Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ለምንድን ነው የኢሳን (አለይሂ ሰላም)፣ የአቡበክር፣ የኡመርን፣ የኡስማንን፣ የአልይን ልደት የማናከብረው?


ለምንድን ነው የኢሳን (አለይሂ ሰላም)፣ የአቡበክር፣ የኡመርን፣ የኡስማንን፣ የአልይን ልደት የማናከብረው?

እነሱ ስሜታቸውን ተከትለው
‹‹የነብዩን (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ልደት የምናከብረው ለሳቸው ያለንን ውዴታ ለመግለፅ ነው፡፡›› ይላሉ
ጥያቄው

ሙስሊም የሆነ ሰው ነብያትን፣ ሰሃባዎችን መውደድ፣ እናት አባቱን መውደድ፣ ኡለማዎችን መውደድ ግዴታው ነው፡፡ ታድያ ከነብያት ውስጥ ለምሳሌ ከ5ቱ የቁርጠኝነት ባለቤት ከሚባሉት ውስጥ የሆነውን ታላቁን ነብይ ኢሳ (አለይሂ ሰላም) ለሱ ያለንን ውዴታ የምንገልፀው የልደት ቀኑን በማክበር ነውን?
በፍፁም
ሰሃባዎችን እንድንወድ ታዘናል፡፡ ታድያ ለምን የአቡበክር ሲዲቅን፣ የኡመርን፣ የኡስማንን፣ የአልይን ልደት አናከብርም?
መልሱም
ስላልታዘዘ እና በዚህ መንገድ ስላልሆነ ለነሱ ያለንን ውዴታ የምንገልፀው፡፡
ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለምን) ከአላህ ቀጥሎ ከነፍሳችን፣ ከልጆቻችንና፣ ከማንም በላይ አስበልጠን መውደድ አለብን፡፡ ለሳቸው ያለንን ውዴታ የምንገልፀው
1) ያዘዙትን ሁሉ አቅም በቻለው መልኩ በመታዘዝ፣
2) የከለከሉትን ሁሉ በመከልከል፣
3) የተናገሩትን ሁሉ እውነት ነው በማለት፣
4) የተዉትን፣ ያላሳዩንን እኛም በመተው፡፡ ምክንያቱም መልካም ሆኖ ያላሳዩን ነገር የለምና፡፡
5) ሰለዋት በማውረድ እና የመሳሰሉትን

እሳቸው በህይወት በነበሩ ግዜ አላህ ዘንድ የተከበረ፣ የተወደደ፣ ቅርብ የተባለው ወንድማቸውን ኢሳን (አለይሂ ሰላም) ልደት ነሷራዎች ቢያከብሩትም እሳቸው ግን አላከበሩትም፡፡ በጣም የሚወዷት ልጃቸው ፋጢማ (ረድየላሁ አንሃ) ልደቷን አክብረውላት አያውቁም፡፡ ምክንያቱም አላህ እንዳላቸው ‹‹ወዳንተ የተወረደልህን ተከተል›› እሳቸው ከአላህ የታዘዙትን ብቻ ነው የሚከተሉት፡፡

በሸሪዐችን አቂቃ የተባለ አንድ ሰው ሲወለድ ደስታችንን በግለጫ፣ ጌታችንን ማመስገኛ ወንድ ልጅ ከተወለደ 2 በግ፣ ሴት ልጅ ከተወለደች 1 በግ ይታረዳል፡፡ አበቃ፡፡
ታድያ ለነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለምና) ለነዛ ውድ ሰሃባዎች የበቃቸው ዲን ለእኛ አይበቃንምን?
ሱና ላይ እንቁም ከሃቅ በኋላ ጥመት እንጂ ሌላ የለም፡፡ ከሱና በኋላ ቢድዐ እንጂ ሌላ የለም፡፡

‹‹እኛ መውሊድን የምናከብረው ለነብዩ ያለንን ውዴታ ለመግለፅ ነው፡፡›› የሚሉ ሰዎች የሚከተሉት ምርጦች
-) ሙሃጂሮች፣ አንሷሮች፣ 10ሩ የጀነት ሙሽሮች፣
-) ታቢኢኖች፣ አትባኡ ታቢኢን፣
-) ኢማም አቡ ሃኒፋ፣ ኢማሙ ማሊክ፣ ኢማሙ ሻፊኢ፣ ኢማሙ አሕመድ፣
-) ኢማሙል ቡኻሪ፣ ኢማሙ ሙስሊም፣ ነሳኢ፣ አቡ ዳውድ፣ ትርሚዚ፣ ኢብን ማጃ፣ እነ ሱፍያን አሰውሪ፣ እነ አብደላህ ኢብን ሙባረክ፣ እና ሌሎችም ፈርጦች አይወዷቸውም ነበርን ልትሉን ነው?

ወይንም እንዴት ውዴታቸውን መግለፅ እንደነበረባቸው አልገባቸውም ወይንም አያውቁም ልትሉን ነው?
ይልቁንስ መውሊድን የጀመሩት የነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም)፣ የሰሃባዎችና፣ የአማኞች ጠላቶች የሆኑት ሺዐዎች ናቸው፡፡ ይህ ብቻ ይበቃናል ሸር ለመሆኑ፡፡
አላህ ሃቁን ይምራን፣ በሃቅም ላይ ያፅናን፡፡