Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

የጥቅም ሰው በጣም አደጋ ነው። ሰሞኑን በድፍረት "መውሊድ" ብሎ መፀሀፍ የፃፈው አጥማሚ እስቲ ትንሽ "ሪዋይንድ (ወደ ኀላ)" ላስታውሳችሁ።

የጥቅም ሰው በጣም አደጋ ነው።
ሰሞኑን በድፍረት "መውሊድ" ብሎ መፀሀፍ የፃፈው አጥማሚ እስቲ ትንሽ "ሪዋይንድ (ወደ ኀላ)" ላስታውሳችሁ።
1) ከአመታት በፊት የተውሂድ እንቅስቃሴ በጣም ጠንካራ በነበረበት ወቅት "አል–ኢርሻድ" የተሰኘውን የሸይኽ ፈውዛን ኪታብ ተርጉሞ ለገበያ አቅርቦ ነበር።
2) ከዛም የኢኽዋን እንቅስቃሴ አገራችን ላይ በተለይ የዩኒቨርሲቲ ተማሪ፣ ዘመናዊ ትምህርት የተማረው ሙስሊም፣ ወጣቶችና አርቲስቶች ሲቀበሉት በጣም ብዙ የሚባሉ የኢኽዋነል ሙስሊሚን መሪዎችን idiology በመተርጎም ለገበያ አቅርቦ ሸጠ። ለምሳሌ የጠሞ አጥማሚው ዩሱፍ አል ቀርዳዊ።
3) የሰው የማንበብ ፍላጎት እየደከመና ፊልምና ድራማ ላይ እያተኮረ ሲመጣ የጀዛ ፊልም ምርቃት የሚሉት ላይ ብቅ አለና "1000 ገፅ ኪታብ ከመፃፍ፣ የአንድ ሰዐት ፊልም ፓወር አለው።" ብሎት አረፈ።
ይህ ሰው ራዲዮ ላይ ቀርቦ ዘፈን መፍቀዱ የሚረሳ አይደለም።
4) አወልያ ላይ የተጀመረው ሰላማዊ ሰለፍ፣ ከዛም አንድነትና ሰደቃ ፕሮግራም እየተባለ በየመስጂዱ ሲደረጉ የነበሩት ድርጊቶች ውስጥ ነበረበት። ለምሳሌ አየር ጤና መስጂድ የተደረገው "አንድነትና ሰደቃ" ፕሮግራም ላይ ሲሰብክ ነበር። ከዛም አካሄዱን ሲያየው አላምረው ሲል "መንታ መንገድ" አለና "የአመቱ ምርጥ ተፅኖ ፈጣሪ" ሲሉት የነበሩትን ተከታዮቹን ጥሏቸው ተቀየሰ። ሰላማዊ ሰልፏ ብታዋጣ ኖሮ??? መጅሊሷ ላይ ከፊት ገጭ ወይንስ???
5) ከዛ እነዛ "የአመቱ ምርጥ" ብለው ያወደሱት የቀድሞ ተከታዮቹ እንደተጣሉት ሲያውቅ ትላንት "አል–ኢርሻድን" በተረጎመበት እጁ ዛሬ የቀብር አምላኪዎች ታላቅ አምልኮ፣ የሽርክ መናኻርያ፣ የቢድአ ቁንጮ፣ የፊስቅ መናኻርያ፣ የሙስሊሙ ኪስ ማውለቂያ የሆነውን መውሊድ ይቻላል ብሎ መፀሀፉን ሊሸጥ ከተፍ አለ።
አሁን ደግሞ አህባሾች፣ የማያውቁ ሚስኪኖችን ለነሱ ያሰበ አስመስሎ፣ መውሊድ ቢድአ ነው የሚሉት የነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ቤተሰቦችን አይወዱም አይነት መርዙን እየረጨ ነው።
እነሱም በሆነ ጉዳይ አይንህን ላፈር ሲሉት በምን ይሆን የሚነግደው???
አላህ ከኢኽዋን ተንኮል ይጠብቀን።