Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ለምንድን ነው መውሊድ አደጋ ነው ብለን የምንጫጫው? ከ 75 በላይ የሽርክ ስንኞች


ለምንድን ነው መውሊድ አደጋ ነው ብለን የምንጫጫው?
መውሊድ የሽርክ መናሃርያ ስለሆነ ነው::
ይህን ለማረጋገጥ የሚከተሉትን መውሊድ ላይ የሚባሉ የሽርክና ቢድዓ ስንኞች እስቲ ልብ በሉ፣ ተጠንቀቁ አስጠንቅቁ
1. በዝቶብኛልና አያሌ ነገር አቤት ብዬ ልጩህ እባሮቹ በር ቀሌቤን ወዳሳቸው አድርጌ ሰንዘር አቤት ጮህኩባችሁ ጌቶቼ ዱስቱር ከሙስጠፋ ይዤ እስከ አቡል በሸር አምቢያ ሙርሰልም አንድ እንኳን ሳይቀር
2. በዘመን ያላችሁ ሳዳቶች አኽያር ቀኝ እጄን ጨብጡኝ ወድቄ እንዳልቀር ሺሊላህ ጌቶቼ አርሂቡ ዱስቱር መቼም ያለናንተ ሁለም አያምር በናንተ የሸሸ ምንም አያፍር ጌቶቼ አትለፉኝ አዳቤም ባያምር አደበቢስ ቡልሀ እንደኔ ቢኖር ባሪያ ሲባሌ ማጥፋት እለት ነው እድር ለናንተ ይገባል ያጠፋን መማር፡፡
3. አልሀምዱሊላሂ ይመስገን ገፋር ቀልቤን ያዞረልኝ ወደናንተ በር በናንተ የሸሸ ያገኛል ሹም ሽር ሊለግስ ነው መሰሌ ዳመናው ዟዟረ የስልካችሁ ንባብ ይሰማ ጀመረ፡፡
4. ሁለም ባንድ ሆነው ከሙስጠፋ ጋር ዛሬ ይድረሱልን ላገኘን ችጋር
5. አንተል ቁረይሺዩ አንተ ነብዩና ቢሲሪ ሲሪከ ዘይን ባጢነና
6. የቦረናው ደግዬ እርዱኝ አባብዬ
7. ሰለፍም ኸለፍም ማወረአል ባህር በሁለም ሸሸሁኝ አንድ እንኳን ሳይቀር ከዛፍ ከቅጠሉ በዝቶብኝል ነውር እሜዳው ላይ ሆኜ ወድቄ በዱር መግቢያ በር አጥቼ ታግቼ ባጥር አልሄድ ወደፊት ወደኋላ አልበር በቀኝ በግራዬ እሳት ገደል ባህር አቤት ጠራኋችሁ ጌቶቼ ዱስቱር፡፡ ረዳቴ ማንነው ከናንተ በቀር
8. የአበራ ሙዝ አባት የማይደፈር አቤት ይታይልኝ ምነው የኔም ዱር ዘሩልኝ ጌቶቼ በአውን በነስር ከጃችሁ ከጅዬ ቆሜያለሁ ከበር፡፡ በናንተ የሸሸ ምን ጊዜም አያፍር ሀጃዬን አውጡልኝ በዟሂር በሲር
9. ሺሊላህ ያሰይድ አብዱል ቃድርእርዳታቸው አይውል አያድር
10. ሺሊላህ ሸህ ሙሃመድ ባህሩለጠራው ደራሽ ነው ምን ቢርቅ አገሩ፡፡እኔስ ይገርመኛል የሰው ነገርይላል እንዘይር ቀልቡን ሳያጠራየማያውቁ መስሎት የቀልቡን የሰድሩን
11. መጀን በኑር ሁሴን በአሩሲው ኑር የአውሉያዎቹ ሻምበል የበርም የባህር ከራማው ይፋ ነው አይደለም መስቱር እጣው እንደ ነቢይ በርዳዳው ገበር፡፡ የሪጀልች አባት የነዚያ ያብራር የነአህመድ ኑረላህ ዚልፈይዲል ሚድራር ተብል አላህ ዘንዳ በሻሀው አብሽር ጌታዬ ኑር ሁሴን በለኝ እንጂ አጀብ በለኝ የኔ አሽከር በዱንያ በአኸይራም እንዳልቸገር በናንተ የሸሸ እንዲሁም አይቀር አላህ ሰጥቷቸኋል ሳይሰፍር ሳይቆጥር፡፡
