Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

እጅግ ምርጥ የሆነ አባባል!!

����እጅግ ምርጥ የሆነ አባባል!!
"አንተ ዩኑስ ሆይ!ከመቶ በላይ በሆኑ ርዕሶች ተስማምተን እንዴት አንዲት ርዕስ ብቻ እኔና አንተን ትለያየናለች?!"
የኢማሙ ሻፊኢይ (ረሂመሁላህ) ተማሪ የነበሩት ዩኑስ ኢብኑ አብዱል አዕላ ኡስታዙ(ኢማም መሐመድ ኢብኑ ኢድሪስ አሻፊዒይ) መስጂድ ውስጥ እያስተማሩ ሳለ በአንዲት " መስኣላ " ቅርንጫፋዊ ርዕስ ላይ ከኡስታዙ ጋር አልተሰማም ነበርና ተናዶ ከተቀመጠበት ብድግ ብሎ ትምህርቱን አቋርጦ ወደ ቤቱ ሄደ።
ለሊት በሆነም ጊዜ የቤቱ በር ተንኳኳ።
ዩኑስ ፈጥን ብለው፦"ማነው? በር ላይ ያለው።" አሉ።
በሩን ያንኳኳው ሰውም፦"መሐመድ ኢብኑ ኢድሪስ" አለ።
ዩኑስም፦" ከሻፊኢይ ውጭ ስሙ መሀመድ ኢብኑ ኢድሪስ ተብሎ የተሰየመን ለማስታወስ ጣርኩ!!"
በሩን ሲከፍቱ፦ ያ ሰው ኢማሙ ሻፊኢይ ሆኖ ሲያገኙ ያልጠበቁት ነገር ሆኖባቸው ተገረሙ!!
ኢማሙ ሻፊዒይ፦"አንተ ዩኑስ ሆይ!ከመቶ በላይ በሆኑ ርዕሶች ተስማምተን እንዴት አንዲት ርዕስ ብቻ እኔና አንተን ትለያየናለች?!"
በሁሉም የኺላፍ አጀንዳ ላይ የራስህን አቋም ብቻ ትክክል በማለት ለራስህ ድጋፍ አትስጥ!
አንዳንዴ ልቦችን የራስህ ለማድረግ መጣር ለግልህ ራዕይ ድገፍ ከመስጠት ይበልጣል!!
በመንገድህ ስትጓዝ ለማለፍ ብለህ የገነባህውን ድልድይ አፈራርሰህ አትሂድ፣ምናልባትም ከዕለታት አንድ ቀን ስትመለስ ያስፈልግህ ይሆናል!!
ሁሌም ቢሆን ስሕተትን ጥላ ተሳሳችን አትጥላ!!
በሙሉ ልብህ ወንጀልን ጥላ፣ነገር ግን ወንጀለኛን ይቅር በል፣እዘንለትም!!
አንድን ንግግር እርምት ስጥ፣ ነገር ግን ተናጋሪውን አክብር!!
ምክንያቱም አላማችን በሽታን መዋጋት እንጂ በሽተኛን መግደል አይደለምና።

በጣም ምርጥ አባባል…
በተወሰኑ ርዕሶች ላይ ከማንስማማቸው ወገኖች ጋር እነዚህን አባባሎች ሂደታችንና ስልታችን አድርገን ብንይዝ ኖሮ…
በሕይወታችን ውስጥ የሚገጥሙን አባዛኛው ችግሮች ይቀረፉ ነበር።
ከዶ/ር ሸይኽ አቡበከር ያሲን ሐሺዲይ የቴሌግራም ቻናል ስርጭት ከአረብኛው ወደ አማርኛ የተወሰነ ማሻሻያ ተደርጎ የቀረበ።
��