Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ጥያቄ፦ "የሐሳብ ነፃነት" ሲባል እንሰማለን እናነባለን። ይህ ለእምነት ነፃነት ጥሪ ማድረግ ነው። እርሰዎ በዚህ ላይ ምን ሐሳብ አለዎት? ሸኽ መሐመድ ኢብኑ ሷሊህ አል-ዑሰይሚን ረሒመሁላህ

December 30, 2015 ·


ጥያቄ፦ <<የሐሳብ ነፃነት>> ሲባል እንሰማለን እናነባለን። ይህ
ለእምነት ነፃነት ጥሪ ማድረግ ነው። እርሰዎ በዚህ ላይ ምን
ሐሳብ አለዎት?

መልስ፦ በዚህ ላይ የምንሰጠው ሐሳብ፦ ሰው የእምነት ነፃነት
እንዲኖረው የሚፈቅድና የፈለገውን ሃይማኖት ሊከተል
እንደሚችል የሚያምን ሰው ካፊር ነው። ማንኛውም ሰው
ከኢስላም ውጭ ሌላ ሃይማኖት ሊከተል ይችላል የሚል እምነት ያለው ሰው ካፊር ነው።
እነደዚህ አይነቱ ሰው ተውበት እንዲያደርግ ይጠየቃል እምቢ ካለ ይገደላል።

ሃይማኖቶች ከሀሳብ የሚፈልቁ አይደሉም፤ ባሮች እንዲከተሉት አላህ በመልክተኞች ላይ ያወረዳቸው ራዕዮች (ወህይ) እንጂ። ሃይማኖትን ለማለት ተፈልጎ ከሆነ <<የሐሳብ ነፃነት>> የሚለው ቃል ከኢስላማዊ መዛግብተ ቃላት መወገድ አለበት። ምክንያቱም ወደዚህ ውድቅ ትርጉም የሚያመራ ነውና። ይህም ማለት ኢስላም ሐሳብ ነው፤ ክርስትናም የአይሁድ ሃይማኖትም ሐሳብ ናቸው (በሐሳብ የመነጩ ናቸው) እንደማለት ነው። እነዚህ ሃይማኖቶች መለኮታዊ ሳይሆኑ የፈለገ ሰው የሚቀበላቸውና የፈለገ ሰው የሚተዋቸው ምድራዊ ሐሳቦች (በሀሳብ የፈለቁ) ናቸው እንደማለት ነው። እውነታው ግን እነዚህ ሃይማኖቶች ሰማያዊ ሃይማኖቶች ናቸው ከአላህ የሆኑ ራዕዮች (ወህዮች) ናቸው። ሰው በነዚህ ሃይማኖቶች አላህን ያመልካል። ሐሳብ ናቸው ማለት አይፈቀድም።

የመልሳችን ማጠቃለያ፦ ሰው የፈለገውን እምነት መከተል
ይችላል የእምነት ነፃነት አለው የሚል እምነት የያዘ ሰው ካፊር
ነው። አላህ እንዲህ ይላል፦

ﻭَﻣَﻦ ﻳَﺒْﺘَﻎِ ﻏَﻴْﺮَ ﭐﻟْﺈِﺳْﻠَٰﻢِ ﺩِﻳﻨًۭﺎ ﻓَﻠَﻦ ﻳُﻘْﺒَﻞَ ﻣِﻨْﻪَ
<<ከኢስላም ሌላ ሃይማኖትን የሚፈልግ ሰው ፈጽሞ ከርሱ
ተቀባይ የለውም፡፡>> 【አል-ዒምራን 3፥85】

ﺇِﻥَّ ﭐﻟﺪِّﻳﻦَ ﻋِﻨﺪَ ﭐﻟﻠَّﻪِ ﭐﻟْﺈِﺳْﻠَٰﻢُ ۗ ِ
<<አላህ ዘንድ (የተወደደ) ሃይማኖት ኢስላም ብቻ ነው፣...>>
【አል-ዒምራን 3፥19】

ማንም ሰው ከኢስላም ውጭ ሌላ ሃይማኖት መከተል ይችላል
የሚል እምነት መያዝ አይፈቀድለትም። ይህን እምነት ከያዘ
ካፊርና ከኢስላም ውጭ መሆኑን ዑለማኦች አቋም ይዘዋል።

【ሸኽ መሐመድ ኢብኑ ሷሊህ አል-ዑሰይሚን ረሒመሁላህ】