12. ጌታችን ቃዲር እኩሉንም አለው አብሽር አጋፍር አልብስም አጉርስም አመኩስ አክብር ኢንስም ጂን ቢሆን በጫማህ ይደር ይፍራህም ይወቅህ አውሪ እንኳ በዱር አውቆና ለጥቆ ሰልቶ ባንተ አምር ለሀልቁ ገበያ መድሀኒት ነበር፡፡ የቸገረው ሄዶ የለውም ማፈር ከሀያቱ በልጧል ውለታው በቀብር ወዲያልኝ የሱ ጉድ አያልቅም ይቅር
13. የሀድራ ጦያራ ይዞ የሚበር ሲጠሩት ፈጣን ነው ቶል የሚሀድር ተምኪን የተሰጠው ዞሂር ወባጢን እኔ ያለሁበት እክጀላ በር ቀድሬም አያደርሰኝ መቃም ለመቁጠር ስንቱን አሳደገው ገና በነዝር ፈይዱ ከአፍ ሲፈልቅ የአጀብ ነበር እንኳን ሰው መላኢካ ያዳምጠው ነበር፡፡
14. ጌታው ሰይድ አህመድ የደባቱ ኑር ዶላል ያስፈቀተው የዲኑ ጨረር ስፍር ቁጥር የለው ስንቱ በእጁ ሻረ አላህ ዘንድ ነበር ተናግሮ የማያፍር ቢያለብስም ቢገፋም ቢያደኸይ ቢያከብር ይግባኝ የለበትም በፈረደው አምር ተብሎ አላህ ዘንዳ በሻሀው አብሽር
15. ጌታው ሸረፈዲን የደግየው ኑር አላህ ትላቅ እጣ አድሎት ነበር ሰውም ጂንም ቢሆን አውሬውም የዱርሁለም አቤት ብሎ ተገዝቶ ነበር ጥላው የሚበቃው በሁለት አገር በሱ ይወሰላል እስላምም ካፊር ሴትም ወንድ ቢሆን አብድ ቢሆንም ሁር በሱ ተወስል የለውም ችጋር
16. ይመነጥቁታሌ ያወጡታሌ ከጭንቅ
17. እኝህን ሳዳቶች ድረሱ አንበላቸው እሱ ወደደና እሱ መረጣቸው አመሀባው ባህር ሺህ አመት አስዋኛቸው፡፡ እሱ ወደዳቸው በፊት ሳይሰራቸው ዩሂቡሁም ወዩሂቡነሁ አላቸው ጀባሩ፡፡ አቤት እርዱኝ ይላል የቤት ልጅ አሽከሩ በናንተ የሸሸ የቂን ነው ማማሩ ጥላቸው ጠባቂ በሁለት አገር
18. ደግሞ ጌታ ሰይድ የማይባሩ ኑሩ ረህመት አድርጎ አላህ አዝልቆት ነበረ ለኸልቁ ነበረ በልግና መህር ሰውም ጂንም መላኢካም ተገዝቶ ነበር
19. አልዩ ሀይደር ነበረ ለነቢ ማኖሪያ ሚስጥር ኢልመልገይብ ከሱ ይጠየቅ ነበር፡፡
20. ሙሀመዱ ሰማን ገፍታሪው ቀደር
21. ሸህ ሙሳ ሰገራት ውስጡ ላዩ ኑር የከሽፋን መነጥር ታድል ነበር፡፡
22. ሸህ ሙሀመድ ሸሪፍ የርጎየው ገበር ሲሞድህ ሙስጠፋን እያየ ነበር፡፡
23. ሰይድ ቡሽራ ገታ ቀምጣላው ገበር ከልካይ የለበትም ሲዘልቅኝ እልፍኝ በር ጨወታው ነበር ቀዷ ቀደር ጋር ከሙስጠፋ ጋራ የሚነጋር ማሂሩ ወጌሻ ለዟሂር ለሲር ስንቱ በሽተኛ ዛቱን አይቶ ሻረ ሰውም ጂንም ለሱ ታጠቀ ገበረ ከራማ በበጠልሻ ነዳፊ ነበረ ሙቶም በሀያቱ ጠቃሚ ገበር፡፡
