Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

እውነታ በውዥንብር አይረታ ! ሸይኽ ዑሰይሚን(ረሂመሁላህ) እንዲህ ብለዋል

በኡስታዝ ሱልጣን ከድር… ✍

ሸይኽ ዑሰይሚን(ረሂመሁላህ) እንዲህ ብለዋል፦
"እኛ የምንለው ፦
ሰለፍ ማለት አህሉ ሱና ማለት ነው፣ የአህሉ ሱና መገለጫ ከነሱ ውጭ ለማንም አይሆንም።በጭራሽ!
"አህሉ ሱና ወልጀማኣ ሲባል (ሰለፍዬች፣አሽኣሪዬች እና ማቱሪዲዮች ናቸው።" የሚል ተሳስቷል።
ይህ ስሕተት ነው!!
ሁሉም አህሉ ሱናህ ሊባሉ ይችላልን?
ከሐቅ በኋላ ጥመት እንጂ ሌላ የለም።
አንዱ ሌላኛው ላይ ምላሽ እየሰጠ እንዴት ሆኖ ሁሉም አሕሉ ሱና ሊሆኑ ይችላሉ?
ይህ ሊሆን ፈፅሞ አይቻልም፣ምናልባት ሁለት ተቃራኒ ነገሮችን በአንድ ላይ ማሰባሰብ ከተቻለ እንጂ!!
ከነዚህ አንጃዎች አንዱ ብቻ ነው አህሉ ሱና ሊሆን የሚችለው።
እሱ ማነው?
አሽኣሪያ?
ወይስ ማቱሪዲያ?
ወይስ ሰለፊያ?
ሱናን የገጠመ እርሱ አሕሉ ሱና ነው፣ሱናን የተፃረረ እርሱ አሕሉል ቢድዓ ነው።
እኛ የምንለው ፦
ሰለፍ ማለት አህሉ ሱና ማለት ነው ከሰለፊዮች ውጭ የአህሉ ሱና መገለጫ ከነሱ ውጭ ለማንም አይሆንም።በጭራሽ!"

【"ሸርሑ ዐቂደቱ አልዋሲጢያ"(1/33_34)】
(የመክተበቱ ጠበሪያ ህትመት አንደኛ ዕትም)
https://telegram.me/sultan_54