክ ምላሱን በማጣፈት ሆነ በመዋሸት የሱ ያልሆነውን የኔነው በማለት ሰውን መዘለም ሲሆን ይህን ዓይነት ሙጉት ነቢያችን ሰለላሁ አሌይኢ ወሰልም እንዲ በማለት ተናግረዋል "إنما أنا بشر، وإنكم تختصمون إلي، ولعل بعضكم أن يكون ألحن بحجته من بعض، فأقضي له على نحو ما أسمع، فمن قضيت له بحق أخيه شيئا فلا يأخذه، فإنما أقطع له قطعة من النار". ( رواه البخاري).
- እነዚህን የተወገዙትን የሙጉት አይነቶችን ለመጠንቀቅ ሲባል ፤ በዚህ አይነት ሙጉት መሰረት አድሮ የሚንቀሳቀሱትን ሰዎች ለመራቅና ከነሱ ጋር ላለመከራከር ሰሃቦችና የአህሉል ሱና ኢማሞች ከፍተኛ ጥንቃቄም ሆነ ማስጠንቀቂያ ሰተው ነበር ፤ ከነዚህም ፡
وقال ابن عباس: "كفى بك إثمًا ألا تزال مماريًا”.
ኢብኑ አባስ " አንድ ሰው በባጢል በሆነ ነገር ላት ሙጉት መፍጠሩ ብቻ ለሓጥያት ይበቀዋል "
وقال الأوزاعي: إذا أراد الله بقوم شرًا ألزمهم الجدل ومنعهم العمل.
ኢማሚ አውዘኢ " አንድ ሰዎች አላህ ለነሱ መጥፎ ነገር ከፈለገላቸው ሙጉት ውስጥ ችንዲገቡና ከስራ እንዲዘንጉ ያደርጋቸዋል "
وقال الشافعي: المراء في الدين يقسِّي القلب ويورث الضغائن.
ኢማሙ ሻፊኢ ፡ በዲን ሙጉት መፍጠር ቀልብን ያደርቃል ፤ ጥላቻን ያወርሳል "
በመጨረሻም እነዚያ በፌስቦክና በዋትስ አፕ ፤ መድኽሊዎች ከኛ ጋር ከመወያየት ይሸሻሉ የሚሉት ኢኽዋኖች ፡ የነሱ የሙጉት አይነት የተወገዘው ሙጉት ነው ። ለምን እና እንዴት ተብሎ ሊጠየቅ ይችላል መልሱ እንዲህ ነው ። እነዚህ ሰዎች በፌስክም ሆነ በሌላ ቦታ የሚያስተላልፉት መልዕክትና አቋማቸው ግልፅ ነው ። አአህሉል ሱና ወልጀማዓ በአንድ ድምፅ ያፀደቁትን ነጥቦችን የሚፃረሩና የሚዋጉ መሆናቸው ነው ፤ ለምሳሌ ፡ በሙስሊም መሪ ላይ ማመፅን ዙሪያ በተመለከት የተሳሳተና የኽዋሪጃችን አቋምን የሚደግፉና ወደዛ መጣረታቸው ፤የተለያዩ ጀማኣዎች ማቋቋሙ የተፈቀደና የተቋቋሙትንም ( እንደነ ኢኽዋኖች ) ከነሱ ሲከላከሉና የነሱን የተበከለውን አስተሳሰብን ሲያሰራጩና ሲያምኑበት፤ በተደጋገቢ በሚለቁት ፁሁፉና ድምፅ የመሰከሩ ሆነው እነዚህና የመሳሰሉት በርካታ መሰረታዊ ነጥቦች ላይ ጥመታቸው ሲያሰራጩ የከረሙት ነበሩ ፤ እነዚህን ነጥቦች በሙሉ በትክክለኛ ማስረጃ መልስ ተሰቶቸው ነበር ፤ ተመልሰው ያንን የተሰጣቸውን ምላሽ ለመመልሰ ያደረጉት ጥረትና አመላለሳቸው ሁሉ ለተመለከተ ሰው ከነሱ ጋር ፊት ለፊት መከራከር ማለት ቀጥታ ወደ ተወገዝው ሙጉት መግባት መሆኑን አላህ ቀልቡን ለሀቅ ከከፈተ ሰው የሚሰወር አይደለም ። ለዚህም ነው እነሱ በእንወያይ መልክ ወደ ሚጠሩ ከተወገዘ ሙጉት የምንርቀው እንጂ ሃቅ እነሱጋ ሆኖ እነሱ ለሚጠይቁን ጥያቄ መልስ አተን አይደለም።
አላህ ሁላችንም በሐቅ ላይ አኑሮን ከሐቅ በሐቅ የምንከላከል አላህ ያድርገን ።