24. መጂት ሀጅ ቡሽራ የራቀው ገበር አገላባጭ ነበር የቀዷ ደብተር ለውሀል መህፉዝ አይቶ ነበር ሲናገር፡፡
25. እነሀጅ አረቦ የሳልመኔው ኑር ሀለዋውን ያደረገው ከነብዩ ጋር
26. ሸህ መሀመድ ፈቂህ ባለመነጽር የታደለው ገበር ከአላህ ዘንዳ ሲር
27. ለካ ገረዋ ላይ አብርቷልጀምበር ሲፈቱ መለኪያ ዛቱ በበሽር ተብሎ አላህ ዘንዳ በሽር ወአንዙር ጎራ የማይጋርደው ይዟል መነጸር ይናገር ነበረ የዟሂር የሲር ይገልጠው ነበረ የኸልቁን ሀጢር
28. እንደሁሴን ጂብሪል ደግሞ ማን ነበረ የከሽፉን መነጸር አይኑ ላይ ነበር የፊቱን የኋላን ይናገር ነበር ሁለም ተገላሌጦ ይታየው ነበር፡፡
29. እነሸህ ሀቢቡ ጉደኛው ገበር ከአርሽ እስከ ሰራ ይታየው ነበር አላህ እድርጎት ነበር የሚስጥር ሰፈር
30. ቁንዲ ሸህ አብደላ ወልዩ ገበር ከአላህ ጋር የፈጀው ሚስጥሩን በሲር ይናገረው ነበር አሟቱ በቀብር
31. አላሁ መሰላ አላ ሙሀመዴ መገን ነቢ የሁለ ቀላቢ
32. የቃጥባሪው ጌታ ኢሳ የአላህ ኑር ከሚን ኢንደላሂ የተባለ አብሽር
33. ለገሂዳም ጃማ ስንቱ ጉድ ነበር እነ ነብዩ ሀድራ የተባሉ አብሽር ባልከው ይሁን ያለው ገና ሲፈጠር
34. ጌታው አባ ረህማ የአውሉያ መምህር ጨዋታው ነበረ ሰይድ ከድር ጋር ሁለም ከሀድራው ይቀስም ነበር፡፡
35. ኢስማኢል ጀበርቲ ጉድ ያለው ነበር ከራማው እንደ ባህር የሞላው ገበር ሰውንም ጂንም ጨልጦ የሚያስቀር እሱነው ይባላል የቃማቴ ሲር
36. እነሱ ይበራሉ በመቶ ሃምሳ ጀት እኛ ቀደምናቸው በአንድ ዘርባ ጫት
37. ሰለላሁ አለይከ፤ ነቢ አለኝታዬ፤ሰለላሁ አለይከ፤ ባለ ውለታዬ፤ሰለላሁ አለይከ፤ሳሎኔ ጋዳዬ፤ሰለላሁ አለይከ፤ እጣዬ ፋንታዬ፤ሰለላሁ አለይከ፤የሚሰትሩ (የሚደብቁ) የኔን ገመና፡፡››ይላል፡፡
38. ሰለላሁ አለይከ፤ አንቱን የሚጠራ፤ሰለላሁ አለይከ፤ እሱ ልቡ ጠራ፤ሰለላሁ አለይከ፤የለበት መከራ፤ሰለላሁ አለይከ፤ አኸይራ ሲጠራ፤››ይላል
39. ሰለላሁ አለይከ፤ የእኔ ፍላጎት፤ሰለላሁ አለይከ፤ አይደለም ጀነት፤ሰለላሁ አለይከ፤ቢያሳየኝ ሙሚት፤ሰለላሁ አለይከ፤ ያንቱን ፊት ማየት፤ሰለላሁ አለይከ፤ አንቱ ኖት ለኔ የጀነት ጀና›› ይላል፡፡
40. ሰለላሁ አለይከ፤ እንዳንቱ የሚሆነኝ፤ሰለላሁ አለይከ፤ መቼም አላገኝ፤ሰለላሁ አለይከ፤ዘይኔ ቅረቡኝ፤ሰለላሁ አለይከ፤ ጣል አታድርጉኝ፤ሰለላሁ አለይከ፤ ካንቱማ እርቄ አልችልም እና፤ያምስኪ መዲና ጋየተል ሙና፤››ይላል፡፡
41. ሰለላሁ አለይከ፤ ካንቱ ጋር የዋለ፤ምንኛ ታደለ፤ሰለላሁ አለይከ፤ ነቢ ነቢ እያለ፤ጭንቀቱ ቀለለ፤ሰለላሁ አለይከ፤ እኔም ልጥራዎት ጨንቆኛል እና፤ያምስኪ መዲና ጋየተል ሙና፤››ይላል፡፡
