Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ለባለቤትሽ ተዋቢ


ለባለቤትሽ_ተዋቢ

የሚያሳዝነው ብዙ ሴቶች መዋብን እና መጋጌጥን ከቤት ለሆነ ጉዳይ ወይም ስብሰባ ለመውጣት በፈለጉ ግዜ እንጂ አያውቁትም፤ የባልን ሐቅ በተመለከተ ግን ፡ ወደ ቤት በገባ ግዜ በተጎሳቆለ ልብስ፣ጥሩ ባልሆነ ሽታ፣ በተነጨባረረ ፀጉር ፣ እንዲሁም እሱ ወደሷ ያለውን ፍላጎት የሚገቱ ገፅታዎችን ተላብሳ ትቀበለዋለች።
ታድያ እንደዚህ አይነት ገፅታን ወደ ተላበሰች (ሚስት) ምን አይነት ፍላጎት የዚህን ባል ቀልብ ሊሞላ ይችላል?
ከሱጋ ሁኔታዋ እንዲህ ከሆነ፣ ምን አይነት ፍቅርስ ልቡን ከቦ ሊይዘው ይችላል?
ይሄ የሴቶችን ሞኝነት እና የትዳራቸውን ህይወት ለሟሟላት እንዲሁም (ትዳር ውስጥ) ያላቸውን ደረጃም ለመጠበቅ ፤ ያላቸውን የአስተሳሰብ ጉድለት የሚያመላክት ነው።

።።።።።።።።።።።።።።።።

የመልካም ሚስት ባህሪ ከሚለው የሸኽ አብደረዛቅ አልበድር ሀፊዘሁላህ
ኪታብ ከገፅ 24 የተወሰደ
#تجمّلــــــي_لزوجِـــك
-
-
ومـــن الأمور المؤسفة أنّ كثير من النّساء لا تعرف الزّينة والتّجمّل إلا أذا أرادت أن تخرج من البيت ، وتغادره لحضور مناسبة أو اجتماع ما أو نحو ذلك ،
أمّا فيما يتعلّق بحقّ الزوج ، إذا دخل فتلقاه بثياب رثّة وبرائحة غير طيّبة ، وبشعرٍ شعث ، وبصفات تصدّه عنها وتقطع من رغبته فيها ،
فأيّ رغبة تملأ قلب هذا الزوج ، تجاه من هذه صفاتها ؟ ،
وأيّ حبّ يكتنف جوانحه إذا كان هذا شانها معه ؟ ،
وهذا مـن دلائـل حمــق المــرأة ، وقلّــة عقلِهــا في تحقيق كمال الحياء الزوجية ، وتحقيق سموّها ورفعتِها .
----------------------------------------------------------------
من كتاب صفات الزوجة الصالحة (صـ 24)
للشيخ عبد الرزاق بن عبد المحسن البدر حفظه الله

ዋነው ትዳር መያዙ ብቻ በቂ አይደለም ሀቅም ጠብቂ እህት

እናም እህቴ ንፅህናሽን ጠብቂ አምረሽ ተውበሽ ጠብቂው ! በተገላቢጦሽ ከሆንሽ ግን እንደሚንቅሽ በእሱ ዘንድ ያለሽ ክብረወ እንደሚቀንስ በልቡ ውስጥ ላ ንቺ ያለው ፍቅር መንምኖ እንድያልቅ አትዘንጊ! በመሀከላችሁ ደግሞ ፍቅር ከሌለ አስቢው ቀሪው ሂወትሽ ምን እንደሚሆን?

" ሴት ልጅ እንደ ግላስ( ብርጭቆ) ነች አንደ ከተሰበረች መጠገን አችልም" እና ልብ በይ
ውዷእህቴ የባልሽን ሀቅ አደራ!

አላህ የመልካም ሚስት ባህሪን ያላብሰን የባል ሀቅ ጠባቂ ያድርገን
ላገባችሁ አላህ ጥሩ ሚስት ያድርጋችሁ ላላገባችሁ አላህ ጥሩ ትዳር ይወፍቃችሁ።