42. መሻር ባንቱ ነው ያደዋኡና፤ያምስኪ መዲና ጋየተል ሙና፤››ይላል፡፡
43. የጀሊል ባለሟል የሆኑት ሃቀኛ፤ምነው ብታሽረው ያንን በሽተኛ፤ሙሃባው ተነጥቆ የሆነ ደመኛ፤ ሀቢቢ ሀቢቢ ሀቢቢ›› ይላል፡፡
44. ‹‹መደድ እና መደዴ›› ብለው ይጠራሉ፡፡
45. ‹‹ሃቢቢ ሃቢቢ ሃቢቢሃቢቢ ሃቢቢ ሃቢቢመዲና ና ይበሉኝ››
46. ‹‹አብሽር ወንድሜ ግባ በቶሎ፤ ማነው ያፈረው ያነቢ ብሎ››
47. ‹‹አንቱን ጠርቼ ምን አጥቼ፤ ልሙት ፈንድቼ ልዬትና፤ አህመድ ሙሽራ የመዲና››
48. ‹‹የፍቅር ነጋሪ ዝም ብዬ ልምጣ፤ባካችሁ ይቅር ሌላው ሀተታ፤ጠዋትም ማታ ጀበል ወትውቱ (አጥብቃችሁ ጠይቁ)››
49. ‹‹አገር የጀበል፤ ግዜው የጀበል፤ደውላው የጀበል፤ እባክህ ጀበል በል፤በፍቅሩ ታጠብ ጠጣ ወተቱ››
50. ‹‹ጥንትም እሱ ነው፤ አሁንም እሱ፤ዛሬም ወደፊት እሱ ነው እሱ፤ይኖራል ነግሶ አለምን ገዝቶ››
51. ‹‹እባኮት ሙሂዬ፤ ሁኒልኝ ሸፈአዬ››
52. ‹‹ነበው ዲጅዋ ዲጁ ነብዮ ዲጅዌ››፤ ‹‹አርሂቡ ነቢ አርሂቡ ነቢ››፤ ‹‹ግቡልን የተንቢ››፤ ‹‹መርሃባ ነቢ መርሃባ››
53. ‹‹ሰላሜ አላ ገውሰል ኢባዲ፤ዳኢመን ቢላ አደዲ››፡፡ ይላል መንዙማው
54. ‹‹አንተ የጠይባው ነጋዴ፤ሰላም በልልኝ አህመዴን፤አንቱ የጅብሪል ጋደኛአትርሱን ቀብር ስንተኛ››
55. ‹‹አለሁልህ በሉኝ፤ዘይኔ አይራቁኝ፤ምግብ ውሃ አይለኝ፤ አንቱን ካገኘ ሁዴ፤ኒዛሙል መደዴ›› ይላል
56. ‹‹ነቢ አንቱን እያለ፤ቀልቤ ጥሎኝ ዋለለ፤ወዳሉበት ደወለ፤ሄሎ በሉት አህመዴ›› ይላል
57. ‹‹ቀልቤ እኮ አንቱ ጋር ነው፤ፍላጎቱ ረውዳ ነው፤ዘይኔ ና በሉት ፈጥነው፤የቀረውን ጀሰዴን›› ይላል
58. ‹‹በሙስጠፋ እጅ ነው፤የጀነት ቁልፍ ያለው፤አላህ ነው ያስረከበው፤ለዚ እኮ ነው መውደዴ›› ይላል
59. ‹‹አንቱ ኖት ረሃቤ ጥሜ፤ልንገሮት አስቀድሜ፤ያላንቱ አይሞቅም ደሜ፤ግቡልኝ በጀሰዴ›› ይላል
60. ‹‹ና በሉት ኸይረል ወራ፤ ሳልሞት ሳልሄድ አኸይራ፤ ያቺን ረውዳ ዚያራ፤ የጀነትዋን አርዴ›› ይላል
61. ‹‹የሰለዋት አንበሳ፤ እንዳይመስልህ ኮሳሳ፤ ጀሰዱማ ቢከሳ፤ አለው ካሳ ከአህመዴ፤ ኒዛሙል መደዴ›› ይላል
62. ‹‹ካልመጣሁኝ መዲና፤ እኔስ የለኝም ጤና፤ እንድሆንሎት ደህና፤ ቶሎ ጥሩኝ አህመዴ፤ ኒዛሙል መደዴ›› ይላል
63. ‹‹ያረሱለላሂ ሸፈዐ ይሁኑና የቢላል እኮ ነን በዲኑ የፀና››ይላል
64. ‹‹ዘይኔ ይበቃናል ኑ በሉን መዲናሀይ እንድናደርገው ሁሌ የርሶን ሱና›› ይላል
65. ‹‹ሰብርም የለኝም አለሁኝ ታምሜመንገዱ ጠፍቶብኝ አልቻለም አቅሜጉልበቴ ብርታቴም ባንቱ ነው መቆሜ›› ይላል
66. ያቀመረል መካ አሰላሙ አለይካልቤ ባንቱ በእርሶ ተመካ
67. በዘመን ያላችሁ ሳዳቶች አህያርቀኝ እጄን ጨብጡኝ ወድቄ እንዳልቀርሺሊላህ ጌቶቼ አርሂቡ ዱስቱርመቼም ያለናንተ ሁሉም አያምርበናንተ የሸሸ ምንም አያፍር ጌቶቼ አትለፉኝ አዳቤም ባያምርአደበቢስ ቡልሀ እንደኔ ቢኖር ባሪያ ሲባል ማጥፋት እለት ነው እድርለናንተ ይገባል ያጠፋል መማር፡፡
68. አላሁመሰሊ አላ ሙሀመዲመገን ነቢ (በጣም ይገርማሉ ነቢ)የሁሉ ቀላቢ
69. ለካም አንቱ ነሁ ያነቢለመላው ኸልቅ ቀላቢብትን ያለውን ሰብሳቢበሶፋ ቡራቅ ጋላቢ
70. ያሙሀመዲ ያሀቢቢያሙሀመዱ ኩን ጠቢቢ (ዶክተሪ ሁኑ)ወአጂርኒ ሚን ለሂዲ(ከእሳት ጠብቁኝ) ኢነ አውዛሪ ሲቃል(ወንጀሌ ከባድ ነው)
71. ‹‹ጀማሉል አለም ሰለላሁ አለይሂ ወሰለምወደ ጀይላኔ ቢወረውረውለውሀል መህፉዝን አስመረመረውበአለም ተሹሞ ብዙ ጉድ እያስወገዱበባግዳድ ምድር ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም እሳት ነው ፍቅር››
72. ‹‹ሺሊላህ ሺሊላህ ኢማሙ ግቡልንሙሃመድ ነው ዋናውእስቲ ላነሳሳው የኔ አቡል ጀበል (ሰልማን የሸይኽ ኢሳ ቃጥባሬ ልጅ)ፍቅሩ በልቤ ውስጥ እንደ እሳት ይቃጠልጠበሉን ገብቼ ታጥቤ ልወልወልየቀረውን ትቼ የእርሱን ቃል ልከተል››
73. ‹‹የፍቅርህን ጥም አይበርድም በውሃአንተን የወደደ አይባልም ደሃትረዳ የለም ወይ ከየትስ በረሃሊጋባ ነህ አሉ ያረሱል ያጣሃ››
74. ‹‹ቁጥርም የለውም የከራማዉ አይነትይጎበኛል አሉ ልጆቹን በእውቀትብርቱ ነው መሳሪያው ጠላትን ለማጥፋትርህራሄው በዛና ቻለ እስከዚህ ወቅት››
75. ‹‹ሳዳቴ አደራ አሁን ለምነናልሁላችን በጅምላ አድሉን ብለናልዱስቱር ዱስቱር ብለን እዛው አፍጠናልአትጨክኑብን እርሶን ለምነናልይሀው ደውለናል በቴሌ ግራሙ ግቡልን ይሀው ለምነናል በቴሌ ግራሙ ግቡልን››
76. ‹‹ግቡልን በማለት ጠራ መሀይሙአንተን በመውደዱ ሄደለት ህመሙልቡ ተሸበረ እንዳየ በህልሙአንተ ነህ ፀሎቱ ስግደትና ፆሙመወትወት ጀመረ ቢፈላበት ደሙ››
77. ‹‹ወጣቶች ዘፈኑ በስልት እያዜሙ እያሉ ይጠሩሃል ሺሊላህ ኢማሙይመጀኑብሃል ቂምሃ እየቃሙማስደሰት አለብህ በኋላ እንዳያሙህባንተ እኮ አያምርም ስትል ዝም ዝም ግቡልን…››
78. ‹‹ሺሊላህ ሺሊላህ ኢማሙ ግቡልንመተኮስ ጀመረ የፍቅር ተኳሹበወዳጆቹ ልብ እንደ ምንጭ ፈሳሹየረሱል መስለኔ አላጋውን ወራሹየልብን መርማሪ እሱ ነው ፈታሹ››
79. አላሁመሰሊ አላ ሙሀመዲአላሁመሰሊ አላ ሙሀመዲመህቡቢላሂ (የአላህ ውድ)ጃሚኢ ሲፋቱላሂ (የአላህን ባህሬ ጠቅልለው የያዙ)
አላህ ግን ስለራሱና ከእርሱ ውጭ ስለሚለመኑት እንዲህ ይላል
ذَٰلِكُمُ ٱللَّهُ رَبُّكُمْ لَهُ ٱلْمُلْكُ ۚ وَٱلَّذِينَ تَدْعُونَ مِن دُونِهِۦ مَا يَمْلِكُونَ مِن قِطْمِيرٍ
ይህ ጌታችሁ አላህ ነው፡፡ ንግሥናው የእርሱ ብቻ ነው፡፡ እነዚያም ከእርሱ ሌላ የምትግገዟቸው የተምር ፍሬ ሽፋን እንኳ አይኖራቸውም፡፡
إِن تَدْعُوهُمْ لَا يَسْمَعُوا۟ دُعَآءَكُمْ وَلَوْ سَمِعُوا۟ مَا ٱسْتَجَابُوا۟ لَكُمْ ۖ وَيَوْمَ ٱلْقِيَٰمَةِ يَكْفُرُونَ بِشِرْكِكُمْ ۚ وَلَا يُنَبِّئُكَ مِثْلُ خَبِيرٍ
ብትጠሩዋቸው ጥሪያችሁን አይሰሙም፡፡ ቢሰሙም ኖሮ ለእናንተ አይመልሱላችሁም፡፡ በትንሣኤም ቀን (እነርሱን በአላህ) ማጋራታችሁን ይክዳሉ፡፡ እንደ ውስጠ ዐዋቂው ማንም አይነግርህም፡፡
ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ደግሞ ‹‹ከአላህ ውጭ ያለን እየጠራ የሞተ ሰው የእሳት ነው፡፡›› ብለዋል
በጣም የሚያሳዝነው ይህን ሁሉ ሽርክ ያቀፈውን ቢድዐ ‹‹ፕሊስ አታንሱት፣ አንድ ነን፣ መውሊድ አይለያየንም፣ መውሊ አቂዳ አይደለም መውሊድ ቅርንጫፍ ነው፣ እና የመሳሰለውን›› እያሉ ኡማውን ጥመት ላይ እንዲተኛ የሚያደርጉት የስሜት ተጣሪዎች አሉ፡፡
ይህን ሽርክ ያለበትን የቢድዐ ተግባር የሚፈፅሙ ሰዎች ሃቅን ተረድተው መመለስ ሲጀምሩ እነዚህ እንቅፋቶች መሃል መንገድ ላይ ተቀምጠው ‹‹መውሊድ አይለያይም›› እያሏቸው መልሰው እንዲያፈገፍጉና ባሉበት ሽርክ ላይ እንዲጨማለቁ ያደርጓቸዋል፡፡ አላህ ዲን አጥፊዎችን ሁሉ ይምራቸው፡፡
የአላህ ባርያዎች ሆይ! አላህና መልክተኛው (ሰላለሁ አለይሂ ወሰለም) አለማዘዛቸው፣ ቢድዐ ብቻ መሆኑ ሳይሆን ይሀው ዱንያ አኸይራ የሚያጠፋ ሽርክ አቅፎ ይዟል፡፡ ይህንን ጉዳይ ደግሞ አያገባንም ማለት ይከብደናል፡፡ የሙስሊሞች ጉዳይ ማሳሰብ ማለትም እነሱን ከሽርክና ቢድዐ ማስጠንቀቅን ከምንም በፊት ይይዛል፡፡ አላህ የሱን ፊት ብቻ ፈልገው ከሚሰቱት ያድርገን፡፡
የአላህ ሰላትና ሰላም በነብያት ሁሉ መደምደሚያ፣ በቤተሰቦቻቸው፣ በባልደረባዎቻቸውና ሃቅን በተከተለ ላይ ሁሉ ይሁን፡፡
https://telegram.me/SadatKemalAbuMeryem